Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow በጅጅጋ በተፈፀመ ጥቃት የሞትና...
በጅጅጋ በተፈፀመ ጥቃት የሞትና... Print E-mail
Wednesday, 09 January 2008

በጅጅጋ በተፈፀመ ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ

በጅጅጋ ከተማ በደረሰ የፈንጂ ፍንዳታ አራት የሱማሌ ክልል ፖሊሶች የመቁሰል አደጋ አጋጠማቸው፡፡ ከፈንጂ ፍንዳታው በፊት በነበሩት ተከታታይ ቀናት በተፈፀመ የተኩስ ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ቆስለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል የፎረንሲክ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር መሀመድ አሊ ሀሰን ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ታህሳስ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በጅጅጋ ከተማ አብዲሰላም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ በፌዴራል ፖሊስ መኪና ውስጥ የነበሩ አራት የክልሉ ፖሊሶች በፈንጂ ፍንጣሪ ቆስለዋል፡፡ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል፡፡

የፈንጂ ፍንዳታው ከመድረሱ አንድ ሳምንት በፊት በነበሩት ተከታታይ ቀናት በፖሊሶችና ሲቪሎች ላይ የተኩስ ጥቃት ተፈፅሞ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል፡፡

ኮማንደር መሀመድ እንዳሉት ታህሳስ 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ያልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች በከፈቱት የተኩስ ጥቃት አንድ ትራፊክ ፖሊስ ተገድሏል፡፡ በዚያው ሰሞን በተፈፀመ ሌላ ጥቃት የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሁለት ፖሊሶች በሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

ከሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው በጅጅጋ ከተማ ጥቃት እየፈፀሙ የሚገኙት ያልታወቁት ታጣቂ ኃይሎች ጥቃት እየፈፀሙ የሚገኙት ያልታወቁት ታጣቂ ኃይሎች ጥቃት እያደረሱ ያሉት በከተማዋ ሲቪል ነዋሪዎች ጭምር ነው፡፡ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ከተፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ አንድ ነጋዴ በመደብሩ ውስጥ እንዳሉ ተመትተው መገደላቸውን የጠቆሙት ኮማንደር መሀመድ ወንጀል ፈፃሚው ለጊዜው አለመያዙን ተናግረዋል፡፡

ኦብነግና አሊትሀድን የመሳሰሉ አሸባሪ ኃይሎች በሱማሌ ክልል ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ የገለፁት የፎረንሲክ ምርመራ ኃላፊው በቅርቡ በመከላከያ ሰራዊት ጥቃት የደረሰባቸው የኦብነግ ኃይሎች ጥቃቱን ፈፅመዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘም ስምንት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንም ኮማንደር መሀመድ አክለው ገልፀዋል፡፡

በኃይሌ ሙሉ

 
< Prev   Next >