Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow የሃይማኖት ልዩነት ያልገደበው የሚሌኒየም በዓል
የሃይማኖት ልዩነት ያልገደበው የሚሌኒየም በዓል Print E-mail
Wednesday, 09 January 2008

የሃይማኖት ልዩነት ያልገደበው አንድነታችን በአዲሱ ሚሌኒየም እንደሚቀጥል የማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚሌኒየም የመጀመሪያ የሆነው የገናን በዓል፤ አገሪቱ የተለያዩ እምነት ተከታዮች፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በፍቅር፣ በመከባባርና በመቻቻል የሚኖሩባት ቅድስት ምድር መሆኗን፣ በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተውን አንድነት መሠረት በማድረግ ብሩህ የዕድገት ጎዳና መቀየስና ዘመኑ የኢትዮጵያ ህዳሴ የሚረጋገጥበት ለማድረግ በጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል፡፡

/አዲስ ዘመን፣ ታኅሳስ 29 ቀን 2000 ዓ.ም/

ከ155 ሺ በላይ ኩንታል የበርበሬ ምርት ተገኘ

በስልጤ ዞን በዘንድሮ የመኸር ወቅት በዘር ከተሸፈነው 12ሺ 929 ሔክታር የበርበሬ ማሳ ከ155ሺ ኩንታል በላይ የበርበሬ ምርት መገኘቱን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

የዞኑ አርሶ አደሮች በልምድ የሚያካሂዱትን የበርበሬ ልማት ከ40ሺ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን፣ በሔክታር ስምንት ኩንታል ብቻ ይገኝ የነበረው የበርበሬ ምርት ወደ 12 ኩንታል ማደጉን፣ አዲሱ ምርት ወደ ገበያ መቅረብ በመጀመሩ በአካባቢው በኪሎ 60 ብር ይሸጥ የነበረው ወደ 32 ብር ዝቅ ማለቱን ገልጿል፡፡

/ዋኢማ/

መጤና ተዛማች ዕጽዋትን ለማስወገድ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ተመደበ

በአርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ አካባቢ የተፈጥሮ መመናመን እያስከተለ የሚገኘውን መጤና ተዛማች ዕጽዋት ለማስወገድ ለተቀረፀው የፕሮጀከት ማስኬጃ ሁለት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መመደቡን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡

በአርብቶ አደሩ በተለይ በአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጥሮ መመናመን እየፈጠረ ያለውን ወያኔ በመባል የሚታወቀው መጤ ዕጽዋት /ፕሮሶፒስ ዛፍ/ የተፈጥሮ ሀብትን፣ ዕጽዋትንና ግጦሽን በከፍተኛ ደረጃ በማጥፋት ላይ ይገኛል፡፡

በአህያ የማረስ ሙከራ ውጤታማ ሆነ

በሰሜን ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ፣ በአህያ ስለማረስ ጠቀሜታ ለማስታዋወቅ የተጀመረው የሙከራ ሥራ ውጤታማ መሆኑን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ገለፁ፡፡

ባለፈው ዓመት በሁለት ቀበሌዎች የተጀመረው በአንድና በሁለት አህዮች የማረስ ሙከራ ትውውቅ ውጤታማ በመሆኑ በአርሶ አደሮቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል፡፡

በወረዳው አህያ በብዛት ስለሚገኝ ለአንድ ጥማድ በሬ ለወር ኪራይ ያወጡት የነበረው ወጪ እንዲቀረፍላቸውና ዘንድሮ 200 አርሶ አደሮችን በሙከራው ለማሳተፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን መምሪያው ገልጿል፡፡                

/ዋኢማ/

ኢኮኖሚያቸውን እያሳደጉ ለኢንቨስትመንት አመቺ ከሆኑ አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ናት ተባለ

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያቸውን በከፍተኛ ፍጥነት እያሳደጉ ካሉና ለኢንቨስትመንት አመቺ ከሆኑ የሰሃራ በታች የአፍሪካ አገሮች መካከል አንዷ መሆኗን የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት /አይ.ኤም.ኤፍ/ አስታወቀ፡፡

አገሮቹ፣ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ አንጎላ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ካሜሩን፣ ታንዛኒያና ኮትዲቭዋር መሆናቸውን፣ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢን በተመለከተ ደቡብ አፍሪካ 664 ቢሊዮን ዶላር ቀዳሚውን ስፍራ መያዟን ኢትዮጵያ አስር ነጥብ አምስት በመቶ ዕድገት ማስመዝገቧን ገልጿል፡፡

/ኢዜአ/

 
< Prev   Next >