Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Monday
Oct 13th
Home arrow Sections arrow ኪባኪና ተቃዋሚዎች ሊሸማገሉ ነው
ኪባኪና ተቃዋሚዎች ሊሸማገሉ ነው E-mail
Wednesday, 09 January 2008
በኬንያ፣ ምርጫውን ተከትሎ በታየው እርስ በርስ መተላለቅ አመጽ እንዲቆም በአሜሪካ ግፊት ፕሬዚዳንት ኪባኪና የተቃዋሚው መሪ ሊነጋገሩ ነው፡፡

ግጭቱን ለማብረድ ወደ ናይሮቢ የበረሩት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ ጃንዳይ ፍሬዘር ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሁለቱን ተቀናቃኞች ሲያነጋግሩ ቆይተዋል፡፡

በኬንያ በታየው ዘርን መሰረት ያደረገ አመጽ 1000 ሰዎች መገደላቸውን ተቃዋሚዎች መግለጫ ሲሰጡ፣ የኪባኪ መንግስት ግን የሟቾቹን ቁጥር ከ500 እንደማይበልጥ ይገልፃል፡፡

ከ255..000 በላይ ኬንያውያንም ተፈናቅለዋል፡፡ ግጭቱ የተደረገው በኪባኪ ደጋፊ ጎሳዎችና ለሩጅም ጊዜ በፖለቲካና በኢኮኖሚ የበላይነት በነበራቸው ኩኩዩዎች ነው፡፡ ሁለቱም ወገኖች ትኩሳታቸውን አብርደው አመጽን እንዲያስቆሙ የምትጎተጉተው አሜሪካ ለኬንያ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ትሰጣለች፡፡

ኪባኪ ለተቃዋሚዎች ስልጣን እንዲያካፍሉ የአሜሪካ ፍላጎት ሲሆን ተቃዋሚዎች ከ210 የፓርላማ መቀመጫዎች 95ቱን በማሸነፋቸው ያለ ተቃዋሚዎች ድጋፍ ኪባኪ ሊያስተዳድሩ እንደማይችሉ ታምናለች፡፡

በተጨማሪ የቀድሞ የመንግሥታት መሪዎች የነበሩት የሞዛምቢኩ ጃዋቺሞ ቺሳኖ፣ የዛምቢያው ኬኔት ካውንዳ፣ የታንዛኒያው ቢንጃሚን ሞካባ ኬንያ ገብተዋል፡፡ የጎረቤት ቤት ሲቃጠል እንደማየት ያህል ሁኔታው አስደንግጦናል ማለታቸውን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ዙማ ለፕሬዚዳንትነት ታጩ

የደቡብ አፍሪካው ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤ.ኤን.ሲ) በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጃኮብ ዙማን እጩ አድርጎ ሰየመ፡፡

ባለፈው ወር ፕሬዚዳንት ታቦ ኢንቤኪን በውድድር አሸንፈው የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት ዙማ፣ በሙስና ተጠርጥረው እንደሚከሰሱ ቢገለጽም ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለዕጩነት ሰይሟቸዋል፡፡

ዙማ በሚሊዮን በሚቆጠር የጦር መሳሪያ ግዥ፣ ገንዘብ በማዘዋወርና በማጭበርበር፤ ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ ባለፈው ሐሙስ አስገድዶ በመድፈር ክስ የቀረበባቸው የ65 ዓመቱ አዛውንት ዙማ ሁሉንም ክስ አስተባብለዋል፡፡

አሜሪካ  በኢራን ጀልባዎች ተቆጣች

የአሜሪካ ጀልባዎች በዋናው የመርከብ መመላለሻ በሚቀዝፉበት ወቅት የኢራን የጦር ጀልባ ለማስፈራራት ሞክሮ እንደነበር ፔንታገን አስታወቀ፡፡

የኢራን ጀልባ ድርጊት፣ ጀልባዎቹ እንዲፈነዱ ሊያደርግ የሚችል እንደነበር መሆኑን የጠቀሰው የአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት፣ ኢራን ማብራሪያ እንድትሰጥ ጠይቋል፡፡

ቦታው አሳሳቢና ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የሚገልፁት የመከላከያ ኃላፊው ሮበርት ጌትስስ ሁኔታው ቴህራን ውስጥ የማይታመን መንግስት መኖሩን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ኢራን በበኩሏ አጋጣሚው በመንገድ ላይ የሚያጋጥም ግንኙነት ነው ስትል ማስተባበሏን ሮይተር ዘግቧል፡፡

የቡቶን ገዳዮች ለመመርመር የእንግሊዝ ፖሊሶች ፓኪስታን ገቡ


የፓኪስታኑ ፕሬዚዳንት ሙሻረፍ የቤናዚር ቡቶን ገዳዮች አድነው ለመያዝና ቅጣታቸውን እንዲያገኙ ማንኛውንም ጥረት እንደሚያደርጉ ዝተዋል፡፡

ለምርመራው ሂደት የእንግሊዝ የፖሊስ ምርመራ ቡድንን ዕገዛ የጠይቁ ሲሆን የእንግሊዝ ፖሊሶችም ፓኪስታን ገብተዋል፡፡ የቤናዚር ቡቶ ደጋፊዎች ግን የተመድ መርማሪዎች እንዲመደቡ እየወተወቱ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

 
< Prev   Next >