Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የአክሱም ሐውልት ሐምሌ...
የአክሱም ሐውልት ሐምሌ... Print E-mail
Sunday, 06 April 2008
የአክሱም ሐውልት ሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ በቦታው ይቆማል

የአክሱም ሐውልት ሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ ሙሉ በሙሉ በቦታው እንደሚቆም የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ ለተከላው የሚወጣው አራት ሚሊዮን ዶላር በሙሉ የሚሸፈነው በጣሊያን መንግሥት ነው፡፡
የመሠረት ሥራው የተጠናቀቀው የአክሱም ሐውልት፣ ከአንድ ወር በኋላ የተከላ ሥራው እንደሚጀመርና ሚሊኒየሙ ከመጠናቀቁ በፊት ሐምሌ 2ዐዐዐ ዓ.ም. አጋማሽ ላይ እንደሚቆም፣ እ.ኤ.አ በ2ዐዐ8 መጨረሻ ላይ ጠቅላላ የኘሮጀክት ሥራው እንደሚጠናቀቅ ገልጿል፡፡

*                        *                   *

በማንኛውም ቀን ወደ ጀርመንና አዲስ አበባ መብረር ይቻላል

ከአዲስ አበባ ጀርመን ፍራንክፈርትና ከፍራንክፈርት አዲስ አበባ በሳምንት ሦስት ቀናት ብቻ የነበረውን የበረራ አገልግሎት ያለማቋረጥ በየዕለቱ ተጓዢ ደንበኞችን ለማስተናገድ የሁለቱም አየር መንገዶች ጥምረት ፈጥረው መብረር መጀመራቸውን አስታወቁ፡፡

ሁለቱ አየር መንገዶች (የኢትዮጵያ አየር መንገድና የጀርመን ሉፍታንዛ አየር መንገድ) እንዳስታወቁት ከመጋቢት 21 ወይም እ.ኤ.አ ማርች 3ዐ ቀን 2ዐዐ8 ጀምሮ የጥምረት በረራ ስምምነት በማድረግ ወደ ሁለቱም ከተሞች ለመጓዝ መንገደኞች በሁለቱም የአየር መንገዶች እየተመዘገቡ በፈለጉበት ቀን መብረር ይችላሉ፡፡

*                        *                   *

የቅጂና ተዛማጅ መብቶች የሕግ አፈፃፀም የሚከታተል ኮሚቴ ሊቋቋም ነው

በሕገወጥ መንገድ የፈጠራ ሥራን ዘርፎ በማባዛት ጥቅም ለማግኘት የሚካሄደውን የወንጀል ድርጊት ለመግታት አንድ አስገዳጅ ኮሚቴ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲቋቋም ተወሰነ፡፡

በቅጂና ተዛማጅ መብቶች የሕግ አፈፃፀም ችግሮች ላይ ለሁለት ቀናት ሲመክር የቆየው የባለድርሻዎች የጋራ መድረክ ሲጠናቀቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ፣ በኪነጥበብ የፈጠራ ሥራዎች ላይ የሚፈፀመውን የመብት ገሰሳ በሕግ አፈፃፀም መከበሩን በቅርብ የሚከታተል የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወስኗል፡፡

*                        *                   *

ከጣና ሐይቅ 900 ሺ ኪሎ ግራም አሣ ተመረተ

ከጣና ሐይቅ 9ዐዐ ሺ ኪሎ ግራም አሣ ተመርቶ ለአካባቢው ገበያ መቅረቡን የደቡብ ጐንደር ዞን ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

አሣውን ያመረቱት ሐይቁን በሚያዋስኑ ወረዳዎች በማህበር የተደራጁ 46ዐ አስጋሪዎች መሆናቸውን፣ በፎገራ፣ ደራና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች የተደራጁት አስጋሪዎች ለአሣ ሀብት ልማት ኮርፖሬሽንና ለተጠቃሚዎች በመሸጥ ከ7ዐዐ ሺ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ገልጿል፡፡

*                        *                   *

ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች ከ854 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በስሩ ያሉ መሥሪያ ቤቶች በተያዘው የበጀት ዓመት የእቅድ ክንውን ከፍተኛ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልፆ፣ በስምንት ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላኩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች 854 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጿል፡፡

*                        *                   *
የአትክልትና ፍራፍሬ ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ሊሰጡ ነው

የመቀሌ ኘላንት ቲሹ ካልቸር ላብራቶሪ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡና በሽታን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቋቋሙ ከ65ዐ ሺ በላይ የተለያዩ የአትክልት፣ ፍራፍሬና አበባ ዝርያዎች ከሚቀጥለው ወር (ሚያዚያ) ጀምሮ እንደሚያከፋፍል አስታወቀ፡፡ 
 
< Prev   Next >