| ትልማ ገንዘብ እያሰባሰበ ነው |
|
|
| Wednesday, 09 April 2008 | |
|
ትልማ ምሥራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የእራት ምሽት የሚያዘጋጅ ሲሆን፣ የማህበሩ ደጋፊ ባለሃብቶችና ተቋማት ለማህበሩ ዓላማ መሳካት የበኩላቸውን እንዲለግሱ ጥሪ አስተላለፈ፡፡
ከትላንት ወዲያ የማህበሩ ቅርንጫፍ አዘጋጅ ኮሚቴ በአክሱም ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የያዘውን የሚልንየሙ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለማሳካት ግንቦት 2/2000 ዓ.ም በአክሱም ሆቴል የእራት ምሽት ፕሮግራም ለማድረግ ዝግጅት አጠናቋል፡፡ አለም አቀፍ የትግራይ ልማት ማህበር በ2000 ዓ.ም በያዘው የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም መሰረት ከአባላት፣ ከባለሃብቶች፣ ከግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ከተቋም አባላት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማሰባሰብ አቅዷል፡፡ የምሥራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ብቻውን ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የቅርንጫፍ ማህበሩ ዋ/ፀሐፊና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሰብሳቢ አቶ ተኪኣ ገ/መድህን ገልፀዋል፡፡ የማህበሩ ምሥራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በያዘው የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም የሚያገኘው ገቢ ለትምህርት ቤት መስሪያ የሚውል መሆኑን በመግለጫው ተብራርቷል፡፡ በፕሮግራሙ ሙሉ የእራት ግብዣና የሙዚቃ ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን ለፕሮግራሙ መሳካት ጥሩ አስተዋፅኦ ላደረጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ጊደሮች ለአርሶ አደሮች ተከፋፈሉ በአርሲ ዞን ሐንቆሎ ዋቤ ወረዳ ከፍተኛ የወተት ምርት የሚሰጡና የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው 54 ጊደሮች ለአርሶ አደሮች መከፋፈላቸውን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ወረዳው የእንስሳትን ምርታማነት ለማሳደግ ጊደሮች ሰሞኑን የተሰራጩት በዘጠኝ የገጠር ቀበሌዎች ለሚገኙ 54 ሞዴል ገበሬዎች መሆኑን፣ ሁርቱ፣ ቦረና ከተባለ የጊደሮችና የወተት ፍየሎች ማከፋፈያ ኢንተርፕራይዝ የተገኙት ከፍተኛ የወተት ምርት የሚሰጡ ጊደሮች አርሶ አደሮች የተከፋፈሉት በእጅ በጅ ስያጭ መሆኑን አስታውቋል፡፡ (ኢዜአ) የአየር ፀባይ ተጽዕኖውን ለመቀነስ በጋራ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ከአየር ፀባይ መዛባት ጋር በተያያዘ በሰው ልጆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ እየተጋረጠ ያለው ፈተና መጠነ ሰፊ በመሆኑ ተጽዕኖውን ለመቀነስ የችግሩን መሠረት በመለየት ከፍተኛ የለውጥ ሥራ መስራት እንደሚጠበቅ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የአየር ፀባይ መዛባት ዛሬ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስና የታዩ ጤና መታወክ ምክንያት እየሆነ መምጣቱ፣ የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የተፈጥሮ ሃብት መመናመን፣ ከመኖሪያ ቤትና ከተለያዩ ተቋማት የሚለቀቀው ጋዝ መጨመሩ፣ የኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና ደረጃቸውን ጠብቀው ያለመሰራታቸው የአካባቢ አየርን መበከል በማስከተል ለአየር ፀባይ መዛባት ዋነኛ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |