| ቀጣዩ ትግል በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ብቻ ነው |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
![]() Ato Temesgen በስልት ምክንያት የተለያዩ የቅንጅት ቤተሰቦች አንድ መድረክ ፈጥረናል ቀጣዩ ትግል በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ብቻ ነው፣ አምባገነናዊ አስተሳሰብና የይሉንታ ፖለቲካ በቅንጅት ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም ሲሉ አቶ ተመስገን ዘውዴ ለሪፖርተር ገለፁ፡፡ ውህደቱ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል፡፡ አቶ ተመስገን ይህንን የገለፁት በእሳቸው የሚመራው የፓርላማ ቅንጅትና በወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው ቅንጅት ለመዋሀድ መወሰኑን ተከትሎ በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ እርሳቸው የሚመሩት ቅንጅት ወ/ሪት ብርቱካን ከሚመሩት ቅንጅት ጋር ባደረገው ውህደት የሚከተለው የትግል ስልት ምን ዓይነት እንደሆነ ከሪፖርተር ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አቶ ተመስገን ..አብዛኛው የቅንጅት ቤተሰብ በሰላማዊ የትግል ስልት እንደሚያምንና ይህ የትግል ስልትም አሁን በተጀመረው የውህደት ድርድር ተጠናክሮ ይቀጥላል.. ብለዋል፡፡ በዚህም ፓርላማ የገባነው ወገኖችና ፓርላማ ሳይገቡ የቀሩት ሲዋሀዱ የአስተሳሰብ ለውጥ ሙሉ በሙሉ እንደማይኖር ይፋ አድርገዋል፡፡ በቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ውስጥ የስትራቴጂ ልዩነት እንጂ የዓላማ ልዩነት እንደሌለ የጠቆሙት አቶ ተመስገን በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ ነገር ግን በስልት ምክንያት የተለያዩ የቅንጅት ቤተሰቦች አንድ መድረክ ፈጥረውና ተጠናክረው የሚወጡበት የመጀመሪያው ምዕራፍ በውህደት ድርድሩ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ አቶ ተመስገን እንዳሉት ሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልት የሚደግፉ ስድስት ሰዎች ወ/ሪት ብርቱካን ከሚመሩት ቅንጅት፣ አቶ ተመስገን ከሚመሩት ቅንጅት ደግሞ ስድስት ሰዎች ተመርጠው ጉዳዩን በዝርዝር እየተወያዩበት ይገኛሉ፡፡ የስልት ልዩነቶች በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት እየተፈቱ ፓርቲው ተጠናክሮ የሚሄድበት መንገድ እየተቀየሰ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተመስገን የውህደቱ መሠረት ሊሆን የሚገባው ሰላማዊና ህጋዊ ትግልም ወደ ፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ እያዘጋጀው ያለው ሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልትም በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ እንደ አቶ ተመስገን ገለፃ ቅንጅት እንደ ፓርቲ ቀደም ሲል እንደሚታመነው በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንዲታገል ከሚደግፉ አካላት ጋርም አብሮ ለመሥራት በሩ አልተዘጋም፡፡ አማራጭ ፖለቲካ፣ አማራጭ የፖለቲካ ፕሮግራምና እያደገ የሚሄድ የዴሞክራሲ ትግል በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግ አቶ ተመስገን ገልፀዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ውህደት ፈርሷል፡፡ አሁንም ተመሳሳይ ችግር ይፈጠራል ብለው አያምኑም በሚል ለተጠየቁት ..አሁን እርግጠኞች ነን፡፡ ውህደታችን የተጠናከረ ቅንጅትን ይፈጥራል፡፡.. በማለት አቶ ተመስገን መልስ ሰጥተዋል፡፡ በአሰግድ ተፈራ |
|
| Last Updated ( Thursday, 10 January 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |