Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow “አዲሱ”ቴሌ በሰኔ ወር ሥራ ይጀምራል
“አዲሱ”ቴሌ በሰኔ ወር ሥራ ይጀምራል Print E-mail
Sunday, 06 April 2008
-በየደረጃው የዋናውን ቴሌ ሥራ ይረከባል

በኢትዮጵያ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በአዲስ አሰራር፣ በአዲስ ቴክኖሎጂና በአዲስ አስተሳሰብ የሚቀይረው የትራንስፎርሜሽን ቢሮ በሰኔ ወር ሥራ ይጀምራል፡፡ የትራንስፎርሜሽን ቢሮው አንድ ሺ የሚሆኑ ባለሙያዎችን ቀጥሮ የአሜሪካውያን ኢትዮጵያውያን አማካሪዎች ለአንድ ዓመት ሲያሰለጥን ማየቱን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡


የሪፖርተር ምንጮች እንዳስታወቁት “The New ETC” በሚል የሽግግር ቢሮ የተቋቋመው በቴሌ ያለውን ያረጀ አስተሳሰብና አሰራር በጥገና ማስተካከል እንደማይችል በመንግሥት ስለታመነበት ነው፡፡

በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢንጂነሪንግ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተሻለ ውጤት የተመረቁ ተማሪዎች ተመልምለው ከኮርፖሬሽኑ የተመረጡ ታክለው ቅጥር ከተፈፀመላቸው በኋላ ስልጠናውን መከታተል መጀመራቸውን ከምንጮቻችን ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ቴክኖሎጂው ሙሉ በሙሉ በዜድ ቲ ኢ የሚዋቀረው የሽግግር ቢሮ (አዲሱ ቴሌ) በየደረጃው መምሪያዎችን ከሊሴ ገብረ ማርያም ትምህርት ቤት በስተጀርባ ወደ ተሰራው ህንፃ ያዘዋውራል፡፡ ለሥራው ቅርብ የሆኑ እንደገለፁት በቅድሚያ የደንበኞች አገልግሎትና የአስተዳደር ጉዳይ ጋር የተቆራኙ መምሪያዎች ወደ ሽግግሩ ቢሮ ይዘዋወራሉ፡፡

ቢሮው ዘመናዊ አደረጃጀት፣ ዘመናዊ የቢሮ መገልገያዎች የተሟሉለት ሲሆን የተጠቀሱትን የሥራ ዘርፎች የሚረከበው የሽግግሩ ቢሮ በሰኔ ወር ሥራ እንደሚጀምር ለፕሮጀክቱ የተያዘው መርሃ ግብር ያስረዳል፡፡

በየደረጃው የዋናውን ቴሌ ሥራ የሚረከበው የሽግግሩ ቢሮ የሚፈጥረው አሰራርና የሚጠቀመው ቴክኖሎጂ አዲስ ከመሆኑ ውጪ የቀድሞው የሚለየው ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ምንጮቻችን “የትራንስፎርሜሽን ቢሮው ቴሌን ከስር እስከ አናቱ የሚቀይር፣ ስር ነቀል ለውጥ የሚካሄድበትና ቴሌን ከቀድሞ አሰራሩ፣ አመለካከቱና የኖረ ባህሉ የሚያላቅቅ ነው” ብለዋል፡፡ የሽግግር ቢሮው ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰር አቶ ወልደጊዮርጊስ ወልዱ መሆናቸውም ታውቋል፡፡  

በአንድ ወቅት የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአሜሪካ የቴሌኮም ባለሙያዎች ተቀጥረው በቴሌ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን፣ ይህም የተደረገው በቴሌ የኖረውን ያረጀ አሰራር ለመቀየር እንደማይቻል ስለታመነበት እንደሆነ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >