Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የአበባ ላኪዎች ከልማት ባንክ...
የአበባ ላኪዎች ከልማት ባንክ... Print E-mail
Sunday, 13 April 2008
የአበባ ላኪዎች ከልማት ባንክ የወሰዱትን ብድር ለልማት ባንክ ብቻ እንዲከፍሉ ታዘዙ

የአበባ ላኪዎች (ኤክስፖርተሮች) ከልማት ባንክ የተበደሩትን ገንዘብና ከሽያጭ የሚያገኙትን ገቢ በልማት ባንክ በኩል ብቻ ገቢ እንዲያደርጉ በመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ታዘዙ፡፡ የባንኩ ኘሬዚዳንት ተበዳሪዎች ከልማት ባንክ የወሰዱትን ብድር በራሱ በልማት ባንክ በኩል እንዲከፍሉ ውል ቢገቡም ተግባራዊ ያልተደረገው ለሥራው መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ነው ብለዋል፡፡
 
መንግሥት ለአበባ አምራቾች ማበረታቻ በሚል በልማት ባንክ ለብድር ካስቀመጠው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ኤክስፖርተሮች ሲበደሩ በተበደሩት ባንክ በኩል እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ውል ይገባሉ፡፡ የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ቀደም ሲል የነበረው አስገዳጅ ውል ተግባራዊ እንዲሆን ማዘዙን የገለፁት የሪፖርተር ምንጮች እንዳመለከቱት “ኤክስፖርተሮች ከልማት ባንክ ተበድረው ከውላቸው ውጪ በሌሎች ባንኮች፣ በተለይም በግል ባንኮች በኩል ብድራቸውን ይከፍላሉ፡፡ በዚህም አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም አጥታለች” ብለዋል፡፡

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ባስተላለፈው መምሪያ መሠረት ኤክስፖርተሮች የተበደሩትን ገንዘብ ባበደራቸው ልማት ባንክ በኩል ብቻ ያስገባሉ፡፡ ባንኩም በየወሩ የሥራ ሪፖርቱን ለኤጀንሲው እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡

የልማት ባንክ ኘሬዚደንት አቶ ወንድወሰን ተሾመ ኤጀንሲው መምሪያ ማስተላለፉን አረጋግጠው “ከአሁን በኋላ መመሪያው ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ጥብቅ ቁጥጥርም ይደረጋል” ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል ባንኩ መመሪያውን ተግባር ላይ ያላዋለው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ባለማመቻቸቱ ነው በማለት ተበዳሪዎች በውላቸው መሰረት እዳቸውን በልማት ባንክ በኩል እንዲከፍሉ ያልተደረገበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ለተጠየቁት አቶ ወንድወሰን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከሌሎች ባንኮች በተሻለ ኤክስፖርተሮች የሚከፍሉበት አሰራር መመቻቸቱን አቶ ወንድወሰን አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም አገልግሎቱን ለመስጠት ባንኩ ቅዳሜና እሁድ ጭምር ለደንበኞች ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“አንዳንድ የአበባ ኤክስፖርተሮች የሸጡበትን ገንዘብ መልሰው አገር ውስጥ እንደማያስገቡ ስለተደረሰበት መመሪያውን ተግባራዊ ማድረግ አስፈልጓል” ያሉት ኘሬዚዳንቱ በድርጊቱ አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንዳጣች አመልክተዋል፡፡ በአዲሱ መመሪያ መሰረት አገልግሎት ያገኙ በአሰራሩ መደሰታቸውንም ተናግረዋል፡፡ በየወሩ ለኤጀንሲው ሪፖርት እንደሚቀርብ አስታውቀዋል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >