| አዲስ ሶላር ሲስተም ተገኘ |
|
|
| Wednesday, 09 April 2008 | |
ከምንኖርባት ዓለም ጋር ተመሳሳይ የሆነ አዲስ ሶላር ሲስተም ማግኘታቸውን የስነ ጠፈር ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡አዲስ የተገኘው ሶላር ሲስተም ከጁፒተርና ሳተርን ጋር ቅርበት ያላቸውና የፀሐይን ግማሽ የሚያክሉ ሁለት ፕላኔቶችን የያዘ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በእንግሊዝ የአንድሪው ዩኒቨርሲቲ መምህርና የስነጠፈር ተመራማሪ የሆኑት ማርቲን ዶሚኒክ “ሁለት ፕላኔቶች ያሏት ዓለም አግኝተናል፡፡ ፕላኔቶቹ በእኛ ዓለም የጁፒተር እና ሳተርን ፕላኔቶች የሚጫወቱትን ሚና የሚጫወቱ ሲሆን እንደ ምድር ህይወት ያላቸው ነገሮች ሊኖሩባቸው እንደሚችሉ እንገምታለን ብለዋል፡፡ ዶ/ር ዶሚኒክ ለቢቢሲ እንዳስታወቁት ሶላር ሲስተሙ የተፈጠረው ከዓለማችን ጋር ተመሳሳይ በሆነ ወቅት ሳይሆን እንደማይቀር ነው፡፡ ይህ እውነት ከሆነው ካለንበት ሶላር ሲስተም፤ በህዋ ላይ የተለየና ብቸኛ ህይወት ያላቸው ነገሮች መኖሪያ ሊሆን እንደማይችል ገልፀው ከምንኖርባት ዓለም ጋር ተመሰሳይ የሆኑ ሌሎች ሲስተሞች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ በሃይድሮጅን ጋዝ የሚሰራው አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ የሃይድሮጅን ጋዝን በመጠቀም የሚሰራው አውሮፕላን ሙከራ ተደርጎለት ያለምንም ችግር ሰማይ ላይ መንሳፈፍ መቻሉ ታወቀ፡፡ አነስተኛ መጠን ያለውና በቦይንግ አቪየሽን ሦስት የሥራ ባልደረቦች የተሰራው ይኸው አውሮፕላን በደቡባዊ ማድሪድ ሦስት ጊዜ በረራ ተደርጎበታል፡፡ ሃይል የሚያገኘው ከሃይድሮጅን ፊውል ብቻ ነው፡፡ ይህም አዲስ የአውሮፕላን ግኝት እንደሆነ ካምፓኒው ገል"ል፡፡ የቦይንግ ቴክኖሎጂ ዋና ኃላፊ ጆን ትሬሲ እንዳሉት "በሃይድሮጅን የሚሰራው አውሮፕላን መስራቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ትልቅ ታሪካዊ እድገት ነው" የሃይድሮጅን ፊውል ሲል በመጠቀም መብረር የተቻለው አዲስ አውሮፕላን በሰማይ ላይ ቆይታ ያደረገው ለ45 ደቂቃዎች ነበር፡፡ በአውሮፕላኑ ላይ የተደረገው የበረራ ሙከራ የተሳካ ቢሆንም የሃይድሮጅን ፊውል ሲል ብቻውን በአየር ላይ ለሚበሩ ትላልቅ አውሮፕላኖች ሁሉ እንደ ቀዳሚ የሃይል ምንጭ ሆኖ ያገለግላል ማለት እንደማይቻል የቦይንግ ካምፓኒ ኃላፊ አስተውቀዋል፡፡ አክለውም “ሃይድሮጅን ለትላልቅ አውሮፕላኖችም እንደ ሁለተኛ የሃይል ምንጭ ሊያገለግል ይችላል” ብለዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የበረራ ሙከራ የተደረገለት ይኸው አዲስ ግኝት የሆነው አውሮፕላን በረራውን ያካሄደው በፓይለት በመታገዝ አልነበረም፡፡ ሥራ ላይ ቢውል የአየር ብክለት ከመበከል አንፃር አዎንታዊ ለውጥ እንደሚያስከትል የተነገረለትን ይኸን አውሮፕላን ለመስራት ከቦይንግ ውጭ ሌሎች ካምፓኒዎችም ፍላጐት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ የተጎዳ አጥንትን ለመጠገን መቅኒን መቀነስ በአጥንት ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ (መቅኒ) በመቀነስ የተጎዳ አጥንትን ማዳን እንደሚቻል ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡ ጥናቱ እንደሚጠቁመው አጥንቱ መሃል የሚገኘውን መቅኒ ማውጣት የተጎዳው አጥንት ጠንካራ እንዲሆንና በቀላሉ እንዲያገግም ይረዳዋል፡፡ የአጥንት መቅኒ የተጎዳ አጥንትን ሴል የመተካት አቅም ባለው ስቲም ሴል የተሞላ ቢሆንም በአይጦች ላይ የተደረገው ሙከራ እንደሚያሳየው ግን መቅኒው ከወጣ በኋላ አጥንቱን በፍጥነት መጠገን ተችሏል፡፡ በያል ዩኒቨርሲቲ ጥናቱን ያደረጉ ሳይንቲስቶች እንዳሉት ኤክስፐርመንቱ ከባድ የሆኑ እንደ ዳሌ አጥንት መተካት ዓይነት ቀዶ ህክምናዎችን ከማድረግ ያድናል፡፡ በአይጦች ላይ በተደረገው ጥናት አጥንትን መተካት የሚችሉ ሆርሞኖች የተሰጣቸው እና የአጥንት መቅኔያቸው እንዲወጣ የተደረገላቸው አይጦች አጥንታቸው መዳን ቢችልም ተቀንሶ የወጣው መቅኒያቸው ግን አልተተካም፡፡ ምንም የመተኪያ ሆርሞን ያልተሰጣቸው እና መቅኒያቸው የወጣላቸው አይጦች ደግሞ በሳምንት ውስጥ ማገገም ችለዋል፤ መቅኒያቸውም በቦታው እንደተተካ ታውቋል፡፡ ከዚህ ጥናት በመነሳት ሳይንቲስቶች እንዳስታወቁት መቅኒያቸው ወጥቶ የዳኑ አጥንቶች ጥንካሬ ከጤነኛውም አጥንት የተሻለ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት የአጥንት መቅኒ መወገድ በፍጥነት አዲስ አጥንት እንዲተካ ያስችላል፡፡ ቴክኒኩ ለሰዎች ሥራ ላይ ቢውል ውስብስብ የሆነ የቀዶ ህክምና ከማድረግ መርፌን በመጠቀም የአጥንት መቅኒን በቀላሉ በማውጣት የተሻለ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ነው ሳይንትስቶቹ ያስታወቁት፡፡ “ከአጥንት ውስጥ የተወሰነ መጠን መቅኒ ማውጣትም በቂ የሆኑ የደም ሴሎች እንደተፈጠሩ ምክንያት አይሆንም” ብለዋል አጥኝዎቹ፡፡ አጫሽነት ከዘር ይወረሳል በሲጋራ መማረክ ከጅን ጋር ግንኙነት እንዳለው ታወቀ፡፡ በሲጋራ ሱስ መጠመድ በዘር እንደሚወሰንም ሳይንቲስቶች ገልፀዋል፡፡ ሳይንቲስቶች በሲጋራ ሱስ ላይ ብቻ ሳይሆን አጫሽ ሆነው በሳንባ ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ የተወሰኑ ሰዎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡ በሱሱ የመጠቃት እድልን የሚወስነውም ክሮሞዞም 15 እንደሆነ ተለይቷል፡፡ በወቅቱ አጫሽ የሆኑና አጫሽ የነበሩ ግን ያቆሙ ሰዎች የተወለዱ ልጆች ከወላጆቻቸው ክሮሞዞም 15ን ከያንዳንድ ወላጃቸው የወሰዱ በሲጋራ ሱስ የመያዝ እድላቸው ከ70 እስከ 80 በመቶ በሲጋራ ከፍ ይላል፡፡ የሳምባ ካንሰር በዋናነት የሚመጣው በሲጋራ ማጨስ ምክንያት ሲሆን አጫሾች ብቻ ሳይሆኑ ከሚያጨሱ ሰዎች አጠገብ በመሆን ዘወትር የጭሱ ተጋላጭ የሆኑትም በበሽታው የመያዝ እድል አላቸው፡፡ ከአጫሾች ግማሽ ያህሉ ለሞት የሚዳረጉት በሳንባ ካንሰር ወይም ከማጨስ ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎች ነው፡፡ በበሽታው የሚሞቱ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም አሁን ድረስ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ወንዶች ናቸው፡፡ ለደቡብ ኮርያ የመጀመሪያዋ ተመራማሪ ህዋ ላይ ሶዩዝ የተሰኘችው ሮኬት ለደቡብ ኮሪያ የመጀመሪያ የሆነችውን የስነጠፈር ተመራማሪ ይዛ ወደ ዓለም አቀፍ የጠፈር ማዕከል መጥቃለች፡፡ ወደ ህዋ ለመምጠቅ ለሃገሪቷ የመጀመሪያ የሆነችው ዩ ሶዩን እና ሁለት የሩስያ ተመራማሪዎች በረራውን ያደረጉት ትናንትና ከጠዋቱ 2፡16 እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የ29 ዓመት ወጣት የሆነችው ዩ ስዩን ህዋ ላይ ለ10 ቀናት ቆይታ የምታደርግ ሲሆን የተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን እንደምታደርግ ይጠበቃል፡፡ አንድ ደቡብ ኮርያዊ ተመራማሪ ወደ ህዋ ለመውሰድ ለወጣው ማስታወቂያ 36 ሺህ ሰዎች ያመለከቱ ሲሆን ዩ ሶዩን የአመልካቾች ሁሉ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡ ወጣቷ የአስር ቀን ቆይታዋን በተሳካ ሁኔታ ጨርሳ እስከምትመጣ ሃገሯ አጠቃላይ የሚያስፈልጋትን የ20 ሚሊዮን ዶላር ወጭ ሸፍናለች፡፡ ወጣቷ የጠፈር ተመራማሪ አብረዋት ከተጓዙ ሌሎች ተመራማሪዎች ጋር እ.ኤ.አ አፕሪል 19,2008 ወደ ምድር እንደምትመለስ ይጠበቃል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |