Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow “ኤርትራውያን ጦርነት ያልከፈቱብን...
“ኤርትራውያን ጦርነት ያልከፈቱብን... Print E-mail
Sunday, 13 April 2008
Image“ኤርትራውያን ጦርነት ያልከፈቱብን እንደማይጠቅማቸው ስለተረዱ ይመስለኛል” ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊው

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሽብርተኛነት ላይ በሚደረገው ጦርነት የዋሽንግተን እጅግ አስፈላጊው የአፍሪካ ሸርካ ናቸው፡፡
አሜሪካ የምትደግፋቸውና የአሰባሰበቻቸው የጦር አበጋዞች፣ በእስልምና በፍርድ ቤቶች ኅብረት ተብለው በሚታወቁት ታጣቂዎች ሞቃዲሾን ከተነጠቁ በኋላ እ.ኤ.አ በ2006 የመለስ ኃይል ሶማሊያን እንዲወር አሜሪካ በድብቅ ረድታለች፡፡

የኢትዮጵያ ሃይሎች፣ የእስልምና ኅብረት ፍርድ ቤቶችን ለማባረር ቢችሉም፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሶማሊያ አክራሪዎችና የጎሳ ሚሊሺያዎች ሰርጎ ገቦች በኢራቅ እንደሚካሄደው፣ የሽምቅ ውጊያ እያደረጉ ናቸው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ባለው ድብልቅልቅ 750,000 ሶማሊያውያን ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ ሲያደርግ የኢትዮጵያ አጋር የሆነውንና በአሜሪካ የሚደገፈው የሽግግር መንግሥት፣ ሞቃዲሾንና አንዳንድ አነስተኛ የሃገሪቱን ክፍሎችን ለመቆጣጠር እንዳይችል አድርጎታል፡፡

በአፍሪካ ሕብረት ባለፈው ዓመት ቃል ከተገባው 8,000 የሰላም አስከባሪዎች ሩብ የሚሆኑት ኢትዮጵያኖችን ይተካሉ፡፡ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እንደገና ለመገንባት ቢሰሩም በዴሞክራሲና በሰበዓዊ መብት አያያዝ ላይ መንግሥተቸው ይተቻል፡፡ የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ የፀጥታ ሃይሎች 193 ሲቪሎች ሲገድሉ አብዛኛዎቹን የተቃዋሚ መሪዎች (በኋላ በይቅርታ ቢለቀቁም) አስረዋል፡፡ በዚህ ሣምንት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የኒውስ ዊኩን ጃሰን ማክሊር ስለ ጠላት ስለሆነችው ሀገር ኤርትራ፣ ከሶማሊያ ለመውጣት ስላላት ዕቅድና ከአሜሪካ ጋር ስላላት ሽርክና አነጋግረዋቸዋል፡፡

ጥያቄ፡- ከሶማሊያ ለመውጣት የኢትዮጵያ እቅድ ምንድን ነው?

ጠ/ሚ መለስ፡-
እዚህ ላይ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው ሸባብ (የእስላሚክ ፍርድ ቤቶች ኅብረት አክራሪ ክንፍ) ሶማሊያን በሙሉ ለመቆጣጠርና በኢትዮጵያ ላይ ጅሃድ ለማወጅ ሲያስፈራራ በኢትዮጵያ ላይ የፈጠረው ሥጋት ነው፡፡ ያ ሥጋት መወገድና መገታት ስለነበረበት በእኛ እምነት ሶማሊያ በገባን በመጀመሪያው ሣምንት ይኸን ተግባር አጠናቀናል፡፡

ከሶማሊያ ለቅቀን ስንወጣ ክፍተት መፍጠር እንደሌለብን በአፍሪካ ኅብረትና በሌሎችም መንግሥታት ስለተነገረ ለትንሽ ጊዜ በዚያው ቆይተን የአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች ሲተኩን ለመውጣት ተስማማን፡፡ ይኸ የተለጠጠ ጊዜ ፈጀ፡፡

ጥያቄ፡- ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪዎች ባይተኩም ከሶማሊያ መልቀቅ አንደኛው አማራጫችሁ ነው?

ጠ/ሚ መለስ፡-
ያም አንድ አማራጭ ነው፡፡ በቀላሉ የማንወስደው አማራጭ ቢሆንም ነገር ግን አማራጭ ነው፡፡

ጥያቄ፡- የአፍሪካ ኅብረትን ወይም የተባበሩት መንግሥታትን ወይም የውጭ የሰላም አስከባሪ ይገባል፤ ብላችሁ እስከመቼ ትጠብቃላችሁ?

ጠ/ሚ መለስ፡-
በእርግጥኝነት ሌላ ዓመት አንጠብቅም፡፡ ለመውጣት የሚያስችሉን ነገሮች ሁሉ ይሳኩልናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው የአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች መሰማራት ነው፡፡ ሁለተኛው የሽግግር መንግሥቱ የፀጥታ ሃይሎች መጠናከር ነው፡፡ ሦስተኛው በሂደት ላይ ያለው ብሔራዊ እርቅ በሞቃዲሾና በሌሎች የሶማሊያ አካባቢዎች መሻሻል ያሳያል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ጥያቄ፡- የፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ ቢወድቅ ወይም ከሞቃዲሾ ውጪ ስልጣኑን ማጠናከር ቢያቅተው ኢትዮጵያ ተለዋጭ እቅድ አላት?

ጠ/ሚ መለስ፡
- ቀደም ብሎ እንዳልኩት እኛ ጣልቃ ከገባንበት ጊዜ በኋላ ባሉት ሳምንታት ሁሉ መውጣት እንችል ነበረ፡፡ ነገር ግን ይህ የሶማሊያን መረጋጋት የሚፈጥር አልነበረም፡፡ በሶማሊያ ዘላቂ መረጋጋት መፍጠር የሁሉም ሰው ፍላጎት ነው፡፡ በግሌ የፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ ይወድቃል ብዬ አላምንም፡፡ አስደናቂ ለውጥ ማምጣት ባይችልም ይወድቃል ብዬ እንዳምን ምንም ምክንያት የለኝም፡፡

ጥያቄ፡- በርካታ ተንታኞች የኢትዮጵያ ወታደሮች ለፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ የደህንነት እርዳታ በመስጠት የአጭር ጊዜ አዎንታዊ ውጤት ቢያስገኙለትም በዘላቂነት ግን ብሔርተኝነትንና እስላማዊ ተቆርቋሪነትን ያነገቡ ኃይሎች አቆጥቁጠው የሽግግር መንግሥቱን ሊያዳክሙት ይችላሉ የሚል እምነት አላቸው፡፡

ጠ/ሚ መለስ፡-
አክራሪ ብሔርተኝነት የሶማሊያ ችግር አይደለም፡፡ በሶማሊያ ያለው ችግር የንኡስ ንኡስ ጎሳ ከመጠን ያለፈ የመከፋፈል አመለካከት ነው፡፡ የእኛ ጥረት ከፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ ጋር በመተባበር ይህ የንኡስ ንኡስ ጎሳ የአመለካከት ክፍተት ለማጥበብ ትኩረት ማድረግ ነው፡፡ የእስላማዊ አክራሪነትን በተመለከተ ሸባብ ሞቃዲሾን በተቆጣጠረበትና መላው ሶማሊያን በቁጥጥሩ ስር ለማዋል ጥረት ሲያደርግ ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ አልነበረችም፡፡ ሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ጂሀድ ሲያውጅ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ውስጥ አልነበረችም፡፡ ኢትዮጵያ ያደረገችው ጣልቃ በመግባት ይህን የሸባብ አጀንዳ በእንጭጩ መቅጨት ነው፡፡

ጥያቄ፡- ከታህሳስ 1999 ዓ.ም ጀምሮ ምን ያህል የኢትዮጵያ ወታደሮች ሞተዋል? ምን ያህልስ ቆስለዋል?

ጠ/ሚ መለስ፡-
በጣም ጥቂት፡፡

ጥያቄ፡- ትክክለኛ ቁጥሩ የለዎትም? በመቶዎች? በሺዎች?

ጠ/ሚ መለስ፡-
በመቶዎች የሚቆጠር፡፡

ጥያቄ፡- በአሁኑ ወቅት በሶማሊያ ምን ያህል ወታደሮች አሉ?

ጠ/ሚ መለስ፡-
  ጥቂት ሺዎች፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ወታደሮች፡፡

ጥያቄ፡- ወረራው ኤትዮጵያን በገንዘብ ምን ያህል አስወጥቷታል?

ጠ/ሚ መለስ፡-
በርካታ ገንዘብ፡፡

ጥያቄ፡- አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር?

ጠ/ሚ መለስ፡-
አይሆንም፡፡ ቀላል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በመጠነኛ ወጭ ነው በኢትዮጵያ በኩል ጣልቃ ገብነቱ የተፈፀመው፡፡ ያ ማለት ግን በሶማሊያ ላይ ያወጣናት እያንዳንዷ ሳንቲም ኢትዮጵያ ላይ ብናወጣው የተሻለ አልነበረም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ጀርባችንን ሳንሰብር በሶማሊያ ቆይታችንን ለመቀጠል ችለናል፡፡

ጥያቄ፡- ይህን ጣልቃ ገብነት ለመሸፈን ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ምን ያህል ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ አገኘች?    

ጠ/ሚ መለስ፡
- ዜሮ፡፡

ጥያቄ፡- ኢትዮጵያ ምዕራባዊያን ለፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ እና ለኢትዮጵያ ባደረጉት የእርዳታ መጠን ተበሳጭታለች?

ጠ/ሚ መለስ፡-
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የተባባሩት መንግሥታት ምላሽ በአጠቃላይ ከጠበቅነው በታች ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ለምን እንዳልላከ እንረዳለን፡፡ ነገር ግን በፀጥታው ምክር ቤት አማካኝነት የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪነት ተግባሩን እንዲወጣ ለምን በገንዘብ እንዳልረዳ አልገባንም፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በዳርፉር ያለው የአፍሪካ ኅብረት ልዑክ በተባበሩት መንግሥታት ልዑክ እንዲለወጥና በተባበሩት መንግሥታት በገንዘብ እንዲደጎም እንደሚወተውት ሲታወቅ በሶማሊያ ያለውን የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በገንዘብ ለመደጎም ግን ፈቃደኛ አይደለም፡፡

አሜሪካ ግን በተሻለ ሁኔታ ተባባሪ ነች፡፡ ለምሳሌ ለዩጋንዳ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ወደ ሞቃዲሾ ለማሰማራት ትብብር አድርጋለች፡፡ ለፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ እና ለሶማሊያ መረጋጋት በዲፕሎማሲው ረገድ ድጋፍ ሰጥታለች፡፡ አሜሪካ የፀጥታው ምክር ቤት ዋነኛ አባል ሆና እያለ የፀጥታው ምክር ቤት በአካባቢው የጠበቅነውን ምላሽ ሰጥቷል ማለት ግን አይደለም፡፡

ጥያቄ፡- የአሜሪካ መንግሥት በሶማሊያ ጉዳይ ድብቅ ተልዕኮ እንዳለው አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡ የአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች በፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ የይስሙላ ቦታ ያላቸውና ለእርቁ ሂደት ጠቃሚ ያልሆኑትን እንደ ቀድሞው የጦር አለቃና የአሁኑ የሞቃዲሾ ከንቲባ ሞሐመድ ዳሒር ዓይነቶቹን ትረዳለች ይባላል?

