| የወጣቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ |
|
|
| Wednesday, 02 April 2008 | |
![]() ሠለሞን ገብሩ ![]() ቤዛዊት ብርሃኔ በተለይም ወጣቱ የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ፖሊሲና ስትራቴጂ በመረዳት ያሉበትን የተለያዩ ችግሮች ከመፍታት አንፃር የትኛውን ፓርቲ መምረጥ እንዳለበት በማመላከት የውይይት መድረኩ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክቷል፡፡ “ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ፖሊሲና ስትራቴጂ ወጣቱ ያሉበትን የተለያዩ ችግሮች በተለይም ሥራ አጥነትን ከመፍታት አንፃር ሊገመግሙ ይገባል፡፡ ነገ በአስተዳደር ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ፓርቲዎች የወጣቱን ችግር የሚፈቱ እንዲሆኑና የወጣቶች ችግርም እንዲቀረፍ ከተፈለገ ወጣቶች ዛሬ ባገኙት መድረክ ተሳታፊ መሆን አለባቸው” ብሏል፡፡ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለውይይት እንደጠሩ፣ ነገር ግን በውይይት መድረኩ ሁለት ብቻ (ኢህአዴግና ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ) ብቻ መገኘታቸውን የሚናገረው ወጣት ሠለሞን ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጥሪ ያስተላለፈው የኗሪዎች ፎረም እንደነበርና የቀሩት ፓርቲዎችም ባለመገኘታቸው ምንም አይነት ምክንያት ስላልሰጡ ዝምታቸውን እንዳለመፈለግ እንደተመለከቱት ጠቁሟል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በግላቸው ከሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ባሻገር እንደዚህ ዓይነት የውይይት መድረኮች ላይ በመገኘት ፖሊሲዎቻቸውን ቢያስተዋውቁ መራጩ ህዝብ የተለያዩ ፓርቲዎች ያሏቸውን የተለያየ የፖሊሲ አማራጭ እንዲገነዘብ እንደሚያደርግ ያምናል፡፡ ወጣቶች ያሉባቸውን ችግሮች ሊፈታ ከሚችል ከማንኛውም ፓርቲ ጋር ተቀራርቦ የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት ስላላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ወጣቱን ቀርበው ማነጋገርና የወጣቱን ሃሳብ መቀበል እንደሚገባቸው ይናገራል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን፣ በአገሪቱ የልማት ጉዞ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊኖረው የሚችለውን ወጣቱን የኅብረተሰብ ክፍል ሳይዙ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እንቅስቃሴ ውጤታማ አይሆንም የሚል አቋም አለው ወጣት ሰለሞን፡፡ የውይይት መድረኩን ለማዘጋጀት ብዙ ቢደክሙም በክፍለ ከተማ ትብብርና በአንዳንድ ግለሰቦች መልካም ፍቃድ መሳካቱን፣ ነገር ግን የተጠሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ አለመገኘት ቅሬታ እንደፈጠረባቸው አልደበቀም፡፡ “ወጣቱን በሚመለከት ያመኑበትን ነገር በአጀንዳቸው ይዘዋል፡፡ በፖሊሲያቸው ቀርፀዋል፡፡ ቢሆንም የሁሉም ነገር ማሰሪያ መሆን የሚችለው ወጣቱን በማነጋገርና ሃሳቡን በመቀበል በድጋሚ መለስ ብለው ፖሊሲና ስትራቴጂያቸውን መመልከት ነው” በዚያው የፖለቲካ ፖርቲዎች የውይይት መድረክ ላይ ንቁ ተሳታፊ ሆና ያገኘናት ወጣት ቤዛዊት ብርሃኔ ናት፡፡ እሷም በቦሌ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ፎረም ቤቶች ልማት ሰብሳቢ ነች፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተመራጮች እንደ ህዝብ ተወካይነታቸው ያላቸውን ሃሳብና የያዙትን አቋም በፖሊሲያቸው ለኅብረተሰቡ የማስተዋወቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው የምትናገረው ቤዛዊት እነሱ ባቀረቧቸው ሃሳቦች ላይ ኅብረተሰቡ ተወያይቶ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ በፖሊሲዎቻቸው ሊያካትቷቸው ይገባል የሚሏቸውን ተጨማሪ ነገሮች እንደሚያቀርብ ጠቁማለች፡፡ በዚህ ዓይነት የፖለቲካ ፓርቲዎችና የኗሪ ኅብረተሰብ ውይይት ወጣቶች በንቃት ተሳታፊ በመሆን ያሉባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ መታገል ይኖርባቸዋል ብላለች፡፡ የወጣቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ በማስመልከት “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት ለወጣቶች ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን የሚያሳዩ በርካታ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ወጣቶች በመደራጀት ያለባቸውን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመፍታት የሚያስችል ሁኔታን ከማመቻቸት ጀምሮ አገራዊ በሆኑ ፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ሁነቶች ላይ መሳተፍ የሚችሉበትን እድል መፍጠርና አቅማቸውን ማጎልበት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው” ብላለች፡፡ የወጣቱ ችግር መደራረብ የወጣቱን ችግር ለመፍታት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ወጣቱን ተሳታፊ አለማድረግ ቀደም ሲል የተወሰዱ እርምጃዎች ደካማ ጎን እንደሆነ ታምናለች፡፡ ዛሬ ላይ ባለው የተመቻቸ ሁኔታ ደግሞ ወጣቱ ያለምንም ማመንታት ችግሬን ሊፈቱልኝ ይችላሉ ብሎ ከሚያምንባቸው አካላት ጋር በጋራ መስራት እንደሚኖርበት አሳስባለች፡፡ “ቀደም ሲል ዳር ላይ ቆመን ነበር ያሉብንን ችግሮች ስንገልጽ የነበረው፡፡ ዛሬ ግን እኛም የመፍትሄ አካል መሆን እንድንችል እድል ተሰጥቶናል፡፡ ይህን አጋጣሚ መጠቀም ምርጫችን ሊሆን ይገባል” እንደ ቤዛዊት አባል በተለይም ወጣት ሴቶች በወጣቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ግንባር ቀደም መሆን ይኖርባቸዋል፡ ለዚህ በምክንያትነት የምታነሳው ሴቶች ሴት በመሆናቸው ብቻ ያለባቸውን ማኅበራዊ ጫና ለመቋቋምና ለማንሳት በማንኛውም ተሳትፎ ቀዳሚ መሆን የግድ እንደሚላቸው ነው፡፡ በምሕረት አስቻለው |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |