Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ መጻሕፍት ትዘረጋለች"
"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ መጻሕፍት ትዘረጋለች" Print E-mail
Sunday, 06 April 2008
Imageየኢትዮጵያ መጻሕፍት ለልጆችና የትምህርት ድርጅት አምስተኛውን የልጆች የመጻሕፍት ሳምንት "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ መጻሕፍት ትዘረጋለች" በሚል መሪ ሐሳብ ሥር በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው፡፡

 

መጋቢት 23 ተጀምሮ እስከ መጋቢት 29 ቀን ድረስ በሚከበረው የልጆች የመጻሕፍት ሳምንት መጻሕፍት ልክ እንደምግብ ሁሉ ለሰው ልጅ ያላቸውን ጠቀሜታ ለማመልከት በመክፈቻው ቀን 5ዐዐ መጻሕፍትና ዳቦ ለሕፃናት ተበርክቷል፡፡

መጋቢት 24 ቀን በታዋቂው ዴንማርካዊ የሕፃናት ታሪክ ጸሐፊ ሃንስ ክርስቲያን አንደርሰን የተሰየመው "የዓለም አቀፍ የሕፃናት ተረቶች (ታሪኮች) ቀን" ሲሆን በዕለቱ ሕፃናቱ የሃንስ ክርስቲያን ድርሰት የሆነውን "የንጉሡ አዲስ ልብስ" በድራማ መልክ አቅርበዋል፡፡

በልጆች መጻሕፍት ሳምንት ክብረ በዓል ከሚስተናገዱት አንዱ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ "ዘ ኤሌፋንት ኤንድ ዘ ኮክ" በሚል ርእስ የታተመው የብሔረሰቦች የተረቶች ስብስብ መጽሐፍና በሦስት ቋንቋዎች፣ በአማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ኦሮምኛ እና አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ትግርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የተረት ሥዕል መጻሕፍት ይመረቃሉ፡፡

"ቡክ-አ-ቶን" ተብሎ የተሰየመ ንባብና የመጻሕፍትን ሥርጭት ለማበረታታትና የባለ ድርሻ አካላትን ትኩረት እንዲያገኝ የሚጠይቅ ለመጽሐፍ የሚደረግ የአምስት ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ መጋቢት 28 የሚደረግ ሲሆን የንባብ ባህልን በኅብረተሰቡ ውስጥ ለማስፋፋት፣ ማኅበረሰቡ ከማንበብ ጎን ለየአብያተ መጻሕፍቱ መጻሕፍት ማሟላት አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል፡፡

የእግር ጉዞው የሚነሳው ዋናው ዳሸን ባንክ ጀርባ ከሚገኘው ሾላ የሕፃናት ቤተ መጻሕፍት ሲሆን መድረሻው ዋናው ፖስታ ቤት ይሆናል፡፡

የመጻሕፍት ሳምንቱ የሚጠናቀቀው በኢትዮጵያ አንድነት ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ አዲስ በተከፈተ ቤተ መጻሕፍት ምረቃ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ መጻሕፍት ለልጆችና የትምህርት ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርት፣ የልጆችና የወጣቶች መጻሕፍት ሕትመትን ለማስፋፋት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያስተዋወቀው የመጀመሪያው በአህያ የሚጎተት ቤተ መጻሕፍት በአዋሳ ዙሪያ ላሉ ገጠራማ አካባቢዎች እየተዘዋወረ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባው ሾላ የሕፃናት ቤተመጻሕፍት 15"000 መጻሕፍት ያሉት ሲሆን ዕድሜያቸው ከ8 እስከ 18 የሆኑ ልጆች ይስተናገዱበታል፡፡
በሔኖክ ያሬድ

 
< Prev   Next >