Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow የዋጋ ተመን ማውጣትና መቆጣጠር...
የዋጋ ተመን ማውጣትና መቆጣጠር... Print E-mail
Sunday, 13 April 2008
Image
ዶ/ር ጃኪም ቮን ብራውን
የዋጋ ተመን ማውጣትና መቆጣጠር በኢኮኖሚ እድገት ላይ ጫና ይፈጥራል


በምግብ ምርቶች ላይ በታየው የዋጋ ጭማሪ የዋጋ ተመን ማውጣት፣ በገቢና በወጪ ንግድ ላይ ቁጥጥር ማድረግ በአጭር ጊዜ ዋጋን ሊያረጋጋ ቢችልም በኢኮኖሚ እድገት ላይ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል ተጠቆመ፡፡
በዓለም አቀፍ የምግብ ፖሊሲ ምርምር ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጃኪም ቮን ብራውን ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2000 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በታዳጊ አገር ያለውን ግብርና ለማሳደግ የግብርና እውቀትና ፈጠራ በሚል ርዕስ በተካሄደ ወርክሾፕ ላይ የዓለም የምግብ ዋጋ መጨመርና የመፍትሄ ሃሳብ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናት ላይ እንደገለፁት የምግብ ዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት የተወሰዱት እርምጃዎች በኢኮኖሚ እድገት ላይ ጫና በመፍጠር ልማትን ወደ ኋላ ይመልሳሉ፡፡

ስለሆነም የግብርና ምርታማነትን በመጨመር በዋጋ ላይ የሚኖረውን ጫና ለመቀነስ የሚያስችል የፖሊሲ እርምጃ ያስፈልጋል፡፡

የዋጋ ተመን ማውጣት፣ በገቢ ምርቶች ላይ ያለውን ታክስና ቀረጥ ማንሳትና መቀነስ የግብርና ምርቶችን ወጪ ንግድ ማቆምና ቁጥጥር ማድረግ በአጭር ጊዜ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ ቢያስችልም ዓለም አቀፉ የምግብ ምርቶች ገበያ አነስተኛና ዋጋው ተለዋዋጭ እንዲሆን እንደሚያደርገው የጠቆሙት ዶ/ር ብራውን በቀጣይ የተሻለ ምርት እንዳያመርቱ የገበሬዎችን ተነሳሽነት በመቀነስ በአቅርቦት ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

በወጪና በገቢ ንግድ ላይ ቁጥጥርና የታክስ ቅነሳ ማድረግ በንግድ ልውውጥ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲፈጥር የገበያ እድልን ይቀንሳል ብለዋል፡፡ በምግብ እህሎች ላይ ያለውን የዋጋ ጭማሪ ለማስተካከል የፖሊሰ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ሚ/ር ብራውን ለአርሶ አደሩ የግብርና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የእርሻ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማስፋፋት፣ የገበያ እድል በመፍጠር፣ ገበያውን ሊያበላሹ የሚችሉ ከለላዎችን በማንሳት የንግድ ፖሊሰ ለውጥ የማድረግ አስፈላጊነትን አብራርተዋል፡፡

 በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣው የምግብ ምርቶች ዋጋ በታዳጊ አገሮች ላለው የዋጋ ንረት ዋነኛ ምክንያት ሲሆን በምግብ እህሎች ላይ ያለውን የዋጋ ንረት መንስኤና ችግሮቹን ለማወቅ ተጨማሪ የተወሰኑ የፖሊሲ (Specific policy) እርምጃዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በመወሰድ ላይ ያሉት እርምጃዎች አስተማማኝና ወጥ መሆን እንደሚገባቸው ገልፀው በአጭር ጊዜ ለችግሩ የተጋለጡትን ለመርዳት ብሎም የዋጋ ንረቱ ከዚህ በበለጠ እንዳይጨምር ለመግታት ወቅታዊ የሆነ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

የዋጋ ንረቱን በረዥም ጊዜ ለማስተካከል የግብርና ምርታማነት በማሳደግ በኩል በትኩረት መስራት አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ለሚደረጉ እርምጃዎች የታዳጊ አገር መንግሥታት አነስተኛ ገቢ ላላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በዋጋ ንረት የበለጠ እንዳይጎዱ ድጎማና ቀጥተኛ እገዛ ለመስጠት እንዲችሉ ያደጉ አገሮች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል፡፡

የዋጋ ንረቱ የጎዳቸውን አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ማገዝና በአነስተኛ ዋጋ እንዲያገኙ ማስቻል በነጋዴዎች ሆነ በሸማቾች ውስጥ ያለውን የዋጋ ይጨምራል ፍራቻ ለመቀነስ እንደሚያስችል ይህ ካልሆነ በማደግ ላይ ያለውን የመጣውን ዋጋ ለመቀነስ ከፍተኛ ወጪ ሊጠይቅ እንደሚችል ያላቸውን ፍራቻ ገልፀዋል፡፡

ለጋሾች ከምግብ ጋር የተያያዘ የልማት ድጋፍ እንዲያጠናክሩና ለባዮ ፊውል የሚሰጡትን ድጎማ እንዲያነሱም ጠይቀዋል፡፡ በአሜሪካ ለኢታኖል በአውሮፓ ለባዮዲዝል የሚሰጠው ድጎማ በዓለም የምግብ ምርቶች ላይ ጫና መፍጠሩንና ገበሬዎች ከድጎማ ነፃ በሆነ መልኩ የሚያመርቱበት ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ለግብርና ምርቶች የሚሰጠውን ከለላ መቀነስ በዋጋ ላይ የሚኖረውን ጫና ለመቀነስ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

ለምግብ ምርቶች ዋጋ መጨመር የነዳጅ ዋጋ መጨመር አይነተኛ ምክንያት ሲሆን በአሜሪካ የሚገኙ አርሶ አደሮች መንግሥት በሰጣቸው ድጎማ ለባዮፊውል አገልግሎት የሚውሉ ምርቶችን በማምረት ላይ ሲሆኑ 3ዐ በመቶ የሚሆነው በቆሎ ለምግብ ገበያ መቅረቡ ቀርቶ ለኢታኖል መሥሪያ በማገልገል ላይ መሆኑንም ሚ/ር ብራውን ገልፀዋል፡፡

አንዳንድ ያደጉ አገሮች የሚሰጡትን ድጎማ የታዳጊ አገር ገበሬዎች እየጎዳ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት በ1999/2000 ያወጣው ጥናት ጠቅሰው እንደገለፁት የምግብ ምርቶች ዋጋ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው በ40 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ጭማሪው ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የስንዴ ዋጋ በ1992 በሦስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን የበቆሎ ዋጋ በእጥፍ አድጓል፡፡ የአብዛኛው ሕብረተሰብ የመግዛት አቅም ባላደገበት ሁኔታ ተጨባጭ የሆነ የምርት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱ አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል በመጉዳት ላይ ነው፡፡

በታዳጊ አገሮች እየታየ ያለው የኢኮኖሚ እድገት የሕብረተሰቡን የመግዛት አቅም በማሳደግ በምግብ ፍላጐት ላይ ግፊት መፍጠሩ፣ የነዳጅ መጨመር፣ የማዳበሪያ፣ የግብአትና የትራንስፖርት ዋጋ ላይ የተፈጠረው ለውጥ ለዋጋ ንረቱ በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡

በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከ50 እስከ 60 በመቶ የሚሆነው ገቢያቸውን ለምግብ መዋሉ በሌሎች ዘርፎች ላይ ያላቸውን ፍላጎት እንደሚቀንሰው ገልፀዋል፡፡

በቤዛዊት ሥዩም
 
< Prev   Next >