| በ27 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው.... |
|
|
| Sunday, 06 April 2008 | |
|
በ27 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው ቤተመጻሕፍት ማሰሪያ የሚውል ቦታ እስካሁን አልተገኘም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሚሌኒየም ጽህፈት ቤት በ27 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚያቋቁመው የሕዝብ ቤተመጻሕፍት ሕንፃ መገንቢያ የሚውል ቦታ በማፈላለግ ላይ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ኃይለሥላሴ አስታወቁ፡፡
ሕንፃውን ለመገንባት ታስቦ የነበረው በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል አጠገብ በሚገኘውና በግ ተራ አካባቢ ባለው ቦታ ላይ እንደነበር አቶ ኪሮስ አመልክተው፣ ይኸው ቦታ ለኢንተርናሽናል ሆቴል ግንባታ እንዲውል በመደረጉ ሌላ ቦታ የማፈላለጉ እንቅስቃሴ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |