| እቃችንን ሳናወጣ ያለማስጠንቀቂያ ቤታችን... |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
በህገወጥ መንገድ የሰፈሩ ስለሆነ እርምጃችን ህጋዊ ነው በቦሌ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 16 ውስጥ መሪ በተባለ አካባቢ የሚገኙ የስድስት አባወራ መኖሪያ ቤቶች ፈረሱ፡፡ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ነዋሪዎቹ በህገወጥ መንገድ ¾cð\ eKJ’ `UÍ‹” IÒ© ’¨< c=M K]þ`}` Ò²?× ÑKì:: ’ª]‡ Ÿ›e^ G<Kƒ ¯Sƒ uLà ux¨< u?ƒ c`}¨< S•^†¨<”“ ለይዞታውም ግብር ሲከፍሉ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ በአካባቢው ከዘጠና ሦስት በላይ አባወራዎች እንደሚገኙና ቀበሌው ውሃ፣ መብራት፣ ስልክ የመሳሰሉ አገልግሎቶች እንዲያገኙ መዋጮ ሲያስከፍላቸው መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡ አስፈላጊውን የቀበሌ መዋጮና አገልግሎት ሲያበረክቱ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ..ክፍለ ከተማው ያለማስጠንቀቂያ እቃችንን ሳናወጣ ቤታችንን አፍርሶብናል.. ሲሉ አማርረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ አቶ አርከበ እቁባይ አስተዳደር በነበሩበት ወቅት በወጣው መመሪያ ቁጥር ሁለት መሠረት ህጋዊ ልንሆን ሲገባ ያለምትክ ቦታ ቤታችን መፍረሱ የዜግነት መብታችንን ይጋፋል ሲሉ ክፍለ ከተማውን ወቅሰዋል፡፡ አዜብና ጐላጐል ለተባሉ የሪል ስቴት ባለሀብቶች መሰጠቱን በመግለፅ ክፍለ ከተማው የመኖር ዋስትናችንን ነፍጐናል ሲሉ ነዋሪዎቹ አማርረዋል፡፡ በአካባቢው ከ93 በላይ አባወራዎች ከነቤተሰባቸው ቤት ሰርተው እየኖሩ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልፀው ቀስ በቀስ የሁላችንም ቤት ይፈርሳል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ክፍለ ከተማው በ20/03/2000 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ..እስከ 1994 ዓ.ም መኖሪያ ቤት ለሰሩ የሚለው መመሪያ ሲወጣ ትስተናገዳላችሁ.. በሚል ያለምትክ ቤታችንን አፍርሶብናል ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ቦታዎች ማስለቀቅ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ለታህሳስ 29/2000 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ክፍለ ከተማው በልዩ ችሎት የተያዘውን ጉዳይ ውሳኔ ሲያገኝ ቤታችንን ማፍረሱ ህገወጥ ድርጊት ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር መምሪያ ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ መሠረት ነጋሽ ነዋሪዎቹ ..በህገወጥ መንገድ የሰፈሩ ስለሆነ እርምጃችን ህጋዊ ነው.. ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ለልማት የተያዘ ቦታ ላይ የሰፈሩ በመሆኑ መነሳት እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡ አቶ መሠረት ..መመሪያ ቁጥር 1 መሠረት የነዋሪዎቹ ቤቶች በአየር ካርታ ላይ የማይታዩ በመሆኑ ፈርሰዋል.. ሲሉ የክፍለ ከተማው እርምጃ መመሪያን መሠረት ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የመሬት ልማትና አስተዳደር ተጠባባቂ ኃላፊው ..ግብር መክፈል ባለይዞታነትን አያረጋግጥም.. ሲሉ አሳውቀዋል፡፡ በዚህም መሠረት ክፍለ ከተማው ለአዜብና ጐላጐል ሪል ስቴት ግንባታ በሰጠው ሰላሳ ሺህ ካሬ ሜትር ይዞ ውስጥ የሚገኙትን ስድስት አባወራዎችን እንዲለቁ በተደጋጋሚ ማሳወቁን፤ ነዋሪዎቹ ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቆታቸውን አቶ መሠረት ገልፀዋል፡፡ አቶ መሠረት በኖርቴክ ካርታ ላይ የማይታዩ አስራ ስምንት ቤቶች መሆናቸውን ገልፀው ለጊዜው ስድስቱን ብቻ ማስነሳታቸውን ገልፀዋል፡፡ ጉዳዩ በፍርድ ቤት መያዙን አናውቅም ሲሉ አብራርተዋል፡፡ በተሾመ ንቁ |
|
| Last Updated ( Thursday, 10 January 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |