Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Wednesday
Aug 20th
Home arrow Sections arrow የቀድሞ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ...
የቀድሞ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ... Print E-mail
Wednesday, 09 April 2008
Image
አቶ ኃይላይ
የቀድሞ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እድሳት በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቃል

የአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት የዓመቱ ምርጥ ተባለ


"የ2007 ምርጥ የአፍሪካ ኤርፖርት" በሚል ሰሞኑን ሸልማት የተቀበለው የአዲስ አበባ ኤርፖርት አሮጌ ተርሚናል ለማሻሻል የተያዘው ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ታህሳስ ወር እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ፡፡

በ72 ሚሊዮን ብር ወጪ የሲቪል እና የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታውን በማከናወን ዓለም አቀፍ በረራ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም እየገነባ መሆኑን፣ ፕሮጀክቱ በጁላይ 2007 ሥራ መጀመሩን፣ ከኮንትራቱ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይላይ ገ/ፃዲቅ ገልፀዋል፡፡

የሲቪል ሥራውን ራማ የተባለ የኮንስትራክሽን ድርጅት በ32 ሚሊዮን ብር ተረክቦ እያከናወነ መሆኑን የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራውን ለማከናወን ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ አንድ የአሜሪካን ኩባንያ መመረጡን አቶ ነጋ ወንድሙ በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የእቅድና ማርኬት ዴቭሎፕመንት ማስተባበሪያ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ግንባታ ኤርፖርቱ አሁን ካለው አምስት ወደ አውሮፕላን መሸጋገሪያ ድልድዮች በተጨማሪ በአሮጌው ተርሚናል አራት አዳዲስ መሸጋገሪያ ድልድዮች ይሰራሉ፡፡

በተያያዘም ኤርፖርቶች ድርጅት የመቀሌን አሉላ አባነጋ እና የባሕርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርቶች ወደዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሸጋገር የጀመረውን ሥራ በቀጣይ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ አቶ ነጋ ገልፀዋል፡፡

ሁለቱ ኤርፖርቶች ያሉበትን ደረጃ የሚያጠና ከኢሚግሬሽን፣ ከአየር መንገድ፣ ከኳረንቲን፣ ከጉምሩክ፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከደህንነት መ/ቤቶች የተውጣጡ አባላት በቅርቡ በየኤርፖርቶቹ ተዘዋውረው መመልከታቸውን ያስታወሱት አቶ ነጋ በተለይ በባሕር ዳር ኤርፖርት ይጎድላሉ የተባሉ ዓለም አቀፍ በረራውን ለማስጀመር የሚያስችሉ ሥራዎች በፍጥነት እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የ2007 የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ኤርፖርት ሆኖ በመመረጥ ሰሞኑን መሸለሙን አቶ ኃይላይ አስታውቀዋል፡፡

ኤርፖርቱ ለሽልማት ሊበቃ የቻለው የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ በመሆኑ፣ ከዓመት ዓመት የተስተናጋጅ ቁጥር እያደገ በመምጣቱ፣ መስተንግዶ ጥሩ በመሆኑ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኤርፖርቱ የታዩ ልማቶች ከግምት ውስጥ ገብተው መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

በፍሬው አበበ
 
< Prev   Next >