| በግብፅ የተቃዋሚ ቡድን ከምርጫ ራሱን ሊያገል ነው< |
|
|
| Wednesday, 09 April 2008 | |
|
የግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን በሀገሪቱ በሚደረገው የአካባቢ ምርጫ ውድድር እራሱን ሊያገል እንደሚችል ማስታወቁን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡
የቡድኑ አባላት በሀገሪቱ መንግሥት ወከባና እስራት እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለፅ፤ “መንግሥት ኢፍትሀዊ አመራር ተያይዟል” ሲሉ የቡድኑ ምክትል ሊቀመንበር መሀመድ ሀቢብ ወቅሰዋል፡፡ ምክትል ሊቀመንበሩ መንግሥት የተቃዋሚ ቡድን እጩ ተወዳዳሪዎች እንዳይመዘገቡ ዘመቻ መክፈቱን አስታውቋል፡፡ የኘሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ ናሽናል ዴሞክራቲክ ፓርቲ በሀገሪቱ ለውድድር በቀረበው ሀምሳ ሁለት ሺ መቀመጫ እጩዎችን ያዘጋጀ ሲሆን ከዘጠና በመቶ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ያለተወዳዳሪ ቀርቧል፡፡ ከስምንት መቶ በላይ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላት በቅርቡ መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ያለፈው ዓመት በተደረገው የፓርላማ ምርጫ ውድድር ሀያ በመቶ መቀመጫ ያሸነፈው የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን በአሁኑ ውድድር ተፎካካሪ እንዳይሆን መንግሥት ጫና መፍጠሩን የውጭ ታዛቢዎች አብራርተዋል፡፡ የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር የሺአት ሚሊሻዎችን አስጠነቀቁ የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር የሺአት ሙስሊሞች መሪ ሙክታድ አል ሳዳር ያደራጁትን የሚሊሻ ኃይል ኢንዲበትኑ ወይም ከፖለቲካ እንቅስቃሴ እራሳቸውን እንዲያገልሉ ማስጠንቀቃቸውን አሶሲየትድ ኘሬስ ከባግዳድ ያሰራጨው ዘገባ አመለከተ፡፡ የሺአት ተጣቂዎች መሪ በበኩላቸው መንግሥት ተቃዋሚዎችን ከምርጫ ውድድር ለማግለል እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ኢ-ህገመንግሥታዊ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በሌላ ዜና የአሜሪካ ባለሥልጣናት የአሜሪካ ወታደሮች ኢራቅን ለቀው የሚወጡበትን መንገድ በተመለከተ ውይይት እያካሄዱ መሆኑ ታውቋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረንስ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ተዘግቧል፡፡ በተያያዘ ዜና በኢራቅ የተገደሉ የአሜሪካ ወታደሮች ቁጥር አራት ሺ ሀያ መድረሱ ታውቋል፡፡ ሙክታር አልሳዳር ዛሬ በባግዳድ አሜሪካ ኢራቅን በመውረር ባግዳድን የተቆጣጠረችበትን አምስተኛ ዓመት አስመልክቶ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያካሂዱ ተነግሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑሪ አልማሊኪ ያለፈው እሁድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአልሳዳር ተከታዮች “በኢራቅ የሚያደርጉትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ካላቆሙ በስተቀር በኢራቅ ፖለቲካም ሆነ የምርጫ ውድድር አይሳተፉም” ብለዋል፡፡ አልሳዳር በበኩላቸው “ምርጫውን በተመለከተ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መወሰን አይችሉም” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ጃክ ሮግ የቲቤት ውዝግብ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲፈታ አሳሰቡ የዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ኘሬዚደንት ጃክ ሮግ በቲቤት መነኮሳትና በቻይና መንግሥት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ በሠላም እንዲፈታ ጥሪ ማቅረባቸውን ቢቢቢ ዘገበ፡፡ ሮግ “አፋጣኝና ሰላማዊ መፍትሔ ለቲቤት ያስፈልጋል” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ኘሬዚዳንቱ የኦሎምፒክ ውድድሩን ለማስተጓጐል የሚደረገው አመፅ ከኦሎምፒክ እሴት ጋር የማይጣጣም መሆኑን በመጥቀስ አመፅ አስፈላጊ አለመሆኑን አብራርተዋል፡፡ የቤጂንግ ኦሎምፒክ ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ቃል አቀባይ ሰንዌዴ በቲቤት እየተካሄደ ያለው አመፅ በጥቂት የቲቤት ተገንጣይ ቡድኖች የሚመራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የቲቤት አማፅያን በበኩላቸው መንግሥት በቲቤት የሰብአዊ መብት ህግጋትን እንደማያከብር በመጥቀስ የቻይና መንግሥት አምባገነናዊ አስተዳደር በአካባቢው ማስፈኑን አስታውቀዋል፡፡ በቲቤት በተቀሰቀሰው የአመፅ ትዕይንት ከሀያ አራት በላይ ሰዎች በፖሊስ መገደላቸውን የቲቤት ነዋሪዎች ሲገልፁ መንግሥት በበኩሉ አሥራ ዘጠኝ ሰዎች በግጭቱ መሞታቸውን አስታውቋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |