Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow "የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን...
"የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን... Print E-mail
Wednesday, 02 April 2008
"የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የካሳ አከፋፈል ለሙስና የተጋለጠ ነው"
(የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን)

የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የካሳ አከፋፈል ለሙስና የተጋለጠ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በባለሥልጣኑ ላይ ባደረገው የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ ጥናት ሪፖርት ላይ የባለሥልጣኑ የካሳ አከፋፈል ስርዓት ለሙስና ክፍት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኮሚሽኑ ጥናት መሠረት ባለሥልጣኑ ለመንገድ ሥራ ተነሺ ለሆኑ አካላት የሚደረገው የካሳ አከፋፈል ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ ነው፡፡ ለዚህም ለተነሺዎች የሚሰራው የካሳ አከፋፈል የንብረት ግምት በንብረት ገማች ኮሚቴ ሳይሆን በባለሥልጣኑ ሰራተኞች መሆኑ ለሙስና በር መክፈቱን አሳውቋል፡፡

በሪፖርቱ መሠረት የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ከባለይዞታዎች ጋር በመመሳጠር የባለይዞታዎችን ንብረት ካሬ ሜትር ልዩነት የመፍጠር፣ የንብረት ቁጥር የመጨመር፣ መጠኑ ትንሽ የሆነውን ንብረት ከፍ እንዲል የማድረግ፣ የተገነቡ የግንባታ ዓይነት በመለወጥ እንዲሁም ምንም ዓይነት ንብረት የሌለው ግለሰብ በቅፅ ላይ ተሞልቶ እንዲቀርብ የማድረግ ሁኔታ እንዳለ አስታውቋል፡፡

የባለሥልጣኑ የግምት አከፋፈል ስርአት ማከናወኛ መረጃ አሰባሰብ ስርዓቱም ለብልሹ አሰራር ክፍት መሆኑን አስታውቋል፡፡ ለዚህም የቤት ግንባታ ማቴሪያልና የቤት ሁኔታ የመረጃ መግለጫ ቅፆች የባለይዞታዎችን ንብረት በዝርዝር ለመመዝገብ የማይቻልበት፣ ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርት ውጤቶችን የማያካትት፣ ግልፅነት የጐደለውና ሁሉንም ንብረቶችን ለመዘርዘርና ለመግለፅ የማያስችሉ መሆናቸውን አብራርቷል፡፡ በተጨማሪም የመረጃ ቅፆቹ የተሟላ መረጃ ስለማይሰጡ የግምት ተግባሩ ለግለሰቦች የግል ውሳኔ የተጋለጠ መሆኑን ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

ሪፖርቱ የባለሥልጣኑ መረጃ አሰባሰብ የነዋሪዎችን የንብረት ዋጋ በየወቅቱ ካለው የገበያ ዋጋ ጋር በመመሪያ መሠረት እየተነፃፀረ የማይከለስ በመሆኑ፣ በየክፍለ ከተሞች መሬት ልማትና አስተዳደር የተመደቡ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ከክፍለ ከተማው ቁጥጥር ውጪ በከፊል የሚነሱ ንብረቶችን ግምት የሚያዘጋጁት ያለተመን በመሆኑ የአሰራር ስርዓቱ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው፡፡

በሌላ በኩል የክፍለ ከተሞች መሬት ልማትና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሥራቸውን የሚያከናውኑት ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት የሚለቀቅበትና ካሳ የሚከፈልበት አዋጅ ቁጥር 455/97 እና አዋጁን ተከትሎ ከወጣው ደንብ ቁጥር 135/99 ውጪ ቀደም ብለው በወጡ ባልተሟላና ባልፀደቁ የአፈፃፀም መመሪያዎችና ሰርኩላሮች መሆኑን ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

በዚህም በማስፋፊያ አካባቢም ሆነ በነባር ይዞታዎች ለመንገድ ሥራ በአዋጁ መሠረት ካሳ የሚከፈልበትን ንብረትና የተነሺዎችን ንብረት የአገማመት ስልት፣ የካሳ አከፋፈል ስርዓት፣ የመረጃ አሰባሰብ ሂደት፣ በመመሪያና በቅፅ ያልተካተቱና ግልፅ ያልሆኑ፤ በሥራ ሂደት የታዩ ችግሮችን በዝርዝር የማይፈቱ በመሆናቸው ለሙስናና ለብልሹ አሠራር የተጋለጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለዚሁ የአሰራር ብልሹ ሂደት አማራጭ የአሰራር መስመር በሪፖርቱ አካትቷል፡፡

በተሾመ ንቁ
 
< Prev   Next >