| በርካታ አፍሪካውያን የባንክ አገልግሎት... |
|
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
በርካታ አፍሪካውያን የባንክ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተጠቆመ በኢትዮጵያ አንድ ባንክ ለ1ዐ ሺህ ሰዎች ይደርሳል በአፍሪካ በርካታ ባንኮች የሚገኙት በከተሞች አካባቢ በመሆኑ በርካታ አፍሪካውያን የባንክ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚቸገሩ ..አፍሪካ ሪኒዋል.. የተባለ የተ.መ.ድ የዜና ምንጭ አስታወቀ፡፡ በዓለም ባንክ የቅኝት ሪፖርት መሠረት በኢትዮጵያ አንድ የባንክ ቅርንጫፍ ለ1ዐ ሺህ ሰዎች እንደሚደርስም ተገልጿል፡፡ በስፔን ደግሞ 96 ቅርንጫፎች ለ1ዐ ሺህ ሠዎች የሚደርስ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በዚሁ ዘገባው በኬንያ 9ዐ በመቶ የሚሆኑት ኬንያውያን በመደበኛ ባንክ ውስጥ የራሳቸው ሂሳብ የሌላቸው ናቸው፡፡ በመላ አፍሪካ መደበኛ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙት ሃያ ከመቶ የሚሆኑት ቤተሰቦች ብቻ ናቸው ይላል ይኸው ዘገባ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ አፍሪካ በኬንያና በሌሎች አገሮች የሞባይል ስልኮች የባንክ አገልግሎት ባልተስፋፋባቸው የገጠር አካባቢዎች እየሰጡ መሆናቸውን የሚጠቁመው ይኸው ዘገባ አፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ የመጡትን የሞባይል ስልክ ለባንክ አገልግሎት ማዋልን ..በእያንዳንዱ ሰው ኪስ ውስጥ ያለ ባንክ.. በማለት ይጠራዋል፡፡ በጐረቤት ኬንያ እንዲህ ዓይነቱ አሠራር እየተለመደ መጥቷል፡፡ የሞባይል ባንክ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልግ ሠው በቅድሚያው በአካባቢው የሚገኙ ትናንሽ ኪዮስክ መሣይ ቢሮዎች በመሄድ አልግሎቱን የሚያገኝበት ምዝገባ በቀላሉ ይፈፅማል፡፡ ከዚያም ገንዘብ ማውጣት በሚፈልግበት ጊዜ የመታወቂያ ወረቀቱንና የሞባይል የይለፍ ቁጥሩን በመያዝ አገልግሎት ወደሚያገኝበት ቢሮ መሄድ ይችላል፡፡ ይህም በፍጥነት ገንዘብ እንዲያኝ ያስችለዋል፡፡ በሞባይል የሚፈፀም የባንክ አገልግሎት በአፍሪካ መስፋፋትና ቴክኖሎጂውን ለማድረስ የሚያስችል ..ኮኔክት አፍሪካ ሰሚት.. የተባለ ጉባዔ በቅርቡ ሩዋንዳ ኪጋሊ ውስጥ ሲካሄድ ይህ አገልግሎት ዋነኛ መወያያ አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል፡፡ በአፍሪካ ከሚገኙ አገሮች በባንክ አገልግሎት የተሻለ ደረጃ ላይ የምትገኘው ደቡብ አፍሪካ የዚህ ዓይነት አገልግሎት በማስፋፋት አመርቂ ውጤት ማግኘትዋንም ይኸው ዘገባ ያስረዳል፡፡ እ.ኤ.አ በ2ዐዐ4 የተቋቋመው ፣ዊዚት፣ የተባለው ኩባንያ በሞባይል ስልክ የባንክ አገልግሎት በመስጠት 5ዐ ሺህ ደንበኞችን አፍርቷል፡፡ ኩባንያው ወደፊት ደንበኞቹን 16 ሚሊዮን ለማድረስም እቅድ ይዟል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |