Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንትና...
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንትና... Print E-mail
Wednesday, 09 January 2008

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንትና ሶስት ዳይሬክተሮች ከስራ ታገዱ

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፀጋዬ ተጠምቀ እና የባንኩ ዳይሬክተሮች አቶ ገ/ሚካኤል ታምራት፣ አቶ ገብረእግዚአብሄር ወልዱና ›„ ¡õÁK¨< ²Ñ¾ ከስራቸው ታገዱ፡፡ የባንኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ መረሳ ኃይለ ሥላሴ የግዳጅ እረፍት እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ባንኩ የፕሬዚዳንቱ መነሳት በችግር አይደለም ይላል፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቻችን ለመረዳት እንደቻልነው የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ቦርድ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ከትናንት ወዲያ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው፡፡ በቦርዱ ውሳኔ መሰረት መታገዳቸው የተገለፀላቸው የባንኩ ኃላፊዎች ውሳኔ በተላለፈበት ቀን በእጃቸው የሚገኘውን ንብረት አስረክበዋል፡፡ ከኃላፊነታቸው የተነሱት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ ተጠምቀ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጥጥር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሰርተዋል፡፡ የግዳጅ እረፍት እንዲወስዱ የተወሰነባቸው ሥራ አስኪያጁ አቶ መርሳ ኃይለ ሥላሴ በአገር ደረጃ ብቸኛው የውጭ ምንዛሬ አሰልጣኝ እንደሆኑ ታውቋል፡፡

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወልደ ገብርኤል ወዳጆ የአቶ ፀጋዬ ተጠምቀን ቦታ ተክተው እንዲሰሩ ቦርዱ ወስኗል፡፡ አቶ ገ/ሚካኤል ታምራት በአቶ ጌታቸው ኪሮስ፣ አቶ ከፍያለው ዘገየ ደግሞ በወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ መተካታቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ገለፀዋል፡፡

ቦርዱ ከትናንት ወዲያ ባስተላለፈው ውሳኔ የታገዱት ግለሰቦች የባንኩ ኦዲተር ባለበት ንብረታቸውን እንዲያስረክቡ በደብዳቤ ሲገልጽ ኃላፊዎቹን ያባረረበትን ምክንያት እንዳላስቀመጠ ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ 

በሌላ በኩል የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ለሪፖርተር ጋዜጣ ትናንት በላከው መግለጫ የኃላፊዎቹን መነሳት በዝርዝር ሳይገልጽ የፕሬዚዳንቱን መነሳት ብቻ ገልጿል፡፡

የባንኩ አክስዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ታህሳስ 25 ቀን 2000 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የባንኩ ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ ፀጋዬ ተጠምቀ ምትክ አቶ ወልደ ገብርኤል ወዳጆ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑን አስታውቋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ከሥራ መሰናበት ገንዘብ ነክም ይሁን ሌላ ባንኩን ሊጎዳ ከሚችል ተግባር ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን ያመለከተው ቦርዱ ፕሬዚዳንቱ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈጣን እንቅስቃሴ በማሳየት ላይ ካለው የባንኪንግ ኢንዱስትሪ ጋር አብሮ ለመራመድ ወቅታዊ፣ እንደ ሁኔታው ተገቢ የሆኑ እና የተጠኑ ውሳኔዎችን ማሳለፍ ስላስፈለገ መሆኑን ገልጿል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በተመሰረተ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 16 ቅርንጫፎች ከፍቷል፡፡ የባለ አክስዮኖቹ ቁጥርም በአሁኑ ወቅት 5500 የደረሰ ሲሆን የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከ162 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍ ማለቱን ባንኩ ለሪፖርተር ጋዜጣ ከላከው ጋዜጣው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በኃይሌ ሙሉ

 
< Prev   Next >