| ሴቶች ጥሩ የፋይናንስ.... |
|
|
| Sunday, 06 April 2008 | |
|
ሴቶች ጥሩ የፋይናንስ መሪ መሆን አልቻሉም
በፋይናንስ የትምህርት ዘርፍ በመማር ላይ ያሉ ሴት ተማሪዎች ቁጥር በርካታ ቢሆንም ትምህርታቸውን አጠናቀው በሙያቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የመድረስ እድላቸው ግን አነስተኛ መሆኑን የሚያሳይ ጥናት ረቡዕ እለት ይፋ ሆነ፡፡ በቻርተርድ ሰርቲፋይድ አካውንታንት ማኅበር የተካሄደው ጥናት፣ ከሴቶች ይልቅ ለወንዶች የፋይናንስ ምሩቃን የመሪነት አቅም ቀላል እንደሆነ ስልሳ ሦስት በመቶ የሚሆኑ የፋይናንስ አመራሮችን ጠቅሶ አመልክቷል፡፡ ጥናቱ በ3381 የማኅበሩ አባላት ላይ የተደረገ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከመቶ አሥራ ስድስት አገሮች ከተውጣጡ 19 የፋይናንስ ሴት አመራሮች ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸዋል፡፡ ይህ በሴቶቹ ብቃት ማነስ ሳይሆን በሥራ ሕይወታቸው ሚዛናዊነት ምክንያት እንደሚከሰት ጥናቱ ቢጠቁምም ይህ ነው የሚባልና የሚጎላ ምክንያት አልተጠቀመም፡፡ የተቋማዊ የተሳሳተ እይታና ባህላዊ ተጽዕኖዎች ጎልተው በምክንያትነት ተቀምጠዋል፡፡ ባለፉት አስርት ዓመታት ችግሩ የሥራ መስኩና ችግርና በመስኩ የተሰማሩ ሴቶች ጥረት አለማድረግ መሆኑ ጐልቶ ቢገለጽም ባህላዊ ተጽዕኖዎች ሴቶች ላይ የሚያደርሱት ተጽዕኖም ትልቁ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |