| ያለፈውን ምርጫ፡- |
|
|
| Wednesday, 09 April 2008 | |
|
ጠንካራ ጎን እናጠናክር፤ ደካማ ጎን እናስወግድ!
በአንድ አገር የምርጫ ታሪክ ልዩ ትኩረትና ክብደት ሊሰጠው የሚገባ በምርጫው ማን አሸነፈ የሚለው ሳይሆን ምርጫው እንዴት ተካሄደ እንዴት ተከናወነ የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም የምርጫ ሂደት የሥርዓት ነፀብራቅ ሲሆን አሸናፊ ፓርቲ ግን በየጊዜው ሊቀያየር ይችላል፡፡ የምርጫ ሥርዓት ዘላቂነት ያለው ሲሆን ተመራጭ ፓርቲ ግን የወቅቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ ነፀብራቅ ሊሆን ይችላል፡፡ በአገራችን በኢትዮጵያም መመዘኛችኝ ይኸው ነው፡፡ የምርጫ አካሄዳችን እንዴት ነበር የሚለው ነው፡፡ ያለፈው የ1997 ዓ.ም ምርጫችን ከምርጫው በኋላ ተበላሸ እንጂ የሚያኮራና ዴሞክራሲያዊ ሂደት ነበረው፡፡ ከነግድፈቱም ቢሆን የአገራችንን የምርጫ ታሪክና ሂደት አንድ ትልቅ እርምጃ ወደፊት ተራምዷል፡፡ ያለፈው ምርጫችን ልንማርበት የሚገባና ልናጠናክረውና ልናስወግደው የሚገባ ሁለት ምዕራፎች የያዘ ነበር፡፡ እስከ ምርጫው ዕለት የነበረው ምዕራፍ በዋነኛነት በአዎንታ የሚገለፅ አኩሪ ምዕራፍ ነበር፡፡ በርካታ ፓርቲዎች ለውድድር የተሰለፉበት ከፍተኛ ቅስቀሳ በመላው አገራቱ የተካሄደበት ነበር፡፡ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ሰፊ የክርክር መድረክ ያዘጋጁበትና ያስተላለፉበት ነበር፡፡ በርካታ ሕዝብ ለምርጫ የተመዘገበበትና በከፍተኛ ስነ ሥርዓት እስከሌሊት ድረስ የመረጠበት ነበር፡፡ እጅግ ሰላማዊና ደማቅና አዎንታዊ መንፈስ ያዘለ ምርጫ ነበር፡፡ የመጀመሪያው የምርጫ ውጤት ሲነገር እንኳ ተቃዋሚዎች በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ አሸነፉ የሚል ነበር፡፡ ከላይ የጠቃቀስናቸው በቀላሉ ሊታይና ሊገመት የሚገባው አይደለም፡፡ ልናዳብረው የሚገባ የምርጫ ሂደታችንን ጠንካራ ጎን ነው፡፡ ሆኖም ከምርጫው በኋላ አሉታዊ ተሞክሮዎችም በብዛት ታይተውበታል፡፡ ጥቂቶችን እንጠቃቅስ፡፡ ገና ምርጫው ሳይነገርና ሳይቆጠር ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ አካባቢ ገና ሕዝቡ መረጦ ሳይጨርስም ምርጫው ተጭበርብሯል፣ የሚል አስፈላጊ ያልሆነ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሳያሳውቅ ውጤቱን ተወዳዳሪዎች ገልፀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ንትርክ ተከስቷል፡፡ አብሮ የተወዳደረ የተቃዋሚ ጎራ ተሰነጣጥቋል፡፡ በኢትዮጵያዊያን ከማመን ይልቅ በውጭ ታዛቢዎች ላይ መተማመን ተጀመረ፡፡ የውጭ በተለይም የአውሮፓ ታዛቢዎች ከስነ ሥርዓትና ከስነ ምግባር ውጭ መግለጫ ሰጡ፡፡ እስከ ምርጫው ዝግጅትና ዕለት በጭራሽ ያልታየ የፀጥታና የደህንነት ሃይል ወደ መድረክ መውጣት ጀመረ፡፡ አላስፈላጊና ዘረኛ ቅስቀሳ ሕዝብን መከፋፈል ጀመረ፡፡ ግድያ እስር ሆነ፡፡ ከምርጫ በኋላ የታየው የጠቃቀስነው ሁኔታ በአሉታ የሚጠቀስ በቀጣይ የፓርቲ ሂደት በጭራሽ ሊደገም የማይገባ ነው፡፡ እንግዲያውስ ስለ ቀጣይ ምርጫ ሰታሰብ ጠንካራ ጎንን የሚያጠናክር ደካማ ጎንን የሚያስወግድ ምርጫ መሆን እንዳለበት ማረጋገጥ ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገርም ነፃና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሁኔታ መፍጠርና አሉታዊና እርስ በርስ የሚያጋጭ ዘረኛ ቅስቃሳ ማስወገድ፣ ከዛም ወደ ግድያ፣ እስርና ይቅርታና መፈታት የሚያመራ አላስፈላጊ ነገር ሁሉ ማስወገድ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ የሁሉም ወገን ሃላፊነት ነው፡፡ የገዥው ፓርቲ የተቃዋሚ ፓርቲና የሕዝብ ሃላፊነት ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ በዚህ ምርጫ ያለፈው ስህተት እንዳይደገም ምን ላድረግ? ያለፈውን ጠንካራ ጎን ይበልጥ ለማጎልበት ምን ልስራ? ብሎ ማሰብና ከልብ መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም እንደዚሁ ባለፈው ምርጫ ምን ፈፀምን? ምን ስህተት ነበረብን? ምን ልናስወግደው የሚገባ ነገር አለ? ብለው ራሳቸውን መገምገም ይኖርባቸዋል፡፡ ተስተካክለው ሊቀርቡ ይገባል፡፡ ሕዝብም ቢሆን ሁሉም ነገር ለእነሱ መተው የለበትም፡፡ ሕዝብ ራሱ የሚጠቀመውን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ በትክክል ሊያይና ሊከታተል ይገባል፡፡ አዎንታዊ ቅስቀሳ እንደ አሉታዊ ቅስቀሳ እንዳይቀበል በውል ማሳወቅና ግልፅ መልዕክት ለፓርቲዎች ሊያስተላልፍ ይገባል፡፡ የማሟያ ምርጫ ለማካሄድ በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡፡ ለአዲስ አበባ ምክር ቤትም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ምርጫ እያካሄድን ነው፡፡ ለአዲስ አበባ በሙሉና ለተወካዮች ምክር ቤት በጎደሉት፡፡ ይህ የምርጫ ሂደት ተጨማሪ አዎንታዊ ተሞክሮ የምንሰንቅበት መድረክ አድርገን ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ በዚህ ተሞክሮ ለቀጣይ ዋና ምርጫ የተጠናከረ ዝግጅት የምናደርግበት ይሆናል፡፡ በዚህ የማሟያ ምርጫ ባለፈው ምርጫ ያገኘናቸው አዎንታዊ ተሞክሮዎች አጠናክረን አሉታዊ ተሞክሮዎችን አስወግደን የተሻለ የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የተሻለ ፓርላማ ይዘን የምንጓዝበት መሆን ይገባናል፡፡ በዚህ የማሟያ ምርጫ የምንጠብቀው አንድ ዓብይ እርምጃ የተገኘውን ውጤት ማንኛውም ወገን በደስታ አሜን ብሎ እንዲቀበለው ነው፡፡ ምርጫና ሁከት አብሮ ይሄዳሉ የሚል በአፍሪካ እየተያ ያለው ገፅታ መቀየር አለብን፡፡ በአፍሪካም ምርጫን በደስታ መቀበል ተጀምሩዋል፤ የሚል መልዕክት ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ ይህንና ይህን ስናደርግ ነው ያለፈው ምርጫ አዎንታዊ ገፅታ አጎልብተን ደካማ ገፅታውን ወደ አዎንታዊ ተሞክሮ ልንለውጠው የምንችለው፡፡ ከተሞክሮ ውጭ ልንጠቀም የምንችለው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
ኢንቨስተሮችን ለመሳብ እንረባረብ!
በእንስሳት ማድለብ ሥራ 1ዐ ሚሊዮን ብር ትርፍ ተገኘ
በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ስምንት ወረዳዎች በእንስሳት ማድለብ ሥራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች አስር ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘታቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የሆላንድ ካርን ድርሻ ለመግዛት...
"ካለን ውስን የሰው ኃይል፣ ፋይናንስና...
(ሚኒስትር መሥሪያ ቤት በኃላፊነት እንዲያሳካ የተሰጠውን ፕሮጀክት የሚገመግም ከአገር ውስጥና ከውጭ የተውጣጣ የኤክስፐርቶች ቡድን ክቡር ሚኒስትሩ መሥሪያ ቤት ድረስ መጥቷል፡፡ እሳቸውም ከባለሙያዎቻቸው ጋር ናቸው፤ ስብሰባው ተጀምሯል)
ጀግኖቻችንን ለማክበር
በሔኖክ ያሬድ
በኢትዮጵያ ከስም የዋለ ተግባር ያከናወኑ ምርጥ ሰዎች መኖራቸው፣ ማለፋቸው የተመዘገበ ነው፡፡ በጀግንነትም ይጠቀሳሉ፡፡ ከሰብዓዊ ጥናት በተለይም በኪነ ጥበባት ዘርፍ አንቱ የተባሉ ኢትዮጵያውያን የመኖራቸውን ያህል በጦር ውሎ የተወደሱት ጀግኖች ያህል ክብር የተሰጣቸው ምን ያህል እንደሆኑ እምብዛም አይታወቅም፡፡
"ጃንጥላና ሹራብ ሰሪ ክረምት ይወዳል"
በምህረት አስቻለው
መርካቶ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ከሚገኝ አንድ የልብስ ሱቅ ደጃፍ ላይ የተበላሹ ጃንጥላዎችን ሲጠግኑ አገኘኋቸው፡፡ አቶ አራርሳ ሔርጶ ለሃያ ዓመታት በእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ ውስጥ በጥበቃነት፣ በአደጋ ተከላካይነት እንደሰሩ ይናገራሉ፡፡ አሁንም በሰራተኛ ልሸፍት ኃላፊነት እዚያው እሳት አደጋ ውስጥ በመስራት ላይ ናቸው፡፡
የምግብና የነዳጅ ፍላጎት መጨመር...
የምግብና የነዳጅ ፍላጎት መጨመር ደንን እያወደመ ነው
የምግብና የነዳጅ ሰብሎችን ማምረት እንዲሁም የእንጨት ፍላጎት መጨመር የደን መጥፋትን ያስከትላል ሲል የ"ዘ ራይትስ ኤንድ ሪሶርስስ ኢንሽየቲቭ" ሪፖርት አስጠንቅቋል፡፡
በትውልድ አገራቸው በልማት...
የወጣቶቹ ፍሬ
በጋዜጣው ሪፖርተር
የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን እንዲመጡ ማበረታቻዎች መኖር አለባቸው፡፡ አገሪቱ የፈጠራ ሥራን ካበረታታችና ከደገፈች አገሪቱን የሚጠቅሙ በርካታ የፈጠራ ባለሙያዎች ይመጣሉ፡፡ ለፈጠራ ባለቤትነት ወይም እውቅና የማይሰጥባቸው ዘርፎችም ብልሃት ሊፈለግላቸው ይገባል፡፡ በኮምፕዩተር ዘርፍ እውቅና የሚሰጠው ማን ነው? ሣይንስና ቴክኖሎጂ አቅምና ብቃቱ የለውም ወይ ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በፈጠራ ባለሙያዎች ዘንድ ሌላው የሚነሳው ለፈጠራ ባለቤትነት ክፍያ መፈፀሙ ተገቢ አለመሆኑን ነው፡፡ ይህንን ክፍያ መክፈል ባለመቻል ፈጣሪዎችና ፈጠራቸው ተዳፍነው ይቀራሉ የሚል ቅሬታ አለ፡፡
በሪሁን ተሻለ
የአገራችንን የሥራ ፈላጊዎች፣ ሥራ አጦችን፣ ሥራ ፈላጊዎችን፣ ሥራ ላይ ሆነው፣ ሥራ እያላቸው የተሻለ ሥራ የሚያፈላልጉትን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ በሚገኝ ከፍተኛ ሥራ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ ያሉትን ጭምር ሲበዛ ሊያሰገርም ሊያስደንቅ የሚችል አንድ "የሥራ ማስታወቂያ" ያየሁት በአሜሪካው የዋይት ሀውስ ዌብ ሳይት (ድረ ገጽ) ላይ ነው፡፡ ከ115 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የሚደረገው የአሜሪካ የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ከስልጣን የሚሰናበተውና የሚተካውን ግለሰብ/ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ፓርቲውንም ጭምር አብሮን ከእኛ ጋር የሚያውቀው የቡህ ቸኒ አስተዳደር ይህንን የሥራ ማስታወቂያ ወይም የከፍተኛ ሹመት ማመልከቻ ጥሪ በዋይት ሀውስ ድረ ገጽ ላይ የለጠፈው ሥልጣን ከያዘበት ከስምንት ዓመት ወዲህ ጀምሮ ነው፡፡ ዛሬም አሁንም አለ፡፡
፣የዓመቱ ምርጥ የፈጠራ ሴት፣
በምህረት አስቻለው
"መንገድ ላይም ይሁን በማንኛውም ቦታ የሰዎችን አለባበስ በትኩረት እመለከታለሁ፡፡ እዚህ ጋር እንዲህ፣ ቀለሙ የዚህ ዓይነት ቢሆን ብዬ አስባለሁ፡፡ የማውቀው ሰው ከሆነ ደግሞ አስተያየት እሰጣለሁ፡፡ ማንኛውም ሰው በሄደበት ሁሉ ከሙያው ጋር የሚገናኙ ነገሮችን ማስተዋሉ አይቀርም፡፡ የምገዛቸው ልብሶችንም ቢሆን በምፈልገው መንገድ አስተካክላቸዋለሁ" ትላለች ፣የዓመቱ ምርጥ የፈጠራ ሴት፣ ተብላ ሽልማት ማግኘት የቻለችው የልብስ ዲዛይነር፡፡
ለኦዲዮ ቪዥዋል ሥራ ኘሮዲውሰሩ ማን ነው?
ግሪኮች ለፍቅር ሦስት ዓይነት ስያሜ ሲሰጡት ሮማውያንም እንዲሁ በሦስት ይከፍሉታል፡፡ በግሪክ የመጀመሪያው ዓይነት ፍቅር "ኤሮስ" የሚሉት ሲሆን ይኸውም ከፍትወት ፍቅር ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ሁለተኛው ዓይነት ፍቅር ደግሞ "ፊሎ" ይሉታል፡፡ ይኸ ደግሞ እንደ ፊሎዞፊ የራሱ የሆነ ሥነ ቃል ሲሆን ይኸውም የሰው ልጅ ፍቅር ወይም የጥበብ ፍቅር ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ ሦስተኛው ዓይነት ፍቅር "አጋፔ" የሚሉት ነው፡፡ ይኸ ዓይነቱ ፍቅር ለአምላክ የሚኖርን ፍቅር በቀጥታ የሚመለከት ነው፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር
ሸመቱና ጓደኛዋ ስራነሽ ለማንም የማይነግሩትና ለሁለት ዓመታት በጋራ የያዙት ሚስጢር አላቸው፡፡ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው መኖሩንና የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት መውሰድ ከጀመሩ ሁለት ዓመታት ማሳለፋቸውን ለማንም ለመንገር አይደፍሩም፡፡
"ከፖሊሲው በተቃራኒ ፌዴሬሽኖችን...
"ከፖሊሲው በተቃራኒ ፌዴሬሽኖችን ወደ አንድ ዕዝ ለመመለስ ይመስላል"
አቶ ተስፋዬ ሽፈራው የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት
የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ከአትሌቲክስና ቦክስ ፌዴሬሽኖች ቀጥሎ በኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ ኢትዮጵያን የሜዳሊያ ባለቤት አድርጓል፡፡ ይሁንና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት በምንም መመዘኛ እውቅና ለሌለው ማርሻል አርት ለሚባል ፌዴሬሽን ሙሉ ጽ/ቤቱ እንደተሰጠበትና ያለ ቢሮ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ሽፈራው ይገልፃሉ፡፡ አነጋግረናቸዋል፡፡
እስራኤል በኢራን ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ገለፀለች
በጋዜጣው ሪፖርተር
እስራኤል ጥቃት ይደርስብኛል የሚል ስጋት ካደረባት በኢራን ላይ እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀች መሆኗን መከላከያ ሚኒስትሩ ገለፁ፡፡
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |
Share your thought and ideas with others on our public forum. Just register here and participate on our new and improved forum. Note that all members of the old version forum have to register again to post on the new version forum.