| አጣጥሞ ያለመጓዝ ችግር |
|
|
| Wednesday, 09 April 2008 | |
|
ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ችግር ሆኖ የቆየው ሀገራዊና ብሔረሰባዊ ማንነትን አጣጥሞ መጓዝ አለመቻል ነው፡፡ ያለፉት መንግሥታት ብሔረሰባዊ ማንነትን ወደ ጐን ትተው፣ ኢትዮጵያ የአንድ ብሔር፣ የአንድ ቋንቋ፣ የአንድ ባህል፣ የአንድ ሃይማኖትና የአንድ አመለካከት አገር እንደሆነች በማስመሰል ለማስተዳደር ሞክሩ፡፡ የተሳካላቸው አይመስለኝም፡፡
ኢሕአዴግ ያለፉት መንግሥታት ቦታ ያልሰጡትን የብሔር ጥያቄ ተመለከተው፡፡ ለብሔር ጥያቄ ቦታ ሲሰጠው፣ ለሀገራዊ ማንነት ግን ቦታ ነፈገው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ "አንተ የዚህ ብሔር ተወላጅ ነህ፤ አንተ የዚህ ብሔር ተወላጅ ነህ" መባባል እስከማይችልበት ደረጃ ድረስ እርስ በርሱ በጋብቻና በማኀበራዊ ኑሮ የተሳሰረ ነው፡፡ አሁን ግን እርስ በርሱ የተሳሰረው ሕዝብ በዘር ተለያየ፡፡ የአንድ ብሔር ተወላጅ ሌላ ክልል ሄዶ መኖር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ አንድ ክልል ሄዶ ለመኖር ቋንቋ መስፈርት ሆነ፡፡ ሰው በገዛ ሀገሩ እንደ ዜጋ ሳይሆን እንደ ባዕድ ተቆጠረ፡፡ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ጠፋ፡፡ ያለፉት መንግሥታትም ሆኑ የኢህአዴግ መንግሥት ትልቁ ችግራቸው ጽንፈኝነት ነው፡፡ የአንድ አመለካከት አክራሪ ደጋፊ ወይም አክራሪ ተቃዋሚ መሆን ነው፡፡ ያለፉት መንግሥታት ለአገራዊ ማንነት ትልቅ ቦታ ሲሰጡ፣ ኢሕአዴግ ግን ለብሔረሰባዊ ማንነት ትልቅ ቦታ ሰጠ፡፡ ሀገራዊ ማንነትና ብሔረሰባዊ ማንነት ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጓት የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ አንዱን ብቻ ነጥሎ መከተል ግን በአንድ ክንፍ ለመብረር እንደመሞከር ይቆጠራል፡፡ (ግርማ ሰይፉ፣ ከልደታ ክፍለ ከተማ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |