Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Saturday
Jul 05th
Home arrow Sections arrow መለስ ከሠራተኛ መሪዎች ጋር ይወያያሉ
መለስ ከሠራተኛ መሪዎች ጋር ይወያያሉ Print E-mail
Sunday, 13 April 2008
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሠራተኛውንና የሠራተኛ መሪዎችን እንዲያነጋግሩ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅላቸው የቀረበላቸውን ጥያቄ መቀበላቸው ተገለፀ፡፡ የተፈቀደው የደመወዝ ጭማሪ በአንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ተግባራዊ ሊሆን አለመቻሉ ተጠቆመ፡፡  

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ኘሬዚደንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት በወቅታዊ የሠራተኞች ችግርና በኢንዱስትሪው ዘርፍ መንግሥት የሚከተለውን አቅጣጫና ከሠራተኛው በሚነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ሠራተኛውን እንዲያወያዩ ሃሳቡን ያመነጨውና በደብዳቤ ጥያቄ ያቀረበው ኮንፌዴሬሽኑ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ማወያየታቸውን ያስታወሱት አቶ ካሳሁን ሠራተኛውም ያለበትን ችግር በተመለከተ ከእርሳቸው ጋር መወያየት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ጥያቄው ሊቀርብ መቻሉንም አመልክተዋል፡፡

በጥያቄያችን መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍቃደኝነታቸውን ሙሉ ለሙሉ ስለገለፁልን ውይይቱ የሚካሄድበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንና የውይይቱ ወቅትም ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይከናወናል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

አገሪቱ ከግብርና መር ወደ ወደ ኢንዱስትሪ መር ልማት ስትራቴጂ እየተሸጋገረች ባለችበት ወቅት የሠራተኛው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ከዚህ እድገት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎችና ወደፊትም ምን መደረግ አለበት የሚለውን ጉዳይ ሠራተኞች ማወቅ ስለሚገባቸው በዚህ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መወያየቱ ወቅታዊ ጉዳይ መሆኑንም አቶ ካሳሁን አስረድተዋል፡፡

በተያያዘም ለኑሮ ውድነት መደጐሚያ የሚውል የደመወዝ ጭማሪ እንዲሰጥ የኘራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት አብዛኛው ድርጅቶች ተግባራዊ ያደረጉ ቢሆንም ጥቂት ድርጅቶች ላይ ግን ችግር መከሰቱን ኮንፌዴሬሽኑ ለዚህ ሳምንት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በቀረበው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ሪፖርቱ እንደሚያስረዳው አንዳንድ ድርጅቶች መመሪያውን በተዛባና በራሳቸው አስተሳሰብና አመለካከት በመተርጐም ችግር እየፈጠሩ መሆኑንና ኤጀንሲውም ያስተላለፈውን መመሪያ ተከታትሎ ማስፈፀም ሲገባው ያለማድረጉ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ይገልፃሉ፡፡

ችግሩ የተከሰተባቸው መስሪያ ቤቶች ላይም ከሥራ ኃላፊዎቹ ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል መድረክ በማመቻቸት ውይይት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ሪፖርቱ ቢጠቁምም ችግር ፈጥረዋል ያላቸውን መሥሪያ ቤቶች ስም አልጠቀሰም፡፡

በሌላ በኩልም ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተካሄደው ውይይት በግል ድርጅቶች ለሚሠሩ ሠራተኞች ከባለሃብቶቹ ጋር መደራደር ካልሆነ በቀር መንግሥት ጣልቃ ገብቶ መመሪያ እንደማይሰጥ የተገለፀልን ባለመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የውይይት መድረክ በማመቻቸት በየደረጃው ከየድርጅቶቹ ባለቤቶች ጋር የመደራደር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም በዚሁ ሪፖርት ላይ ተጠቁሟል፡፡

በዳዊት ታዬ

 
< Prev   Next >