| በፑንትላንድ የኢትዮጵያ ወታደሮች... |
|
|
| Sunday, 06 April 2008 | |
|
በፑንትላንድ የኢትዮጵያ ወታደሮች አለመኖራቸው ፕሬዚዳንቱ አስተባበሉ
የኢትዮጵያ ወታደሮች አንፃራዊ መረጋጋት ባለበት የፑንትላንድ ግዛት ውስጥ ሰፍረዋል የሚል ግምት የክልሉ ፕሬዚዳንት ማስተባላቸው ጋሬዋይ አንላይን ዘገበ፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት መሐመድ “አዴ” ሙሴ ይህንን ያሉት ባለፈው እሁድ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በቦሳሰ የወደብ ከተማ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት ወደ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉዞ ክልላቸው ከኢትዮጵያ ያላት ኢኮኖሚያዊና የፀጥታ ግንኙነት ለማጠናከር መሆኑን ነው፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ወታደሮች በፑንትላንድ ግዛት ውስጥ በውጭ ኩባንያዎች ሊካሄድ የሚችል የነዳጅ ኢንቨስትመንት ለመከልከል በአካባቢው ሰፍረዋል የሚል አሉባልታ አስተባብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ የልዑካን ቡድን ባለፈው ወር በፑንትላንድ ዋና ከተማ ከነዳጅ ኩባንያው ተወካዮችና ከክልሉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የዝግ ስብሰባ ማድረጋቸው ድረ ገፁ ገል..ል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |