Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow የተባበሩት የ1.1 ቢሊዮን ብር...
የተባበሩት የ1.1 ቢሊዮን ብር... Print E-mail
Sunday, 06 April 2008
የተባበሩት የ1.1 ቢሊዮን ብር የነዳጅ ጨረታ አሸነፈ

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ ሙገር ሲሚንቶ ያወጣውን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የነዳጅ አቅርቦት ጨረታ አሸነፈ፡፡

በአገሪቱ ካሉ የነዳጅ ኩባንያዎች ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የተቋቋመው ይኸው ብቸኛ ድርጅት ጨረታውን ያሸነፈው በጨረታው ከተካፈሉት ቶታል ኢትዮጵያ፣ ኖክ (NOC) እና ኰቢል ኢትዮጵያ ጋር ተወዳድሮ በማሸነፉ መሆኑን ከሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ ያገኘነው መረጃ  ይጠቁማል፡፡

የተባበሩት ጨረታውን ማሸነፉ የሚገልፅ ደብዳቤ ከሙገር ሲሚንቶ በያዝነው ሳምንት የደረሰው ሲሆን በዚሁ መሠረት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያው ለሚያቀርበው ነዳጅ 1.1 ቢሊዮን ብር የሚከፈለው መሆኑ ታውቋል፡፡

የነዳጅ አቅርቦቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚከናወን ሲሆን አቅርቦቱም 88 ሚሊዮን ሊትር ፈርነስ ኦይል (furnance oil) ፣ ሁለት ሚሊዮን ሊትር ናፍጣና ቤንዚን መሆኑ ተገል..ል፡፡

ለረዥም ጊዜ በቶታል ኢትዮጵያ እጅ የነበረውን፣ በአገሪቱ ካሉ ትላልቅ የነዳጅ አቅርቦት ውሎች አንዱ የሆነው የሙገር ነዳጅ አቅርቦት ጨረታን ያሸነፈው የተባበሩት የነዳጅ ድርጅት ከዚህ ቀደም ሙገር ሲሚንቶ ያወጣውን ጨረታ በማሸነፍ ቶታል ኢትዮጵያን ከገበያው ማስወጣት ችሏል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት በተከፈተው የጨረታ ውጤት መሠረት ሁለተኛውን አነስተኛ የጨረታ ዋጋ ያቀረበው ቶታል ኢትዮጵያ መሆኑም ታውቋል፡፡

በኃያል ዓለማየሁ
 
< Prev   Next >