| በሕገወጥ የውጪ ምንዛሬ የተሰማሩ... |
|
|
| Wednesday, 02 April 2008 | |
|
በሕገወጥ የውጪ ምንዛሬ የተሰማሩ ንግድ ፈቃዳቸው ታገደ
በሕገወጥ ምንዛሬ ተሰማርተዋል ተብለው የተያዙ የንግድ ፈቃዳቸው መታገዱን የየክፍለ ከተሞቹ የንግድ ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤቶች አስታወቁ፡፡ ለግለሰቦቹ የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ለእግዱ ምክንያት የሆነው የንግድ የሥራ ፈቃድ ከተሰጠበት አላማ ውጭ ሲገለገሉና ተገቢ ያልሆነ ሕገወጥ የንግድ ሥራ ሲሰሩ መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በማረጋገጡ ነው፡፡ "ስለሆነም" ይላል ደንበኛው "ስለሆነም በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀጽ ሐ መሰረት ንግድ ፈቃዱም እንዲታገድ የተወሰነ መሆኑን እናስታውቃለን" የየክፍለ ከተሞቹ ደንብ ማስከበር ትዕዛዙን ተቀብለው ደብዳቤው ከደረሰ ጊዜ ጀምሮ የንግድ ሥራቸውን እንዲያቆሙ ማስጠንቀቂያ ጽፏል፡፡ በዚህ የእግድ ማዘዣ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ፣ ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ፣ ካዛንቺስ፣ ሂልተን ጀርባና መርካቶ አካባቢ በሕገወጥ ምንዛሬ ስራ ተሰማርተዋል ተብለው የተከሰሱ ድርጅቶች ይዘጋሉ፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |