| የእህል ዋጋ ንረትና እጥረት... |
|
|
| Wednesday, 02 April 2008 | |
|
የእህል ዋጋ ንረትና እጥረት ዓለም አቀፍ አጀንዳ እየሆነ ነው
የምግብ እህል ሠብል እጥረትና የዋጋ መናር ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ የአለማችን ወቅታዊ ችግር እየሆነ ከመጣ ወራት አስቆጥሯል፡፡ ችግሩ በእጥረትና በዋጋ መወደድ ብቻ የተገባ ሳይሆን በርካታ በተለይም በድህነታቸው የሚታወቁ አገሮች ውስጥ አስደንጋጭ የዋጋ ግሽበት እያስከተለም ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን ይህንን የእህል ዋጋ መናርና እጥረት የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ህብረትም ወቅታዊ አጀንዳ አድርገው እየተነጋገሩበት ናቸው፡፡ ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ የአፍሪካ የገንዘብና የፋይናንስ ሚኒስትሮች ይህንን ችግር በተመለከተ ልዩ አጀንዳ ይዘው አዲስ አበባ ውስጥ እየተወያዩበት መሆኑንም በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እርዳታ ኤጀንሲ እንዳስታወቀውም ለጋሽ የሚባሉ አገሮች "ቦ"ቈቄቈሳሽቃቁቨ emergency ሮቅቅስሮቁ" ለተባለው ፕሮግራም 500 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንዲለግሱ ጠይቋል፡፡ ይህም ገንዘብ የሚውለው በነዳጅ ዋጋ መናር በምግብ እህሎች መወደድ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት ለመሸፈን ነው፡፡ ተቀማጭነቱ በጣሊያን ሮም የሆነው የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለጋሽ መንግሥታት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ገንዘቡን እንዲረዱ ጠይቆ ይህም እርዳታ እስከ ግንቦት ድረስ ካልደረሠ ከፍተኛ የሆነ ችግር እንደሚከሰት ጠቁሟል፡፡ የተከሰተው የምግብ እህሎች ዋጋ መናር በደሃ አገሮች ያልተጠበቀ ረሃብ እንዲከሰትባቸው ሊያደርግ እንደሚችል ይኸው የአለም ምግብ ፕሮግራም ሪፖርት ያመለክታል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በአሁኑ ወቅት የአለም ምግብ ፕሮግራም የሚያቀርበውም እርዳታ እየቀነሰ መምጣቱና በየሳምንቱም ክፍተቱ እየሰፋ መጥቷል፡፡ 70 ሚሊዮን ህዝብም ለዚህ ችግር የተጋለጠ በመሆኑ ከግንቦት ወር በፊት የሚያስፈልገው እህል ካልተገዛ ችግር ይፈጠራል ብሏል፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ በመላው አለም ለመሠረታዊ የምግበ አቅርቦት የሚውል የእህል ሰብሎች ዋጋ በሚያስገርም ሁኔታ እያደገ መምጣትን ተከትሎ በታዳጊ አገሮች የዋጋ ግሽበትና በተለይም ቤተሰቦች ለኑሮ የሚያውሉት በጀት ቀውስ እንደገጠመው የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል፡፡ የቪኦኤው ዘጋቢ ማይክሮ በውማን ከዋሽንግተን ባስተላለፈው በዚሁ ሪፖርቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ንረት ያሳየው የምግብ ሠብል ዋጋ መንስኤው የተለያዩ ምክንያቶች እንደሆነና ይህንን የምግብ ሠብል የዋጋ እድገት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቀነስ አስቸጋሪ እንደሆነም ይጠቁማል፡፡ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የፊሊፒንስ ባለሰልጣኖች በሩዝ የዋጋ መናር ምክንያት ችግር ውስጥ መግባታቸው ተገል"ል፡፡ የኢንዶኔዥያ ባለስልጣኖች ደግሞ መሠረታዊ የምግብ ዋጋ ከመጠን በላይ እየጨመረ በመምጣቱ የማህበራዊ ቀውስ ሊያመጣ ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል፡፡ ሩዝ አብቃይ አገሮች ያጋጠማቸውን እጥረትና ግሽበት ለመቀነስም ለጊዜው መፍትሔ አድርገው የወሰዱት የሩዝ ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ከማቅረብ መቆጠብና ይህንንም ማወጅ ነው፡፡ በግብፅም ተመሳሳይ ሁኔታ መፈጠሩን የገለፀው ይኸው ዘገባ በግብፅ የዳቦ እጥረት መፈጠሩንና ይህንንም እጥረት ተከስቶ ተቃውሞ መቀስቀሱ ታውቋል፡፡ የምግብ እጥረትና የዋጋ መወደድ አለም አቀፍ ክስተት መሆኑን ተቀማጭነቱ ዋሽንግተን የሆነው ኧርዝ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ተማራማሪ የሆኑት ሚስተር ብራውን ለዘጋቢው ገልፀው ይህም ባለፉት ዓመታት ውስጥ የአለም የሠብል ምርት የሚያስፈልገውን ፍጆታ መሸፈን ሲያቅተው ለሰባተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው የምግብ ሠብል ተቀማጭ እየቀነሰ መጥቶ ከ34 ዓመታት በፊት በነበረበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ኤክስፐርቶች እንደሚናገሩት ከሆነ ደግሞ ለእህል ዋጋ መወደድ ብዙ ምክንያቶችን ይደረድራሉ፡፡ የአለም ሕዝብ እድገት፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ውስጥ ቴክኖሎጂ አነስተኛ መሆኑ፣ የነዳጅ ዋጋ መናር፣ በእርሻ መሬት ላይ የመኖሪያ ቤቶችና ሌሎች የቢዝነስ ልማቶች እየተስፋፉ መምጣታቸው፣ ድርቅ ጐርፍና ሌሎች የአየር ፀባይ ለውጦች ጋር ተያይዞ እንደመጣም ይጠቅሳሉ፡፡ የውሃ አቅርቦት እጥረት በተለየ መልኩ መከሰቱም ለችግሩ መባባስ እንደምክንያት ቀርቧል፡፡ እንደ ኤክስፐርቶቹ ትንተና ከሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የምግብ እህል እጥረትና የዋጋ መወደድ እንዲያድግ በማድረግ ለምግብ ፍጆታ ይውሉ የነበሩት አዝእርትና እንስሳት ከምግብነት ባሻገር ለባዮፊውል አገልግሎት እንዲውሉ መደረጉ ነው፡፡ ይህም ክስተት በአለም አቀፍ ደረጃ ዋጋው እያደገ የመጣውን የነዳጅ ፍጆታ ለማካካስ የታሰበ ቢሆንም የነዳጅ ምርትን ከአዝዕርትና ከእንስሳት ለማግኘት የተደረገው ጥረት አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መገኘቱን ነው፡፡ ሁሉም አገሮች የራስ ምታት የሆነው የምግብ ሠብል ምርት ዋጋ መጨመር ከወዲሁ መፍትሄ እንዲበጅለት ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡ ሮይተርስ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ በተለይ ደግሞ ታዳጊ አገሮች የፖሊሲ አቅጣጫቸውን እንዲመረምሩና ከዋጋ መናሩ ጋር ተያያዥ የሆኑ የፖሊሲና የስትራቴጂ መንገድ መቀየስ የግድ ይላቸዋል መንግሥታት፣ በሠብል ምርት ዕድገት ወሳኝ የሆነውን የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ፈጠራ እንዲያበረታቱ፣ የአየር ፀባይ ለውጥ ጋር የሚሄድ አቅጣጫን መያዝ፣ የአካባቢ ጉዳዮች፣ የውሃ አስተዳደር ጉዳዮችን እንዲሻሻሉ ማድረግ፣ የባዮፊውል ምርት ለምግብ ዋጋ ላይ ለደረሰው ንረትን ጋር ያለውን ቁርኝት ጠንቅቀው እንዲረዱ፣ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዚምባብዌና በቬንዙዌላ በደረሰው የምግብ ዋጋ መናር የሁለቱ ሀገር መሪዎች ከችግሩ ጋር በተያያዘ መፍትሄ ነው ያሉትን "የዋጋ ቁጥጥር" በማድረግ ህግ አውጥተዋል ይህ ደግሞ ያለውን ችግር የከፋ ያደርገዋል እንጂ መፍትሄ አያመጣም ይላሉ በዘርፉ የተሠማሩ ባለሙያዎች፡፡ የወቅቱን ችግር ለመከላከልም የዋጋ ቁጥጥር በማድረግ ላይ ካሉ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳና ዶል በአፍሪካ ተጠቃሽ ሆነዋል፡፡ ሲዋ ሳንጋይ ዋና መሥሪያ ቤቱ ዋሽንግተን የሆነው "ቄቄሳ & policy resoles ህቃቋ"ሽ"በ"ስ" ተመራማሪ ሲሆኑ ቬንዙዌላ እና ዚምባቡዌ የወሰዱን የዋጋ ቁጥጥር መፍትሄ የሚያመጣ አይደለም፡፡ ባይ ናቸው፡፡ ነገር ግን ብዙ አገሮች የእነዚህ ዓይነት መንገድ እየተከተሉ ነው ይላሉ፡፡ ሳንጋይ አሁንም በምግብ ዋጋ ንረትና መፍትሄዎቹ ላይ ጥናት መደረግ አለበት ቢሆንም የዋጋ ንረቱን በሚቀጥሉት ዓመታትም የሚያቆመው የለም የሚል የጠነከረ አስተያየት አላቸው፡፡ ሳንጋይ ሲናገሩ፣ የዓለም ሕዝብ ዕድገት እየታየበት ቢሆንም በቻይና እና በህንድ የሚገኙ ሸማቾች በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ እያለፉ በመምጣታቸው የአበላል ስርዓታቸው ተቀይሯል፡፡ በዓለም አቀፍ የምግብና የነዳጅ ዘይት እየጨመረ የመጣውን ፍጥነት ያሳየው በ2008 ዓ.ም ነው፡፡ በአብነት በጃንዋሪ 2007 እና 2008 መካከል ያለው የዋጋ ግሽበት ሲታይ ከ10 በመቶ እስከ 34 በመቶ ጭማሪ አድርጓል፡፡ ከዋጋ ንረቱ በስተጀርባ የባዮ ፊዮል ምርትን በማምረት የሚውለው እህል የሚመረተው ከፍተኛ ወጪ የተደረገበት ማዳበሪያ ነው፡፡ ማዳበሪያ በፋብሪካ ለማዘጋጀት የሚፈጀው ነዳጅ ራሱ በርካታ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲሰበሰቡ የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው የሚናገሩ በርካታ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በቆሎ፣ አኩሪ አተር፣ የሽንኮራ አገዳና ሌሎች እህሎች ርካሽ የሆነውን ባዮፊዮል በማመረት ያገለግላሉ፡፡ ይህ ማለት ለሰው ልጅ ፍጆታ የሚውለው እህል እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የዋጋ መወደዱ ሊከሰት ችሏል፡፡ የዓለም ምግብ ድርጅት በበኩሉ፣ 100 ሚሊዮን ቶንስ አዝዕርት በየዓመቱ ለባዮፊዮል መስሪያ ይውላል ብሏል፡፡ ሁኔታዎች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነና 25 በመቶ የሚሆነው የዓለም እህል በተለያዩ ምክንያቶች ለልዩ ልዩ ጥቅሞች የሚውሉ ከሆነ ችግሩ እየሰፋ መጥቶ እ.ኤ.አ በ2025 አፍሪካ ለራስዋ ሕዝቦች ማቅረብ የምትችለው የእህል ምርት የፍላጎትዋ 40 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕዝብ እድገት እየጨመረ በመምጣቱ፣ ዓለም በምግብ እህል ላይ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የእህል ምርት ሠብል አቅርቦት እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ህንድ አዝመራ ችግር አጋጥሟታል፡፡ የአውስትራሊያ የአየር ሁኔታ በምግብ ሠብል የሚያስተማምን አልሆነም የቻይና ደግሞ ከፍተኛ ተጠቃሚነት ከፍ ብሏል፡፡ እነዚህ ክስተቶች መላ ካልተበጀላቸው ደግሞ አደጋው የከፋ እንደሚሆንና ታዳጊ አገሮችም ሆነ በለፀጉ የሚባሉ አገሮችን ጭምር ሊጐዳ እንደሚችልም በጉዳዩ ዙሪያ የተዘገቡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |