Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በሶማሊያ የተመድ ሠራተኞች ታገቱ
በሶማሊያ የተመድ ሠራተኞች ታገቱ Print E-mail
Sunday, 06 April 2008
ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች ማንነታቸው በውል ባልታወቁ ታጣቂዎች መታገታቸውን ቢቢሲ ከሥፍራው ያሰራጨው ዘገባ አመለከተ፡፡
 
በዘገባው መሠረት ሁለቱ ሠራተኞች የተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት ሠራተኞች ናቸው፡፡ የታገቱት እንግሊዛዊና ኬንያዊ የተመድ ሠራተኞች የደህንነት ሁኔታ አልታወቀም፡፡ በሶማሊያ በጁባ አካባቢ ሲኮው ከተማ የታገቱት የተመድ ሠራተኞች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ የአይን እማኞችን በመጥቀስ እንግሊዛዊው ታጋች በጥይት መቁሰሉን ዘገባው አመልክቷል፡፡

በሶማሊያ የአለም አቀፍ የልማትና የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች እንዲሁም ጋዜጠኞች ላይ በታጣቂዎች የሚደርሰው የእገታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ተቋማት ሥራቸውን ለማቆም መገደዳቸው ታወቋል፡፡


ተመድ ተመላሽ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ቁጥር በእጥፍ ያሳድጋል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን በኡጋንዳ፣ በኬንያና በኢትዮጵያ የሚገኙትን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን የደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች ለመመለስ ጥረት መጀመሩን የድርጅቱ የዜና አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ኮሚሽነር አንቶኒዮ ጉተርስ ያለፈው ሳምንት በኡጋንዳ በሰጡት መግለጫ በሚቀጥለው ወር በሱዳን በሚደረገው የህዝብ ቆጠራ ውስጥ ስደተኞቹ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡ ኮሚሽነሩ በኡጋንዳ ከነበሩት አንድ መቶ ሀምሳ ሺ በላይ የሱዳን ስደተኞች መካከል ስልሳ ሺ ገደማ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፣ "በአገሪቱ በሚደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውስጥ እንዲካተቱ ሲባል ተመላሽ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር በእጥፍ እንዲያድግ ይደረጋል" ብለዋል፡፡

-----------------
በኮንጐ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተነሳ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኮንጐ ላይ የተጣለው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ መወሰኑን የድርጅቱ ድህረ ገጽ መረጃ አመለከተ፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት በዴሞክራቲክ ኮንጐ ላይ የጣለውን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ከአገሪቱ መንግሥት ላይ እንዲነሳ ወስኗል፡፡ በውሳኔው መሰረት የአገሪቱ መንግሥት እንዲሁም የአማጺ ቡድኖችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የጦር መሣሪያ ዝውውር እንዳያደርጉ አስጠንቅቋል፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት የጦር መሣሪያ ዝውውር በአካባቢው የሚደረግ ከሆነ ማዕቀቡን እንደገና ለመጣል የሚገደድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ለዚህም የተመድ የጥናት ኤክስፐርቶች በኮንጎ እንዲሁም በጎረቤት አገራት የጦር መሳሪያ ዝውውር ጥናት እንደሚያደርጉ አስታውቋል፡፡ የጥናት ቡድኑ ከስድስት ወር በኋላ በሚያቀርበው ሪፖርት የማዕቀቡ አስፈላጊነት የሚጤን መሆኑ ተገልጿል፡፡

--------------
የአለም ባንክ የድርቅ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ገለፀ

የአለም ባንክ በአለም ላይ እየተከሰተ ያለው የድርቅ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የአለም አቀፍ ማኅበረሰብ በአንክሮ እንዲመለከተው ማሳሰቡን የአሶስየትድ ፕሬስ ዘገባ አመለከተ፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት ሮበርት ዞሊክ በሠላሳ ሶስት አገራት አስቸጋሪ የምግብ እጥረት መኖሩን ገልፀው "ይህም ከፍተኛ ስጋት ነው" ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በድርቅ ምክንያት ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ንረት መከሰቱን አስታውቀዋል፡፡ ሮበርት ዞሊክ የተመድ የምግብ ፕሮግራም ድርጅት ለሚያካሂደው የምግብ እርዳታ አቅርቦት ከአምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት በአፋጣኝ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡
 
< Prev   Next >