Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የዝምባብዌ ተቃዋሚዎች እንደሚያሸንፉ ገለፁ
የዝምባብዌ ተቃዋሚዎች እንደሚያሸንፉ ገለፁ Print E-mail
Wednesday, 02 April 2008
በዝምባብዌ ያለፈው ቅዳሜ የተደረገው የምርጫ ስነ ስርዓት ውጤቱ ባይገለፅም ተቃዋሚዎች እንደሚያሸንፉ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የመገናኛ ብዙሀን ምርጫው ሀገሪቱ ነፃነቷን ከተቀናጀች ወዲህ ባሉት ሀያ ስምንት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ፉክክር የታየበት የምርጫ ውድድር መሆኑን ዘግበዋል፡፡ የምርጫው ቅስቀሳ ሰላማዊ እንደነበረ ተጠቁሟል፡፡ የመራጮች የድምፅ ካርድ ቆጠራ ያለፈው እሁድ ተጀምሯል፡፡ ተቃዋሚዎች በየፊናቸው ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ገልፀዋል፡፡ ኘሬዚደንት ሙጋቤ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱ ከመገለፁ በፊት አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

በአንጐላ ሀያ አራት ሰዎች ሞቱ

በአንጐላ ርዕሰ ከተማ ሉዋንዳ በሚገኘው የሀገሪቱ የፖሊስ ኃይል ዋና ጽህፈት ቤት ህንፃ ተደርምሶ ሀያ አራት ሰዎች መሞታቸውን የአሶሲየትድ ኘሬስ ዘገባ አመለከተ፡፡

በዘገባው መሠረት ያለፈው ቅዳሜ ህንፃው ሲደረመስ በውስጡ ከአንድ መቶ ሰማንያ የማያንሱ ሰዎች እንደነበሩ ታውቋል፡፡ ከህንፃው ፍርስራሽ ውስጥ አንድ መቶ አርባ አምስት ሰዎች በነብስ አድን ሰራተኞች መውጣታቸው ሲገለፅ የህይወት አድን ስራው መቀጠሉን ዘገባው አስታውቋል፡፡ የአደጋ ሰራተኞች አስተባባሪ ኡጉኒዬ ሊብሪደ “የህይወት አድን ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሊል ሞንቲሮ “ህንፃው ያረጀ በመሆኑ እንጂ በአሸባሪዎች አልፈረሰም” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

በባግዳድ የታወጀው የሰዓት እላፊ ተነሳ

የባግዳድ ባለሥልጣናት ያወጁትን የሰዓት እላፊ አዋጅ እንደተነሳ ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ከስፍራው ዘገበ፡፡

የሰዓት እላፊ አዋጁ ያለፈው ሰኞ ተነስቷል፡፡ ባለሥልጣናቱ ያለፈው ሳምንት በከተማዋ በተካሄደው ከባድ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጐዱ በማሰብ የሰዓት እላፊ አዋጅ ማወጅ እንዳስፈለገ አብራርተዋል፡፡ በባግዳድ በፀጥታ ኃይሎችና በአክራሪ የሺአ ሙስሊሞች መካከል የተካሄደው ጦርነት ለጊዜው ማቆሙን ዘገባው አመልክቷል፡፡ በቅርቡ በባዝራ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች በተቀሰቀሰ ውጊያ ከሁለት መቶ አርባ በላይ ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡ የሰዓት እላፊ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎ በባግዳድ መጠነኛ ንግድ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተዘግቧል፡፡

ራይስ የእስራኤልና የፍልስጤም ባለሥልጣናትን አናገሩ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንደሊዛ ራይዝ በመካከለኛው ምስራቅ የጀመሩት ዲኘሎማሲያዊ ጉብኝት ማጠቃለያ ላይ የእስራኤልና የፍልስጤም መሪዎችን ማነጋገራቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

ኮንደሊዛ ራይዝ ያለፈው እሁድ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሁድ አልመርትንና የፍልስጤማውያኑን መሪ መሀመድ ኦባሳን በተናጠል ማወያየታቸው ታውቋል፡፡ ኮንደሊዛ ራይዝ በአሜሪካ አደራዳሪነት የአናፖሊስ የተካሄደውን የሰላም ውይይት እንደገና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ ራይስ እስራኤል በጋዛ ከዘጋቻቸው መተላለፊያዎች ሀምሳ ያህሉን እንዲከፈት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
 
< Prev   Next >