Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባረሩት...
ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባረሩት... Print E-mail
Wednesday, 09 January 2008

ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባረሩት ዳኞች ክስ የሚመሰረትባቸው አሉ

በተጨማሪ 16 ዳኞች ላይ ክስ ተመሰረተ

የኦሮሚያ ምክር ቤት ከሥራ እንዲሰናበቱ ከወሰነባቸው በተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ ዳኞች ፈፅመዋል በተባሉት ..የዲስፒሊን ግድፈቶች.. ክስ እንደሚመሰረትባቸው ታወቀ፡፡

Ç™‡ ŸY^ ”Ç=c“u~ የሚጠይቀው ሪፖርት ሲቀርብ ..ከዳኞች ከሚጠበቅ ሥነ-ምግባር ውጪ.. የተለያዩ ጥፋቶችን ፈፅመዋል በሚል የቀረበባቸው የጥፋት ዝርዝር የሚያስከስስ በመሆኑ በቀጣይ ክስ የሚመሰረትባቸው እንዳሉ የሪፖርተር ታማኝ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

. . . የዳኝነትን ሥራን በሙስና፣ በአማላጅ፣ በተለያዩ አድሏዊ ድርጊቶች እንዲከናወን በማድረጋቸው፣ ፍትህ ፍለጋ ፍርድ ቤት የሚቀርቡትን ተገልጋዮች በማመናጨቅ፣ በማስፈራራት በስድብ ስብዕናቸውን በማዋረድ፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ የታወጁትን ህጐች በአግባቡ ባለመተርጐምና ዜጐችን በአግባቡ ባለማስተናገድ፣ ለህግ የበላይነት መስፈን ቅድሚያ መሰለፍ ሲገባቸው በተቃራኒ ለህግ መሸርሸር ምክንያት በመሆናቸው ዜጐች በፍርድ ቤቶች ላይ እምነት እንዳይኖራቸው አድርገዋል.. በማለት የቀረበባቸው የሪፖርት ሰነድ ያስረዳል፡፡

ህብረተሰቡ በፍርድ ቤቶች በሚደርሱበት በደል ..በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይኖራቸው አድርገዋል.. ያላቸውን ዳኞች ይፋ ያደረገው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ርምጃ የተወሰደባቸውን ዳኞች ስም ዝርዝር ጠቅሷል፡፡ በደብዳቤው የተጠቀሰውና ዳኞቹ ከሥራ እንዲሰናበቱ ያደረጋቸው ነጥቦች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ያለባቸውን ችግር በዝርዝር ለማወቅ እንዲያጣራ ባለፈው በጀት ዓመት የተቋቋመው ኮሚቴ ለሦስት ወራት ገደማ ባደረገው ጥናት የዳኞች የዲሲኘሊን ግድፈት ሕብረተሰቡ በፍርድ ቤቶቻችን ላይ ለሚያቀርበው ቅሬታ ዋናውን ድርሻ የሚይዝ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ለፍትህ አካላት ባለሙያዎች (የፍርድ ቤት ዳኞች፣ ዐቃቤ ሕግና ፖሊሶች) ባለፈው በጀት ዓመት መጨረሻ ለሃያ ቀናት በመንግሥት ፖሊሲዎች ላይ ሥልጠና ሲሰጥም የፍርድ ቤቶቻችን ተሿሚ ዳኞች ከፍተኛ የሥነ ምግባር ችግር ያለባቸው መሆኑ በዳኞችም ጭምር ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡

ከዚያ በኋላ ሁሉም የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ዳኞች በተሳተፉበት ለአንድ ቀን በተደረገ ውይይት የዳኞች የሥነ ምግባር ጉድለት ከፍተኛ ችግራችን መሆኑ በሰፊው ተነስቶ ከዳኞች ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘ ከመሆኑም በላይ ከባድ የዲስኘሊን ጉድለት ያለባቸውና ሕግን በአግባቡ ሥራ ላይ ባለማዋል ሕዝብና መንግሥትን የሚያጋጩ ዳኞች ተለይተው ሕጉንና ሥርዓቱን ተከትሎ አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ዳኞች ተስማምተውበታል፡፡ በተለይም በጥቂት ግን ከፍተኛ ችግር ባለባቸው ዳኞች ምክንያት የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች በሕብረተሰቡ ዘንድ ሊጠሉና ሊወገዙ አይገባም የሚል አስተያየት ቀርቦ ከቤቱ የላቀ ድጋፍ አግኝቷል፡፡

ቀጥሎም በተለያዩ መድረኮች በየደረጃው ካሉ የፍርድ ቤቶቻችን አመራር አካላት በተደረገው ውይይት አስፈላጊውና አግባብነት ያለው ማጣራት ተደርጎ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱ የፍርድ ቤቶችን ሕልውና ለማስጠበቅ በአሁኑ ወቅት ሊኖረን የሚገባ ብቸኛ መፍትሄ መሆኑ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በመቀጠል የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በዋናነት ከፍርድ ቤቶቻችን ዳኞች የምስክርነት ቃል በመቀበል፣ ችግር ያለባቸውንና በየጊዜው በተገልጋዩ ዜጋ አቤቱታ የሚበዛባቸውን ዳኞች በተመለከተ የሰሩአቸውን መዛግብት በመመርመር፣ የባለጉዳዮችን ቅሬታ በመስማት እንዲሁም ከተለያዩ የፍትህ አካላት ጋር በመነጋገር በቂ ማስረጃ የተገኘባቸውን ዳኞች በመለየት በክልሉ የዳኞች ሥነ ምግባር ደንብ መሠረት ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡

የተመሠረተባቸው የዲሲኘሊን ክስም ደርሶአቸው ያላቸውን መቃወሚያና ክርክር እንዲያቀርቡ ተደርጓል፡፡

ያቀረቡት መቃወሚያና ክርክር በክልሉ ጉባዔ ለዚህ ጉዳይ በተመሠረተ ኮሚቴ ከተመሠረተባቸው የዲሲኘሊን ክስና ከዲሲኘሊን ደንቡ ጋር አንድ በአንድ ታይቶ ለጉባዔው የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ የዚህ ኮሚቴ አባላት የጉባዔው አባላትና በአብዛኛው ለረጅም ጊዜ በዳኝነት ያገለገሉ ናቸው፡፡

የኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ ቀደም ተብሎ ለጉባዔው አባላት በሙሉ ተልኮ አባላቱ በቂ ዝግጅት አድርገው ለጉባዔው ስብሰባ እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡

በጉባዔው ስብሰባ ዕለትም ከፍተኛ ውይይትና ክርክር እንዲሁም የማጣራት ሥራ ተደርጎ ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተዘረዘሩት ዳኞች ከፍተኛ የዲሲኘሊን ግድፈት ያለባቸው መሆኑ በሚያሳምንና በበቂ ማስረጃ ስለተረጋገጠባቸው  ከዳኝነት እንዲሰናበቱ ጉባዔው በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል፡፡ ምክር ቤቱ በ336 ድጋፍ በ36 ድምፅ ተአቅቦ ያለአንዳች ተቃውሞ ውሳኔውን አፅድቆታል፡፡

ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አቶ ግርማ ሚደቅሳ፣ አቶ ገለታ ደገፋ፣ አቶ ፉፋ ለገሠ፣ አቶ ስብሀት አክሊሉ፣ አቶ አለማየሁ ብሪሳ፤ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች አቶ ሐሰን ጅማ /አዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት/፣ ወ/ሮ ፅጌ አብዲ /ከምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት/፣ አቶ ሽመልስ ሄይ /ጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት/፤ ከወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች አቶ አለማየሁ አበጄ /ከምዕራብ ሸዋ ዞን/፣ አቶ አበበ ሰቦቃ /ከምስራቅ ሐረርጌ ዞን/፣ አቶ ከሊፋ አህመድ /ከምስራቅ ሐረርጌ ዞን/፣ አቶ ገለታ ቦሩ /ከምዕራብ ሸዋ ዞን/፣ አቶ ደጀኔ አሰፋ /ከምዕራብ ሸዋ ዞን/፣ አቶ ረጋሣ ኦልአና /ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን/፣ አቶ ጉቱ አባሶ /ከአርሲ ዞን/ ናቸው፡፡

ከዲሲፒሊን ግድፈት ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሥራ ስድስት የዞንና የወረዳ ፍርድ ቤቶች ኘሬዚዳንቶችና ዳኞች ላይ ክስ መመስረቱ ታወቀ፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ክስ መስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ካሉት ውስጥ ሁለቱ ኘሬዚዳንቶች ሲሆኑ የተቀሩት የከፍተኛ፣ የዞንና የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች እንደሆኑ መረጃው አመልክቷል፡፡

ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ክስ የቀረበባቸው ዳኞች መልስ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡ በተጠየቁት መሠረት ለቀረበባቸው ክስ መልስ የሰጡ እንዳሉና መልስ እንዲሰጡ የሚጠበቁ አሉ፡፡

በአሰግድ ተፈራ

 
< Prev   Next >