ጠ/ሚ መለስ፡-
እ.ኤ.አ. በ2006 ሸባብ ሞቃዲሾን ከመቆጣጠሩ በፊት በአሜሪካ የደህንነት ማህበረሰብ አባላት የነበሩ ጥቂት ሰዎች አልሸባብን ለማስወገድ የተሰባሰቡትን ሁሉንም የጦር አለቆች ይረዱ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ያልተሳካ ሙከራ በመሆኑ አሉታዊ ሚና ነበረው፡፡ ፖሊሲው በሚያሳዝን ሁኔታ ወድቋል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን በነበረበት ሁኔታ አልቀጠለም፡፡ ከዚያ በኋላ የአሜሪካ ዋነኛ ጥረት በአፍሪካ ኅብረትና በፌዴራል ሽግግር መንግሥቱ በኩል ነው፡፡ አሁንም ቢሆን በሶማሊያ በሸመቁ ግለሰብ አሸባሪዎች ላይ ትኩረት የሚደረግበት ሁኔታ አለ፡፡ በተለይም በአንዳንድ የስለላ ድርጅቶች በኩል ይህን የሽብርተኝነት ጉዳይ ለይቶ የማየት ሁኔታ አለ፡፡ ነገር ግን በአጠቃላይ ከዚያ በኋላ የአሜሪካ ፖሊሲ ተለውጧል፡፡

ጥያቄ፡- በአሜሪካ መንግሥት ውስጥ ጥቂት ሰዎች ሽብርተኝነትን በተናጠል ያዩታል ሲሉ በሰፊው ፖሊሲ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ይኖረዋል?

ጠ/ሚ መለስ፡-
ብዙም የለውም፡፡ እነዚህን ሽብርተኞች ለመግደል የሚደረጉ ዘመቻዎች ነበሩ፡፡ ይሄ ጥሩ ነው፡፡ የእነዚህ ሽብርተኞች መወገድ አንዱ የመፍትሔው አካል ነው፡፡ ነገር ግን እነሱን ለማዳን ያልተመጣጠነ የሀብትና የጊዜ መጠን ካወጣና አገር ከመገንባት መፍትሔው ጋር ከተፃረረ ውጤቱ አሉታዊ ይሆናል፡፡ ይህ ዓይነት አደጋ አለው፡፡ አንዳንድ የአሜሪካ ተቋማት በዚህ ዓይነት ዘመቻ ላይ ከበቂ በላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡

ጥያቄ፡- ምክንያቱም የአሜሪካ መንግሥት በአጠቃላይ ወደ ደርዘን የሚጠጉና ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ግቦችን ማግኘት ይፈልጋል፣

ጠ/ሚ መለስ፡-
አዎ፡፡

ጥያቄ፡- ስለዚህ እነዚህን ደርዘን ግቦች ለማግኘት የአሜሪካ መንግሥት ሌሎች ነገሮች ላይም አቅርቦትና ትኩረቱን ያደርጋል ማለት ነው?

ጠ/ሚ መለስ
፡- አዎ ጊዜህንና አቅርቦትህን የማመጣጠን ጥያቄ ነው፡፡

ጥያቄ፡- በቅርቡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአልሸባብ ቡድን በአሸባሪነት ተርታ አስፍሮታል፡፡ ይህ በዕርቁ ሂደት ምን ዓይነት ተፅዕኖ ይኖረዋል?

ጠ/ሚ መለስ፡- 
የአሜሪካ መንግሥት የአልሸባብ ቡድንን እስከ አሁን በአሸባሪዎች ተርታ ሳያስመዘግበው የቆየበት ምክንያት አልገባኝም፡፡  ማዕከል ያደረገው እስላማዊት የአፍሪካ ቀንድ ለመመስረት አጀንዳ የያዘና ከአልቃኢዳ ጋር ከፍተኛ ትስስር ያለውን ከዚህ ዓይነት ቡድን ጋር ዕርቅ መፍጠር ይቻላል የሚል እምነት ላለው ወገን ይህንን ቡድን በአሸባሪነት መመዘገቡ የዕርቅ ሃደቱን ይጎዳል ሊባል  እየተባለው ያለውን ዕርቅ እንደማሸነፍ የሚቆጠር ከሆነ ደግሞ ቡድኑ በአሸባሪነት መፈረጁ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም፡፡ በእርግጥ ከተቃዋሚው የእስላማዊ ፍ/ቤቶች ኅብረት ውስጥ የአልሻባብ አባል ያልሆኑት በርካቶች ናቸው፡፡ የአልሸባብ ቡድን በጣም ጥቂትና አጅግ አክራሪዎች የሆኑ ሰዎች ያቀፈ ቡድን ነው፡፡

ከዚህ  ውጭ ያለው ማናቸውም ጋር መነጋገርና በአልሸባብ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉት ግለሰቦችም ማሸነፍ ይቻላል፡፡

ጥያቄ፡- በኦጋዴን አካባቢ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በተመለከተ፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት የሽምቅ ተዋጊዎች ለማጥፋት የወሰዳችሁት እርምጃ ምን ደረጃ ላይ ደረሰ? በኦብነግና በሶማሊያ ውስጥ ያሉት የሽምቅ ተዋጊዎች መካከል ያለው ትስስርስ ምን ይመስላል?

ጠ/ሚ መለስ፡-
በኤርትራውያን አቀነባባሪነት የሶማሊያ እስላማዊ ፍ/ቤቶች ኅብረት ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ዓመፂ ቡድኖችን ያካተተ አንድ ትልቅ ግንባር ተፈጥሮ ነበር፡፡ በዚህ ግንባር ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ኦብነግን ነው፡፡ ከወዲሁ ኦብነግ ወደ አካባቢው ተመልሶ የመምጣት ዕድሉ ያበቃለት ይመስለኛል፡፡

ጥያቄ፡- ኢትዮጵያ በኦጋዴን የነበረው ዓማፂ ቡድን መልሶ ለማጥቃት በወሰደችው እርምጃ በርካታ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተከሳ ነበር፡፡ የአሜሪካ ሳተላይቶች በአካባቢው የተቃጠሉ መንደሮችን አሳይቷል፡፡ እነዚያ ጥሰቶች በአሁኑ ወቅት ምን ደረጃ ላይ ናቸው?

ጠ/ሚ መለስ፡
- በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ምን ዓይነት ጥሰት እየተፈፀመ አይደለም፡፡ በተፈጥሮው ጦርነት ባለበት ሞት ይኖራል፡፡ እንደውም አንዳንድ ጊዜ የንፁሃን ዜጎች ሞት ያጋጥማል፡፡ በአካባቢው የነበረው ጦርነት ግን በአብዛኛው በሰው ሃይል የተካሄደ በመሆኑ፣ የጅምላ ጭፍጨፋው የቀነሰ ነው፡፡ የአሜሪካ የመረጃ መረበቦች የመንደሮች መቃጠል (መውደም)፣ የንፁሃን ዜጎች መገደልና በአጠቃላይ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የሚያሳይ እንደሆነ አላቅም፡፡

ጥያቄ፡- ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ሰላም አስካባሪዎቹ ከድንበሩ ወጥተዋል፡፡ ሁለቱም አገሮች ጦርነት ከመክፈት ያገዳቸው ምንድን ነው?

ጠ/ሚ መለስ፡-
እኛ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ያልከፈትነው ስለማያስፈልገን ነው፡፡ የባለፈው አንድ መጥፎ ጦርነት ይበቃል፡፡ በኤርትራውያን ወገንም ጦርነት ከመክፈት የተቆጠቡት ከጦርነቱ እንደማይጠቀሙ በመገንዘባቸው ይመስለኛል፡፡

ጥያቄ፡- የአገልግሎት ዘመንዎ ከሁለት ዓመት በኋላ (እ.ኤ.አ በ2010) ሲያበቃ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የመቆየት ፍላጎት አለዎት?

ጠ/ሚ መለስ
፡- ለእኔ የመጨረሻው የአገልግሎት ጊዜዬ ይመስለኛል፡፡

ጥያቄ፡- የአካባቢና የማሟያ የምርጫ ጊዜ እየተቃረበ ነው ረእየተካሄደ ነውሪ፡፡ በእስር ላይ የቆዩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች  አመራሮች አብዛኛዎቹ በምርጫው አይሳተፉም፡፡ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ ወከባና ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ ጥረት አሁን ያለበትን ደረጃ እንዴት ይገልፁታል?

ጠ/ሚ መለስ፡
- ዴሞክራሲን ደረጃ በደረጃ እያጠናከርነው ነው፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ ፓርላማ የገቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የነበራቸው ስጋት ለማስወገድ ተወያይተናል፡፡ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አደረጃጀትን ለውጠናል፡፡ በፓርላማ ውስጥ አነስተኛ መቀመጫ ያላቸው አካላት አጀንዳ በማንሳት በተወሰኑ ቀናት ለክርክር እንዲቀርብ የሚያደርግ የፓርላማ አሰራር ቀርፀናል፡፡ አዲስ የፕሬስ ሕግ ለማፅደቅ በሂደት ላይ ነን፡፡ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የፕሬስ ህጎች አንዱ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ስለዚህ በተቋሞቻችን የነበሩት ችግሮች ላይ በተከታታይ መሻሻል እያደረግን ነው፡፡ ምርጫ በመጣ ቁጥር አንዳንድ ሰው በሚያስጠላ ሁኔታ ያለቅሳል፡፡ ይህ ያለመታደል ሁኖ በአህጉራችን የተለመደ አድራጎት ሆኗል፡፡ ይህ ደግሞ የሚከናወነው በማስረጃ ማስደገፍ አጠራጣሪ ነው፡፡ ከዚህ ነገር ጋር ሁላችንም መላመድ አለብን፡፡

ጥያቄ፡- ነዳጅ ከሚያመርቱ የአፍሪካ ሀገሮች በፍጥነት በማደግ ላይ ያለችው ሀገር ኢትዮጵያ ነች፡፡ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ግን 9 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕዝቦች የምግብ እርዳታ በዚህ ዓመት እንደሚያስፈልጋቸው ገል..ል፣

ጠ/ሚ መለስ፡-
አርብቶ አደሩ አካባቢ ያስመዘገብነው ድል በሌሎች አካባቢዎች ካስመዘገብነው እድገት ያነሰ ነው፡፡ የአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ደግሞ ለየአር ንብረት ለውጥ የተጋለጡ ናቸው፡፡ አርብቶ አደሩ የበለጠ ምርታማ እንዲሆን እና በፈቃደኝነት የተመሰረተ የሰፈራ ፕሮግራም እንዲፈፅሙ እናበረታታለን፡፡ ከመስኖ ጋር የተያያዙ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በተለይም በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ነገሮችን መፈፀም እንፈልጋለን፡፡ በቅርብ ዓመታት ድህነት የሚብሰው በከተማ ባሉ ደሀዎች ይሆናል፡፡ ባለፉት ዓመታት በድህነት ይበልጥ የሚጠቃው የገጠሩ ሕዝብ የነበረ ቢሆንም አሁን በከተማ የሚኖረው ደሀው ማኅበረሰብ ገቢው ሊጨምር አልቻለም፡፡ ስለዚህ ተጠቂው አካል ከገጠር ወደ ከተማ ተዛውሯል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት ባለ ሁለት አሀዝ እድገት ብናስመዘግብም አሁንም የተጋረጥናቸውና መልስ መስጠት ያለብን በርካታ ፈተናዎች ተደቅነውብናል፡፡
 
< Prev   Next >