| አዲሱ የሶማሊያ ካቢኔ በምክትል... |
|
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
አዲሱ የሶማሊያ ካቢኔ በምክትል አፈ ጉባኤ ተቃውሞ ገጥሞታል ጌዲ ለፕሬዚዳንትነት ይወዳደራሉ የሶማሊያ ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ በቅርቡ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተመሰረተው አዲስ ካቢኔ በይፋ መቃወማቸውን ጋረወይ ኦንላይን የተባለው ድረገፅ ዘግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በመጪው ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት ይወዳደራሉ፡፡ የአገሪቱ ፓርላማ ምክትል ›ð Ñ<v›? *eT” ›=MT> xŸ<` ŸvÃŪ Ÿ}T K]þ`}a‹ እንደተናገሩት፣ የኑር አዴ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ መንግሥት አመሰራረት ፍትሃዊነት የለውም ብለዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ቦኩር፣ ..ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት የመመስረት መብታቸው የተጠበቀ ቢሆንም፣ እኔም የተመሰረተው መንግሥት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መስሎ ካልታየኝ በይፋ የመቃወም መብት አለኝ.. ብለዋል፡፡ ባለስልጣኑ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑር አዴ ጉዳዩን አስመልክተው በአካል መነጋገራቸው የገለፁ ሲሆን፣ እንደ እሳቸው አባባል ምክራቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ከንቱ ቀርተዋል፡፡ ..እኔ የተቃዋሚ ወገን አባል አይደለሁም፣ ይሁን እንጂ ባለኝ የመንግሥት ኃላፊነት መሠረት ሊያማክሩኝ ይገባ ነበር.. ያሉት ቦኩር፣ በእሳቸው ጎሳ ሌላ ቀርቶ በዴኤታ ሚኒስትርነት ደረጃ ቦታ ያገኘ አባል አለመኖሩ የተቃውሞአቸው ምክንያት አስቀምጠዋል፡፡ አዲሱ የሶማሊያ ካቢኔ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ጫና ምክንያት ከቀድሞው ባለ 31 አባላት ወደ 18 አባላት ዝቅ ያለ ቁጥር ያለው ሲሆን፣ ይህ የምክትል አፈ ጉባኤው ተቃውሞ የመጣው ከተለያዩ የህግ አውጪ አካላት ትችት ከተሰነዘረ ጥቂት ቀናት በኋላ ነው፡፡ አዲሱ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑር አዴ የሚመሰርቱት አዲስ ካቢኔ በአገሪቱ አሳታፊ ፖለቲካ ይፈጥራል የሚል የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ከፍተኛ ግምት ጥሎባቸዋል፡፡ በአዲሱ ካቢኔ ከተካተቱት አባላት መካከል ከግማሽ በላይ የተሾሙት ከሽግግር መንግሥቱ ውጪ ሲሆኑ ሂደቱ በተለያዩ አስተያየት ሰጪ ወገኖች ..አበረታች.. መባሉ ይታወሳል፡፡ የአሁኑ የምክትል አፈ ጉባኤው ተቃውሞ የጎሳቸው አንድም አባል በሚኒስቴርነት ደረጃ አለመካተቱ ምክንያት ሲሆን፣ የሶማሊያ ፖለቲካ በእጅጉ በጎሳና ንዑስ ጎሳ ተመጣጣኝ የስልጣን ቦታ ማግኘት መሠረት ያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት ጎሳን መሠረት ያደረገና ቢያንስ በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ሁሉንም የአገሪቱ ጎሳዎች እና ንዑስ ጎሳዎች ተመጣጣኝ የስልጣን ቦታዎች እንዲያገኙ ይረዳል ተብሎ የሚገመት ..4.5 የስልጣን ክፍፍል.. በመባል የሚታወቀው የስልጣን መጋራት ቀመር መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ያሁኑን አካሄድ የሚቃወሙ የአገሪቱ ህግ አውጪ አካላትና አንዳንድ የጎሳ መሪዎች አዲሱ ካቤኔ ለማፅደቅ ወይም ለመቃወም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ድረገፁ እንደአተተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሊ መሐመድ ጌዲ በአገሪቱ እንዲካሄድ እ.ኤ.አ ለ2009 በዕቅድ በተያዘው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ አሳውቀዋል፡፡ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸው በገዛ ራሳቸው የለቀቁ መሐመድ ጌዲ፣ በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባል ሆነው የቀጠሉ ሲሆን፣ አገሪቱን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩዋት የሶማሊያ ሕዝብን ይመርጠኛል የሚል ከፍተኛ እምነት አላቸው፡፡ ..እኔ በለውጥ የማምን ሰው ነኝ.. ያሉት ጌዲ፣ ..2009 ተቃርቧል፣ የሽግግር መንግሥቱ ደግሞ ብዙ መሠራት ያለባቸው የቤት ሥራ አለበት፡፡ ህገ መንግሥቱን ተግባራዊ ካልሆነ እኛ ሶማሊያውያን ወደ ዴሞክራሲ መሸጋገር አንችልም.. በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ እስከ አሁን በአገሪቱ በመጪው ዓመት ለሚደረገው ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት ፉክክር እንደሚወዳደሩ ይፋ ያደረጉ ብቸኛ ሰው መሆናቸውም ገልፀዋል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሽግግር መንግሥቱ አገሪቱ ለሚቀጥለው ዓመት ምርጫ ለማካሄድ እንዲያዘጋጃት ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የህገ መንግሥት ማርቀቅና የሕዝብ ቆጠራ ማካሄድ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማሸጋገር ዋነኛ መከናወን ያለባቸው ተግባራት አስቀምጠዋል፡፡ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ ሕዝብ፣ ጌዲ ስልጣን የለቀቁ በገንዘብ አጠቃቀም ድክመትና ፌዴራላዊ ህገ መንግሥቱን ተግባራዊ ማድረግ ስላቃታቸው ነው ብለው ያምናሉ ይላል ድረገፁ፡፡ በአሁኑ ወቅት በሞቃዲሾ ያለውን አመፅ፣ የሶማሊላንድ የመገንጠል ጥያቄ፣ በውጭ ሃይልና ገንዘብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ የሆነው ደካማ የሽግግር መንግሥት ባለበት ሁኔታ አገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት እንዴት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ ትችላለች በማለት ዲፕሎማቶች ጥርጣሬያቸውን ይገልፃሉ፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |