Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሚኒስቴሩ የፍትህ ሥርዓት...
ሚኒስቴሩ የፍትህ ሥርዓት... Print E-mail
Sunday, 13 April 2008
ሚኒስቴሩ የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያዎችን እየተገበረ መሆኑን ገለፀ"
ፍትህ ሚኒስቴር ሰፊ የፍትህ ሥርዓት በመዘርጋት ያሉበትን ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን የፌዴራል የመጀመሪያ ከፍተኛ ደረጃ አቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ክትትልና ማስተባበሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚካኤል ተክሉ ገለጹ፡፡

 

መሥሪያ ቤቱ በፈጣን የፍትህ አሰጣጥና በኤግዚቢት የተያዙ ንብረቶች አመላለስን በተመለከተ እየወጣ ባለው እርምጃ ዙሪያ ባለፈው ሐሙስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አቶ ሚካኤል እንዳመለከቱት፣ ፍትህ ሚኒስቴር እንደሌሎች ሲቪል መሥሪያ ቤቶች ካለፉት ሥርዓቶች ሲተላለፍ የመጣ ሰፊ ችግሮች አሉበት፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ሰፊ እንቅስቃሴ ተደርጐ አጥጋቢ ውጤት ተገኝቷል፡፡

የተለያዩ ምድቦች ሥራቸውን በተቀላጠፈና አጋዥ በሆነ መልኩ የሚያከናውኑበት አሠራር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

አዲስ ዘመን፣ ሚያዚያ 3 ቀን 2000 ዓ.ም
*          *            *

300 አውቶብሶች አገር ውስጥ ገቡ

መንግሥት የአዲስ አበባን ትራንስፖርት ችግር ለማቃለል በ166 ሚሊዮን ብር ገዝቶ ከውጭ ለማስገባት ካቀደው 500 አውቶብሶች መካከል 300 የሚሆኑትን ከነ ሙሉ መለዋወጫቸው አገር ውስጥ መግባታቸውን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በቅርቡ ተገዝተው የገቡት 300 መለስተኛ አውቶብሶች ከ99 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተገዙ፣ ወደ ግል ባለሀብት የማዘዋወር ሥራ እየተሰራ መሆኑን፣ 101 የሚሆኑት ሥራ መጀመራቸውን፣ የአንዱ ዋጋ 332 ሺ ብር እንደሆነና ለመግዛት የሚፈልግ እጅ በእጅ ወይም በባንክ ብድር 30 በመቶ በዝግ አካውንት አስይዞ 70 በመቶ በመበደር መግዛት እንደሚችል ገል"ል፡፡

ኢዜአ
*          *            *

የዶሮ ማጂ በገበያ ላይ ዋለ

በዓለም ታዋቂ የምግብ አምራችና የማጂ ምርቶች ባለቤት የሆነው ኔስሌ ምርቱን ለኢትዮጵያ የምግብ አዘጋጆች እንዲደርስ ማድረጉንና ከአስር ዓመታት በላይ በፔትራም በኩል ማቅረቡን፣ እስካሁን በኢትዮጵያ ገበያ ላይ የቀረቡት ምርቶች የዶሮ ማጂና የአትክልት ባለ 2 እሽግና የማጂ ኪዮብ የዶሮና የቅመም ዓይነቶች፣ የማጂ ፈሳሽ ለአትክልት በላተኞችና ለፆመኞች መሆኑን የማጂ ቢዝነስ ሥራ አስኪያጅ ሚስተር አሌክስ ተጁልኪን ገልፀዋል፡፡

አዲሶቹ ምርቶች የዶሮ ማጂም ስላላቸው በኢትዮጵያውያን ተመጋቢዎች ዘንድ ተመራጭነት ስለሚኖራቸውና ከባህል ምግብ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ ምርት ባለአንድ፣ ባለሁለት እሽግ ወይም ባለስድስት እሽግ አድርጐ ለገበያ ያቀረበው ኩባንያው፣ የሁሉንም አቅም እንዲመጥን ታስቦ መሆኑን፣ ኢቴን ሩጅ በሸራ ተን ሆቴል በተካሄደው የምርት ማስተዋወቂያ ላይ መናገራቸውን የማጂ ዶሮ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ መዋሉን ተወካዮቹ ሚያዚያ 2 ቀን 2000 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልፀዋል፡፡

*          *            *

ከ448 ሚሊዮን ዶላር በላይ ስምምነት ተፈረመ

በኢትዮጵያ መንግሥትና በዓለም ምግብ ፕሮግራም መካከል 595ሺ 325 ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የ448 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈረመ፡፡

የምግብ እርዳታው በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በአገራቱ የሚካሄደውን የሶፍትኔት ፕሮግራም፣ የዕርዳታ እንቅስቃሴና የተጨማሪ መመገቢያ ፕሮግራምና ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ፕሮግራም ድጋፍ ይውላል፡፡

ኢዜአ

 
< Prev   Next >