Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow 650 ኩንታል ዱቄት...
650 ኩንታል ዱቄት... Print E-mail
Wednesday, 02 April 2008
650 ኩንታል ዱቄት አከማችተው የተገኙ ግለሰቦች ተቀጡ

በደሴ ከተማ የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው 650 ኩንታል ዱቄት አከማችተው የተገኙ ሁለት ተከሳሾች እስራትና የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባቸው መሆኑን የከተማው ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

ተከሳሾቹ ቅጣቱ የተወሰነባቸው በሕገወጥ መንገድ ለመክበር ዱቄቱን መደበቃቸው በሕዝብ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል ስለተደረሰባቸው መሆኑንና አንዱ ተከሳሽ 2ሺ ሲቀጣ፣ ሌላኛው ተከሳሽ በሦስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡

የ700 ታዳጊዎች ጋብቻ ተሰረዘ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ያለዕድሜያቸው ሊዳሩ የነበሩ 700 ታዳጊዎች ጋብቻ መሠረዙን የዞኑ ፍትህ መምሪያ ገለፀ፡፡

የታዳጊዎቹ ጋብቻ ሊሰረዝ የቻለው መምህራን፣ ተማሪዎችና ሕብረተሰቡ ባደረጉት ትብብር ሲሆን እገዳውን ተላልፈው የተገኙ በጣርማበር ወረዳ ክስ ተመስርቶባቸው እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ እስራት መቀጣታቸው ታውቋል፡፡

የሙስና ወንጀል በፈፀሙ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስና ወንጀል በፈፀሙ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

ግንቦት 2 ቀን 1998 ዓ.ም በቦሌ ኤርፖርት በጥበቃ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ ሦስት የፌዴራል ፖሊስ አባላት የተሰጣቸውን ፖሊሳዊ ኃላፈነት ወደ ጎን በመተው ከሳውዲ አረቢያ መጥተው በኤርፖርቱ ግቢ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ግለሰብ በማስፈራራት ከ464 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይና የተለያዩ ንብረቶችን ዘርፈው ዘርፈዋል በሚል በቀረበባቸው ክስ ሰሞኑን ከስምንት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ እስራትና ከሁለት ሺህ እስከ አምስት ሺህ ብር በሚደርስ ገንዘብ እንዲቀጡ እንደተወሰነባቸው ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡

ተመራማሪዎች ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ክትባት ማግኘት የሚያስችል ሙከራ እያደረጉ ነው

ተመራማሪዎች ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ክትባት ማግኘት የሚያስችል ሙከራ እያደረጉ መሆናቸውን በማስታወቂያ ሚኒስቴር የፕሬስ ሥራዎች በሚል በየአሥራ አምስት ቀኑ የሚታተመው ሜዲካል ዎርልድ መፅሔት አስታወቀ፡፡

መፅሔቱ አካዳሚያ ሲንካ ኤንድ ዘ ዩ ኤስ ስክራብስ ሪሰርች ኢንስቲትዩት የተሰኘ ፕሮጀክትን ጠቅሶ እንደዘገበው ምርምሩ በቤተ ሙከራ ደረጃ የመጀመሪያ ተቀባይነት ቢያገኝም በሰው ልጆች ላይ ሙከራ ከመደረጉ በፊት ቀጣይ ምርምር በስፋት እንደሚደረግበት ይህ የምርምር ፕሮጀክት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በመከላከልና በማከም በኩል አዲስ ምዕራፍ ነው ብሏል፡፡

የሥርዓተ ፆታ ሥልጠና በሴቶችና ወንዶች መካከል ያለውን ልዩነት ሚዛናዊ ለማድረግ ይረዳል

በሥርዓተ ፆታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለፖሊስ አመራር አካላት መሰጠቱ ፍትሀዊነትን በማስፈን በሴቶችና ወንዶች መካከል ያለውን ልዩነት ሚዛናዊ ለማድረግ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ገለፀ፡፡

ስልጠናው የፖሊስ አካላት ተመርቀው ወደ ህብረተሰቡ በሚገቡበት ወቅት በሴቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን፣ የሚፈጠሩ ተፅዕኖዎችን ማህበራዊ ልዩነቶችንና መድሎዎችን ለማስቀረት የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡ የፖሊስ አመራር አካላት በሥርዓተ ፆታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ጠቃሚ መሆኑ ተገል..ል፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የሀይል ጥቃቶችንና ወንጀሎችን ለመከላከል የፖሊስ አመራር አካላትን በሥርዓተ ፆታ ላይ ማሰልጠን ሴቶች እኩል የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል፡፡

ዩኒቨርስቲው በሥርዓተ ጾታና በፆታ ላይ የተለያዩ ስልጠናዎችን መውሰዳቸውን የገለፁት ሰልጣኞቹ በኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አማካኝነት የተሰጣቸው ስልጠና ይበልጥ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅም እንደሚሆናቸው ተናግረዋል፡፡
 
< Prev   Next >