Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Monday
Oct 13th
Home arrow Sections arrow ያልተገባ ድርጊት
ያልተገባ ድርጊት E-mail
Wednesday, 09 January 2008
ታህሳስ 20 ቀን 2000 ዓ.ም በ..እኔ የምለው.. ገጽ በፓትርያሪኩ ..ያልተገባ ድርጊት.. ዙሪያ የቀረበውን ጽሁፍ አንብቤ እኔም የራሴን ማለት እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡

ፓትሪያሪካችን በየጊዜው በእንዲህ ዓይነት ያልተገባ ድርጊት ላይ መሰማራታቸው የራሳቸው ጊዜያዊና ዘለቄታዊ ባህሪይ ብቻ አይመስለኝም፡፡ አጠገባቸው ያሉ አማካሪዎቻቸውና የቤተክህነት ሰዎች እንዲሁም እኛ (ማኅበረ ምዕመናን) እጃችን አለበት፡፡ አጠገባቸው ያሉ አማካሪዎቻቸውና የቤተክህነት ሰዎች ተጠያቂ ናቸው፡፡

በፓትርያሪኩ አጠገብና ዙሪያ ያሉ ሰዎች በእርሳቸው መንፈሳዊ አባትነት እየተመራ ያለው ማኅበረ ምዕመናን ምን አይነት መንፈሳዊ ግልጋሎት እየተሰጠው እንዳለና በመንፈሳዊ አባትነታቸው ሊፈቱለት የሚገቡ ችግሮችንና አጠቃላይ ሁኔታዎችን እንዳያዩ አድርጓቸዋል፡፡ ለዚህም አብነት የሚሆኑን ጽሁፎችን ይዞ በሚወጣው የቤተክርስቲያኗ ልሳን የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና የቅኔ ባለሙያዎች የሚቀርብላቸው ውዳሴና ቅኔ (ሙገሳና ውዳሴ ከንቱ የበዛበት) ማንበብና መመልከት ይበቃል፡፡

በእነዚህ መልካምነታቸውና የተጋነነ ሙገሳ ብቻ የሚቀርብላቸውን የሚሰሙትና የሚያነቡት ቅዱስ ፓትሪያሪካችን ፎቶአቸውን በትላልቅ አድባራት እያስለጠፉ ..ሕዝቡ ስለሚወደኝ ነው፡፡ ምንም ችግር የለም፡፡ ይገባኛል.. ነው የሚሉት፡፡

ለፓትርያሪካችን የማሳስበው እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጥታ ከሕዝቡ (ከምዕመናኑ) ጋር የሚገናኙበትን መንገድ ይፈልጉና ትክክለኛውን የሕዝብ አመለካከት ይረዱ፡፡ ለችግሮች ትክክለኛውን መፍትሄ ይስጡ፡፡ ዳግመኛ እንዲህ አይነት ክፍተት በመሪና በተመሪ መሃል እንዳይፈጠርም የተሻለ አስተዳደራዊ መዋቅር ይበጅ፡፡

(ኃይለ ገብርኤል፣ ከአማኑኤል)

 
< Prev   Next >