Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Wednesday
Aug 20th
Home arrow Sections arrow የአፍሪካና የአውሮፓ የንግድ...
የአፍሪካና የአውሮፓ የንግድ... Print E-mail
Wednesday, 09 April 2008
የአፍሪካና የአውሮፓ የንግድ ስምምነት እክል ገጠመው

በአፍሪካና በአውሮፓ አገሮች መካከል የታሰበው አጠቃላይ የንግድ ስምምነት ያልተጠበቁ አጋጣሚዎች እያራዘሙት ሲሆን የአፍሪካ የገንዘብና የንግድ ሚኒስትሮች በሽግግር ወቅት በሚኖረው ስምምነት እንዲስተካከል ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ቢዝነስ ዴይሊ የተሰኘው የኬንያ ጋዜጣ እንደዘገበው በኢኮኖሚ ስምምነቱ አገራቸውን ለመመራት የሚያስችላቸውን አቅም ያሳጣናል በሚል አንዳንድ አገሮች ስምምነቱ ከመቀጠሉ በፊት እንዲቀየር ወስነዋል፡፡

የአፍሪካ የገንዘብና የንግድ ሚኒስተሮች ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ባደረጉት ስብሰባ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ የንግድ እንቅስቃሴውን ነፃ ማድረግ ከአገራቱ ተጨባጭ የሆነ የልማት ስትራቴጂ በተቃራነ በኩል ከተጓዘ የልማት አጀንዳ ላይ ጫና እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

እስከ ጥር 31 ቀን 2007 በነበረው ስምምነት ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ስምምነቱን ከመፈረም ቢቆጠቡም ኬንያ የሽግግር ስምምነቱን በመፈረም ከአለም የንግድ ድርጅት መስፈርት አንፃር በገበያዋ ላይ ያለውን የንግድ እገዳዎችን ማንሳቷ ተጠቁሟል፡፡

የአፍሪካ ካረቢያንና ፓስፊል አገሮች (አካፓ) ምርቶቻቸውን በአውሮፓ ገበያ ከቀረጥና ኮታ የሚያስገቡበት እድል ለ25 ዓመታት ቢቆይም የንግድ ሕጉ ከአለም የንግድ ድርጅት ስምምነት ጋር ተጣጥሞ እንዲጓዝ ለማስቻል በአዲስ ስምምነት መተካቱ ይታወቃል፡፡

የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስፈልገው የሽግግር ስምምነት አብዛኛውን ኅብረተሰብ የሚያስማማ የኢኮኖሚ ውሳኔና አገርን የመምራት አቅማቸውን ለመጠበት ማራዘማቸውን ተናግረዋል፡፡

ለእነሱ በሽግግር ስምምነቱ ዋነኛ አጀነዳ የሆነው በልማትና ልዩ ሁኔታ መግባባት የተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ በሚያተኩረውና ለአገራቱ የተለየ ድጋፍ በሚያደርገው የስምምነት አካል ላይ ነው፡፡

ለአገራት የተለየ ድጋፍን የሚያመለክተው የስምምነት አካል አገራት የንግድ አጋሮቻቸው በሆኑ አገራት መካከል አንድ ምርት ላይ ብቻ የጉምሩክ ቀረጥን በመቀነስ ልዩነት እንዳይፈጥሩ የሚከለክል የስምምነቱ አካል መኖሩን የአለም ንግድ ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡

እንደዚህ አይነት ልዩ ድጋፍ የሚደረግ ከሆነ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለሆኑ አገራት ሁሉ ተፈፃሚ መሆን አለበት፡፡

"የሽግግር ስምምነቱ የተወሰኑ ነጥቦችን የያዘ ሲሆን፣ በአገራት የተለየ ድጋፍን የሚመለከተው የስምምነቱ አካል፡ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ድጎማና የአፍሪካ አገራት የፖሊሲ ነፃነትን የሚጋፋው የስምምነት አካል ይገኝበታል"

የታሪፍ መቀነስ ለአውሮፓ ኅብረት ጥቅም የለውም በተለይ ለኢንዱስትሪ ምርቶቻቸው በተቃራኒው ደግሞ ታሪፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለብዙዎቹ የአፍሪካ አገራት የገቢ ምንጭ ነው፡፡ በተጨማሪም ለእድገታቸውን ትልቅ አስተዋጽኦ አለው" ብለዋል፡፡

ባለፈው ወር የአፍሪካ አገራት ከታሪፊ መቀነስ ስምምነትና ከገበያ የማግኘት ሁኔታ ይልቅ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሲከራከሩ የነበረው በዋናነት በኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት የሽግግር ጊዜ ለልማት የሚደረግን እገዛ በተመለከተ ነበር፡፡

ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ በተደረገው ስብሰባ ከድሃ አገራት የተወከሉ ተሳታፊዎች እንዳሉት የበጀት ድጋፍ ፕሮግራሙ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለማሳደግ አልረዳቸውም፡፡ ይህም አዲሱን የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት ለመፈረም እንዳይችሉ አድርጓቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ብራሰልስ ላይ በተካሄደው ስብሰባም እነዚህ ተሳታፊዎች በጀት ካልተሰጣቸው ስምምነቱን እንደማይፈፅሙ ገልፀው ነበር፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >