Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ጉሎ ለአማራጭ የሃይል ምንጭ ሊውል ነው
ጉሎ ለአማራጭ የሃይል ምንጭ ሊውል ነው Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
Imageበኢትዮጵያ ከኦርጋኒክ ምርቶችና ከሚባክን ኃይል አማራጭ የኃይል ምንጭ ለማምረት አስፈላጊ የሆነውን ጉሎ ለማልማት የመጀመሪያ ደረጃ ሥራውን ማጠናቀቁን ግሎባል ኢነርጂ አስታወቀ፡፡
 
ግሎባል ኤን አር ጂና ፓስፊክ ግሎባል ኢነርጂ ኢትዮጵያ፣ ከእፅዋት የሚገኝ ነዳጅ ለማምረት ለምግብነት የማይውሉ የቅባት እህሎችን ለማምረት የሚያስችለውን ፕሮጀክት መጨረሱን አስታውቋል፡፡ ግሎባል ኢነርጂ ለአገልግሎት የሚውለውን የጉሎ ተክል በሚያዚያ ተክሎ ከነሐሴ እስከ መስከረም መሰብሰብ እንደሚችልም ገል"ል፡፡ ከቀረበው 12"000 ቶን ዘርም እስከ 28"000 ቶን ጉሎ ምርት እንደሚጠበቅና አሁን ባለው ዋጋ አንድ ቶን ጉሎ ከ700 እስከ 1100 ዶላር እንደሚያወጣም ተመልክቷል፡፡

ባለፉት አምስት ወራት ግሎባል ኢነርጂ ኢትዮጵያ ጉሎ በወላይታና ጋሞጎፋ ለማምረት አስፈላጊ የሆነ መሬት በመውሰድ መሠረተ ልማት በመገንባት ላይ ነበር፡፡ በተጨማሪም ከ25"000 አባወራዎች 7"500 የሚሆን ሄክታር መሬት ለጉሎ ልማት ለማዋል ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ግሎባል ኢነርጂ አዳዲስ ዝርያዎችን ለማግኘትና በቀጣይ የሚኖረውን ውጤት ለማሳደግ በስምንት የምርምር ጣቢያዎች የምርምርና የልማት ፕሮግራም መጀመሩም ተመልክቷል፡፡
ኃይልን ከተረፈ ምርቶች፣ ለምግብነት ከማይውሉ የቅባት እህሎችና ከታዳሽ የኃይል ምንጮች ማምረት ከባቢ አየርን ከብክለት ለመከላከልም የተሻለ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የተገኙት ውጤቶች በተለያዩ ምክንያቶች /ከፕሮጀክቶቹ የተለዩ/ ሲሆኑ ለረዥም ጊዜ የባዮ ፊውልና የሌሎች የአማራጭ ሃይሎች ምንጮች አለመረጋገጥ፣ የአካባቢያዊ ተጽዕኖዎች፣ የሜካኒካል፣ የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስና የሰው ሀይል የሚጠቅሱ ስጋቶች ናቸው፡፡

ሆኖም አሁን ካለው ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋና ለባዮፊውል አገልግሎት የሚውሉ ምርቶች ዋጋ መጨመር አንፃር የጉሎ ዘይት ዋጋ ከሌሎች ምርቶች አነስተኛ መሆኑና በአጭር ጊዜ መድረሱ የተሻለ አማራጭ መሆኑ ተገል"ል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >