| የመጀመሪያው ቅጅ ድምጽ ተደመጠ |
|
|
| Wednesday, 02 April 2008 | |
|
ከ150 ዓመታት በፊት የአንዲት ፈረንሳዊት ድምፃዊት ሙዚቃ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀርጾ የነበረው የ10 ሰከንድ ክሊፕ ዳግም መደመጥ መቻሉን ቢቢሲ አስታወቀ፡፡
በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያው የተቀረፀ የሰው ድምጽ በመባል እስከ ዛሬ የሚታወቀው እ.ኤ.አ "AU clair de la Lune" በ1860 የሚለው ሙዚቃ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ በ1877 የአለማችን የመጀመሪያው የተቀረፀ ድምጽ ተደርጎ ይታሰብ ነበር፡፡ በቅርቡ የተገኘውና ፓኖት ግራፍ በሚል መሳሪያ የተቀረፀው እድሜ ጠገቡን ክሊፕ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች እያንዳንዱን መስመር ለማንበብ በሚያስችል ጥበብ “የአለማችን የመጀመሪያ የተቀረፀ ድምጽ" ሙዚቃ ማዳመጥ ችለዋል፡፡ ታሪካዊውን ቅጂ ያገኘው ባለሙያ ዴቪድ ጊዮቫኖኒ ለአሶሽየትድ ፕሬስ እንደገለፀው፣ “በመጀመሪያ ቅጂውን ማዳመጥ እንደቻልኩ ምትሃት ነበር የሆነብኝ” ብሏል፡፡ በጣም አጭር የሆነው የሙዚቃ ቅጂ የተቀዳው እ.ኤ.አ ኤፕሪል 9, 1800 ፓኖትግራፍ በተባለ መሳሪያ ሲሆን የቀረፀውም የፐርሺያ የሙዚቃ መሳሪያ ፈጣሪ በሆነው ኤድዋርድ ነበር፡፡ የሙዚቃ መሳሪያው ድምፁን የሚያነበው በተቃጠለ ናፍጣ ጥላሸት አማካኝት የተዳፈነ የድምጽ ሞገድ የሚወክል ጽሁፍ ነው፡፡ ሚስተር ጊዮቫኖን ለሮይተርስ እንደገለፁት ቶማስ ኤዲሰን ድምጽን የቀረጸና የቀረጸውንም መልሶ ማዳመጥ የቻለ የመጀመሪያው ሰው ነው፡፡ ግብረሰዶማውያን አሁንም ለኤች.አይ.ቪ ቅርብ ናቸው በኤች.አይ.ቪ የሚጠቁ ግብረሰዶማውያን ወንዶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ መረጃ የተገኘው እንግሊዛውያን ግብረሰዶማውያን ሲሆን እ.ኤ.አ በ2007 አዲስ የተያዙ ግብረሰዶማውያን ቁጥር ስድስት ሺህ 840 ደርሷል፡፡ የኤች.ፒ.ኤ ኤች.አይ.ቪ አገልግሎት ኃላፊ ዶ/ር ቫሊር ደልፐች እንዳሉት፣ “እንግሊዝ ውስጥ ግብረሰዶማውያን አሁንም በኤች.አይ.ቪ የመያዝ እድላቸው እጅግ ሰፊ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም ግብረሰዶማውያኑ ጥንቃቄ የተሞላበት የወሲብ ሕይወት እንዲኖራቸው ማስገደድ አለብን፡፡ ነባርም ሆነ አዲስ ጓደኛ ሲይዙ ኮንዶም መጠቀም አለባቸው” ብለዋል፡፡ ዶልፊኖች የዛፍ ቅርንጫፎችን በመጠቀም ተቃራኒ ፆታን ያማልላሉ በደቡብ አሜሪካ ወንዞች የሚገኙ ዶልፊኖች የዛፍ ቅርንጫፎችንና የተለያዩ ተክሎችን በጅራታቸው በማወዛወዝ ተቃራኒ ፆታን ለማማለል እንደሚጠቀሙበት አጥኚዎች ገልፀዋል፡፡ በጆርናል ባዮሎጂ የተፃፈው የአጥኚዎች አስተያየት እንደሚያስረዳው እንዲህ አይነቱ ተቃራኒ ፆታን የመማረክ ባህሪ በሌሎች የውሃ ውስጥ አጥቢ እንስሳት ላይ ታይቶ አይታወቅም፡፡ የአጥኚዎቹ ጽሁፍ እንደሚያስረዳው፣ ወንድ ዶልፊኖች የፆታ ግንኙነት መፈጸም ሲፈልጉ ወደ ውሃው ውስጥ በመስጠም በጅራታቸው የዛፍ ቅርንጫፍ በኃይል ያወዛውዛሉ፣ አለቶችን በጅራታቸው ይመታሉ፡፡ ይህ እንቅስቃሴያቸው በውሃው ላይ የሚፈጥረውን ማዕበል የተመለከቱ እንስት ዶልፊኖች ይማረካሉ፡፡ ወንድ ዶልፊኖች የፆታ ግንኙነት ሲፈልጉ ስሜታዊና ኃይለኛ እንደሚሆኑም ታውቋል፡፡ የፀረ ተባይ መድሃኒት ለጡንቻ በሽታ ያጋልጣል የፀረ ተባይ መድሃኒቶች ከነርቭ ሲስተም ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የጡንቻ በሽታ የማጋለጥ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ባለሙያዎች አሳሰቡ፡፡ ቢኤም ሲ በተባለ በነርቭ ላይ የሚያተኩር ጆርናል የአሜሪካ ሳይንቲስቶችን ጠቅሶ እንደገለፀው መድሃኒቱ ከነርቭ በሽታ ጋር ያለው ቁርኝት የጠበቀ ነው፡፡ ሳይንቲስቶቹ በ600 ሰዎች ላይ ባደረጉት ጥናት ለፀረ ተባይ መድሃኒቶች ቅርበት ያላቸው ሰዎች ከሌላቸው በ1.6 እጥፍ የመያዝ እድል አላቸው፡፡ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረ እንደሚመጣና በእንቅስቃሴና ንግግርን ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ በዘር ባህርይ የሚወሰን መሆኑን ተጠቁሟል፡፡ ብዙ የጅን ችግር ያለባቸው ሰዎች የተለዩ ቢሆንም እስከ አሁን በእንግሊዝ ከ120,000 በላይ ሰዎች የበሽታው ተጎጂ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ በአሜሪካ የተቋቋመው የጥናት ቡድን ከደክ ሚያሚ ዩኒቨርሲቲና ዩዳል ፓርኪንሰን በሽታ ምርመራ ማዕከል ፀረ ተባይ መድሃኒት በመጠቀሙ 319 ሕመምተኞች ላይ ምርመራ በማድረግ 200 የሚሆኑት ብቻ ከበሽታው ነፃ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ለ200 ቀናት በተከታታይ ለሚጠቀሙ ሰዎች አደጋው በእጥፍ እንደሚጨምርም ተገልጿል፡፡ የተመራማሪዎቹ ቡድን ኃላፊ ዳና ሀንኮክ እንዳሉትም ከነርቭ ጋር የተያያዘ የጡንቻ በሽታ ትክክለኛ ምክንያት ባይታወቅም ከዘርና ከአካባቢያዊ ሁኔታዎች ውህደት የመምጣት እድሉ ሰፊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፕላስቲክ ውጤቶች ብክለት አሳሳቢ ሆኗል የፕላስቲክ ውጤቶች በባህር አካባቢ መጣላቸው ለወደፊቱ በተለይ በምግብ ላይ የሚያስከትለው ብክለት አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ የፓስፊክ ደሴቶች አካባቢ ሁኔታው እየተባባሰ መሆኑንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቢሊዮን የሚቆጠሩ የፕላስቲክ ቁርጥራጮች እንደ ዲዲቲ ያሉ በባህር ከሚደፉ መርዛማ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ብክለትን እየፈጠሩ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራው በአይን የሚታዩ የፕላስቲክ ውጤቶች እያስከተሉ ያለው ችግር ሲሆን አጥኚዎች ግን በባህር ውስጥ ለውስጥ እየታየ ያለው ድብቅ የመመረዝ ችግር አሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በውሃ ውስጥ የፕላስቲክ ውጤቶች መጠራቀምና መርዛማ ኬሚካሎች በዛው አካባቢ መፍሰስ በባህር ለሚኖሩ እንስሳት ህይወት አስጊ እየሆነ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ተመራማሪዎች በውሃ ውስጥ በፕላስቲክ ውጤቶች አማካኝነት ሊከሰት የሚችለው የመመረዝ አደጋ የሚታሰበውንና የሚፈራውን ያህል እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ የመርሳት በሽታን ህክምና ያባብሰዋል ለመርሳት በሽታ ማስታገሻነት የሚሰጠው የተለመደ መድሃኒት የበሽተኞችን የመርሳት ሁኔታ እንደሚያባብሰው በጥናት ተረጋገጠ፡፡ ጥናቱ ያተኮረው ቁጥራቸው 165 በሚደርሱና የበሽታው ተጠቂ በሆኑ ሰዎች ላይ ሲሆን 60 በመቶ የሚሆኑት በተለይ በሽታው የሚያስከትልባቸውን እንደ ቁጡነት የመሳሰሉ የባህሪ ለውጦች ለማስቀረት መድሃኒት ይወስዳሉ፡፡ ብዙዎቹም ቤታቸው ውስጥ ሆነው በመታከም ከ6 ወር በላይ ለመርሳት በሽታ የሚሸጥ መድሃኒትን ወስደዋል፡፡ በባህሪ ለውጦች ላይ የሚያስከትልባቸውን ችግር ለማስወገድ የስድስት ወር ህክምና በቂ ቢሆንም ግን መድሃቱን መውሰድ ይቀጥላሉ፡፡ በመሆኑም መድሃኒቱን በተከታታይ መውሰድ በሸታውን የሚያባብስ ሲሆን የመሞት እድልንም ሊጨምር እንደሚችል ሳይንቲስቶች አስታውቀዋል፡፡ ዋና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ክሊቭ ባላርድ እንዳሉት “የመርሳት በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከስድስት ወር በላይ ለበሽታው የሚሰጡ መድሃኒቶችን ከስድስት ወር በላይ መውሰዳቸው ጥቅም የለውም፡፡ በተለይ ብዙ የባህሪ ለውጦች ለሚታይባቸው በሽተኞች ባህሪ ለመመለስ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |