Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የዓለማችን ረጅሙ ሊፍት በጃፓን ተሠራ
የዓለማችን ረጅሙ ሊፍት በጃፓን ተሠራ Print E-mail
Wednesday, 09 January 2008
የጃፓኑ ሚትሱቢሽ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን የዓለማችንን ረጅሙን ሊፍት መሥራቱን ቢቢሲ አስታውቋል፡፡

በጃፓኗ አናዛዋ ከተማ የተሠራው ሊፍት /ሶሌ/ የተሰኘ ሲሆን 173 ሜትር ወይም 567 ጫማ ከፍታ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ካምፓኒው እንደገለፀው የሊፍት ፍጥነትን ለማጥናትና ታላላቅ ህንፃዎች እንዴት ሆነው መሠራት እንደሚገባቸው ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ይረዳል ብሏል፡፡

ለኬብል፣ ለመዘውሮችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ጨምሮ ሚትሱቢሽ ለጥናት ከ5 ቢሊዮን የጃፓን የን /50 ሚሊዮን ዶላር/ ወጭ እንደመደበ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የተለያዩ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች እየተገነቡ መሆናቸውን የገለፀው ቢቢሲ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የረጅምነት ክብረ ወሰን ይዞ የነበረው የታይፒው ህንፃ ባለ 101  508 ሜትር ከፍታ ያለው ቢሆንም በዱባይ፣ በሻንጋይ፣ በሞስኮና በችካጐ በሚሠሩ ፎቆች ሊበለጥ ይችላል ብሏል፡፡

በቶሺባ ኢሊቬተር ኤንድ ቢዩልዲንግ ሲስተም የተሠራው የታይፒ ባለ 101 ሊፍት በሰከንድ 17 ሜትር ፍጥነት በመሄድ በዓለም ፈጣኑ ሊፍት እንደሆነ የጠቆመው ዘገባው የጃፓኑ ሶሊ የሊፍት ቴክኖሎጂውን ለማሳደግ ይረዳል ብሏል፡፡

 
< Prev   Next >