Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የዓሣ ዋጋ
የዓሣ ዋጋ Print E-mail
Sunday, 06 April 2008
ዝዋይ ከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ የዝዋይ ስም ሲነሳ በዝዋይ ሐይቅ የሚመረተውን ዓሣ ማስታወስ የግድ ይላል፡፡

 ከዝዋይ ሐይቅ በዓመት ከ4 ሺህ 500 ቶን በላይ የሚደርስ የዓሣ ምርት እንደሚመረት ይገመታል፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከሚገባው ዓሣ ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውም የሚገኘው ከዚሁ ሐይቅ ነው፡፡

የዓሣ አመጋገባችን ብዙም የዳበረ ባይሆንም በአሁኑ ወቅት ለውጥ እየታየበትና የተጠቃሚው ቁጥር በማደግ ላይ ነው፡፡ በተለይ በፆም ወቅት የዓሣ ገበያ የሰፋ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን የዓሣ አመጋገባችን ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር አሁንም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በባለሙያዎች ገለፃ መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአማካይ አንድ ሰው በዓመት 14 ኪ.ግ ዓሣ ይመገባል፡፡ ሌላው ቀርቶ ከሰሃራ በታች ያሉ አገሮች በአማካይ በዓመት 7 ኪ.ግ ዓሣ ይመገባሉ፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ግን በዓመት የሚመገበው ከግማሽ ኪ.ግራም በታች ነው፡፡

እንዲህም ሆኖ ነው፡፡ በፆም ወቅት በአዲስ አበባ የአንድ ኪሎ የዓሣ ዋጋ በአማካይ ሃያ ብር ድረስ ይደርሳል፡፡

ከሦስት ቀናት በፊት ዝዋይ ነበርኩ፡፡ ዓሣ ወደሚመረትበት የዝዋይ ሐይቅ ተጉዤ እንዴት  እንደሚመረትና እንዴት እንደሚሸጥ ለመመልከት ችያለሁ፡፡

በግልም ሆነ በማኅበር የተደራጁ የዓሣ አጥማጆች አሉ፡፡ እንደተነገረኝ ቁጥራቸው ከአራት ሺህ በላይ ይሆናል፡፡ አጥማጆቹ አንድ መካከለኛ መጠን ያለውን ዓሣ የሚሸጡት በአንድ ብር ነው፡፡ ተወደደ ከተባለ ደግሞ አንድ ብር ከሃምሳ ነው፡፡ ይህንንም የዓሣ ምርት ከአምራቾቹ በብዛት የሚገዙት ከአዲስ አበባ የሚመጡ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ የከተማው ነዋሪዎችና ከተማዋን የሚያቆራርጥ መንገዶች ይገዛል፡፡ እንደታዘብኩት አንዳንድ ብር የሚሸጡት አሣዎች አራት ወይም አምስቱ አንድ ኪሎ ይመዝናሉ፡፡ በዚህ ስሌት የከተማችን ነጋዴዎች አንዱን ኪሎ ዓሣ ቢበዛ በአምስት ብር ይገዛሉ ማለት ነው፡፡

አዲስ አበባ ሲያመጡት ግን 20 ብር ቢደረግ ይሻላል፡፡ ይህ በምን ሂሳብ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ዓሣውን ለማጥመድ ፈተናውን የሚጋፈጠውን የሚያገኘው ጋር ሲነፃፀር አይመጣጠንም፡፡

የከተማችን የዓሣ ነጋዴዎች ዝዋይ ላይ በአንድ ብር የሚገዙትን ዓሣ በአዲስ አበባ ይህን ያህል ዋጋ ጨምረው የሚሸጡበት ምክንያት ትራንስፖርት ወጪ ነው? ሌላው ቀርቶ እያንዳንዱ ባለ አንድ ኪሎ ዓሣ በሚኒባስ ወንበር ተይዞለት ..ዓሣ በለው፣ በለው፣ ዓሣ በለው.. የሚለውን ዘፈን እያዳመጠ ቢመጣ እንኳ አሁን አዲስ አበባ ውስጥ የሚሸጥበትን ያህል ዋጋ አያወጣም፡፡

ይህም ብቻ አይደለም፡፡ በዓሣ ምርትዋ የምትታወቀው ዝዋይ የደረሰ ዓሣ ሳይመገብ አይመጣምና ከሐይቁ ጉብኝቴ መልስ ከአንዱ ሆቴል ጐራ ብዬ ዓሣ አዘዝኩ፡፡ ያዘዝኩት ዓሣ ጥብስ ነው፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ መጣልኝ፡፡ በሳህኑ ላይ አንድ መካከለኛ ዓሣና አንድ ትንሽዬ ዓሣ ከአንድ ዳቦ ጋር ቀርቦልኝ ማባያም አለው፡፡

ትንሽዬዋ ዓሣ ብዙም ..ሥጋ.. የላትም፡፡ እንዲያውም የዓሣ ባለሙያዎች እነዚህ ዓሣዎች ፈፅሞ መጠመድ ያልነበረባቸው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ለማንኛውም ተጠብሶ መጥቶልኝ በላሁት፡፡

ሂሣብ 12 ብር መሆኑ ተነገረኝ፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ የዓሣ ምንጭ ነው በሚባልበት ከተማ ይህን ያልህ የተጋነነ ዋጋ እንዴት ሊጠየቅ ይችላል?

ከሁሉም በላይ የሚገርመው ደግሞ ሐይቁን በምጎበኝበት ጊዜ የከተማው ባለሆቴሎች አንዱን ዓሣ በአንዳንድ ብር ሲገዙ በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ፡፡ ትንንሹን ደግሞ አምሣ ሣንቲም ገዝተው በጋሪ አስጭነው ሆቴላቸው አስገብተዋል፡፡ በዚህ ዋጋ የተገዛውን ዓሣ ጠብሰው ሲሸጡት አስራ ሁለት ብር ይጠይቁበታል ብዬ ፈፅሞ ፈፅሞ አልጠበቅሁም ነበር፡፡ ነገር ግን ሆነ፡፡ ይህ ዋጋ አዲስ አበባ ላይ ቢሆን ብዙ ላይገርም ይችል ይሆናል፡፡

እንዲህ ዓይነት ለሸማቹ ወይም ለተጠቃሚው የሚያስቡ ስላሉ ምክርም ተግሳጽ ቢሰጣቸው ጥሩ ነው፡፡


በናታን ዳዊት

 
< Prev   Next >