| በአዲስ ንግድ ለእድገት... |
|
|
| Sunday, 13 April 2008 | |
|
በአዲስ ንግድ ለእድገት ትርዒት ከ200 በላይ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ
“ተወዳዳሪነት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል 11ኛው የአዲስ ንግድ ለእድገት የንግድ ትርዒትና ባዛር ላይ ከ200 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ተገለፀ፡፡ የአዲስ ንግድ ለእድገት የንግድ ትርዒትና ባዛር አዘጋጅ የሴንቸሪ ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውገ ጀማል እንደገለፁት የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ይህ የንግድ ትርዒትና ባዛር “የኢትዮጵያን ምርቶች ይግዙ” (Buy Ethiopian) የሚል መልዕክት ያለው ሲሆን የአገሪቱ ምርቶች የሚተዋወቁበትም ይሆናል፡፡ ከሚያዚያ 8 እስከ 18 ቀን 2000 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሚካሄደው ዝግጅት ተሳታፊ ከሚሆኑት ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በኩል የተመረጡ 100 ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ ምርትና አገልግሎታቸውን እንደሚያቀርቡ የተገለፀ ሲሆን የኢንተርፕራይዞቹ ቢሮው 100 ሺህ ብር የቦታ ክፍያ እንዲፈፅም ተደርጓል፡፡ ለ100ዎች ኢንተርፕራይዞች ለቦታ ክፍያ ይከፈል የነበረው 265 ሺህ ብር ቢሆንም የኢንተርፕይዙን ምርቶች ለማስተዋወቅ ሲባል 165 ሺህ ብሩን ሴንቸሪ ፕሮሞሽን ስፖንሰር እንዳደረጋቸውም ከአቶ ዘውገ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ሴንቸሪ ፕሮሞሽን የዘንድሮውን የፋሲካ በዓል የንግድ ትርዒትና ባዛር ለማዘጋጀት ኤግዚቢሽን ማዕከልን ለአስር ቀን ለመጠቀም ያሸነፈበት የጨረታ ዋጋ አንድ ሚሊዮን ብር በመሆኑ ለተሣታፊ ኩባንያዎች የ30 በመቶ ቅናሽ አድርጓል፡፡ በመሆኑም ተሳታፊ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን በቅናሽ ዋጋ ይሸጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሴንቸሪ ፕሮሞሽን ቀደም ሲል የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት በተዘጋጀው ዝግጅት ማዕከሉን ለመጠቀም በተደረገ ጨረታ 2.5 ሚሊዮን ብር ለገና ደግሞ 1.4 ሚሊዮን ብር በመክፈል ዝግጅት ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |