| ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የሚመለከታቸው... |
|
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ተጠየቀ ባለሐብቶች በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ እንዲሠማሩ ለማስቻል ፍሰቱን ለማሳደግ ኤጀንሲው የሚሰራው ብቻ በቂ ስላልሆነ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ አቢ ወልደመስቀል ባለፈው ሐሙስ ጥር 24 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ባለሐብቶች በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ለማስቻል የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸው አመልክተዋል፡፡ በኤጀንሲው ፈቃድ የወሰዱት የውጪ ባለሀብቶች የሚያገኙት ድጋፍ ሌሎች ባለሀብቶች እንዲገቡ እንደሚያበረታታ፣ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ መሬት በመስጠት፣ በጉምሩክ፣ የካፒታል ዕቃዎችን ከቀረጥ ነጻ በማስገባትና መረጃን በመስጠት ቀልጣፋ አመራር መከተል አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል፡፡ ከፕሮሞሽን በፊት አስፈላጊ የኢንቨስትመንት ከባቢ አየር መፍጠር ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በኤጀንሲው አስፈላጊ ያልሆነና እሴት የማይጨምሩ ሕጎችንና የቢሮክራሲ አመራሮችን ለማስተካከል የሪፎርም ፕሮግራም ተቀርፆ ተግባራዊ በመሆን ላይ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ከአምስት አመት በፊት አጠቃላይ የፕሮሞሽን ሥራ ቢከተሉም በኢንቨስትመንት ፍሰት ስኬታማ የሆኑ አገሮችን ልምድ በማጥናት በማነጣጠር ላይ የተመረኮዘ የፕሮሞሽን አካሄድ አዋጪ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ እየሠሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡ አቶ አቢ፣ አጠቃላይ የፕሮሞሽን ስልት ሰፊ ጥናትና ሐብት እንደሚጠይቅ፣ ማነጣጠር ከሚፈለገው ኢንቨስትመንት አኳያ የኩባንያዎችን፣ የአገሮችን ልምድ በመመልከት መመልመል የተሻለ ውጤታማ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም ከኤምባሲዎች ጋር በመቀናጀት አስፈላጊ ጥናት እየተደረገ መሆኑንና አግባብቶ የማምጣት ሂደቱ ቀጣይነት እንደሚኖረውም ይፋ አድርገዋል፡፡ ባለፈው ወር ከፍተኛ በቆዳና ሌጦ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ይዘው በመሄድ የፕሮሞሽንና የምልመላ ሥራ በኢጣሊያ ሁለት ከተሞች መሠራቱን አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም በእንግሊዝ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኦስትሪያ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የማግባባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በጨርቃ ጨርቅ በቆዳና ሌጦ ላይ በተሠራው የማግባባት ሥራ የኢንቨስትመንት ከባቢውን ለማጥናት የመጡ ባለሃብቶች መኖራቸውንም ገልፀዋል፡፡ የኢንቨስትመንት መረጃ በሚፈለገው ጥራትና መጠን እንደሌለ ያመለከቱት አቶ አቢ የተለያየ ደረጃ ያለው ጥናት በገበያ፣ በጥሬ ዕቃ፣ በሰው ኃይል፣ በፋይናንስና ቅድሚያ በሚሰጣቸው መስኮች እየተሰባሰበ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ኤጀንሲው ለባለሐብቶች ፈቃድ መስጠት ብቻ ሳይሆን በሚሄዱበት ክልል መሬት እንዲሰጣቸው ድጋፍ መፃፍ፣ እንዲሁም ያሉበትንም ሁኔታ ደረጃ በደረጃ እንደሚከታተል አስረድተዋል፡፡ ፈቃድ ከወሰዱት ባለሀብቶች ወደ ሥራ የገቡት ቁጥር አናሳ እንደሆነ፤ ባለሀብቶቹ ፈቃድ በወሰዱበት አገልግሎት በትክክል መሥራት አለመስራታቸውንና ያሉባቸው ችግሮች በሚደረገው ክትትልና ውጤት በየዓመቱ ፈቃድ በሚያሳድሱበት ጊዜ እየታየ ማስተካከያ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ ሥራ ያልጀመሩ ባለሐብቶች በኤጀንሲው በተቋቋመው የክትትልና ድጋፍ መምሪያ የሚመጡ መረጃዎችን ከባለሀብቱ ምክንያት ጋር በማመሳከር አሳማኝ ካልሆነ ፈቃድ የሚሰረዝበት ሁኔታ እንዳለም ጠቅሰዋል፡፡ አጠቃላይ መረጃን በመስጠት በኩል በገበያ፣ አካባቢ፣ ተፈጥሮ ሀብት ዙሪያ ያሉት መረጃዎች የፕሮጀክት ሃሳብ ለማመንጨት ደካማ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ እንደ አቶ አቢ ገለፃ፣ ከጥጥ የተለየ አንጻራዊ ጠቀሜታ፣ ከ322 ሄክታር መሬት ቢኖርም የት? በምን ያህል ሄክታር? ምን አይነት አፈር? የመሰረተ ልማት ሁኔታና ማበረታቻ በማሳየት ያለው መረጃ ገላጭ አለመሆኑን ለዚህም በስፋት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ካሉት አንፃራዊ ጠቀሜታ አኳያ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና ሌጦ፣ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ሆቴልና ቱሪዝም፣ አግሮ ፕሮሲሲንግ ኢንዱስትሪዎች ኮንስትራክሽን አኳያ ስትራቴጂ ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም ተገቢውን ያህል ባለሐብቶች አለመገኘታቸውን አቶ አቢ ገልፀዋል፡፡ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ እንዲሠማሩ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን የገለፁት አቶ አቢ፣ በፊት ጊዜ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ዜግነቱን የቀየረ እንደ ውጪ ባለሐብት ተቆጥሮ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲኖራቸው ይጠይቅ የነበረው ሁኔታ ቀርቶ በአሁኑ ጊዜ እንደ ውጪም ሆነ አገር ውስጥ ባለሐብት በመረጡበት ሁኔታ የአገሪቱን የኢንቨስትመንት ሕግ ጠብቀው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱን ገልፀዋል፡፡ ማበረታቻ በሚደረግባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ የአገር ውስጥም ሆነ የውጪ ኢንቨስተሮች ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ገልፀው ከገቢ ግብርና እፎይታ በማይሰጣቸውና ከቀረጥ ነፃ ለማይሆኑ ዘርፎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደማይሰጥ ጠቁመዋል፡፡ በአዲስ አበባ አብዛኛዎቹ የኢንዱስትሪ ዞኖች በመያዛቸው ብዙ ጥያቄ ቢኖርም ከመሬት አሰጣጥ አኳያ ችግር መኖሩንም ተናግረዋል፡፡ ባለፉት 14 ዓመታት ከ331 ቢሊየን በላይ ያስመዘገቡትና ፈቃድ ከተሰጣቸው 28..230 የአገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች ወደ ሥራ የገቡት ቁጥር አናሳ ቢሆንም በተግባር ላይ ያሉት ከ300..000 በላይ ሰዎች ቋሚ የሥራ እድል መፍጠራቸውም ተመልክቷል፡፡ ፈቃድ የወሰዱት ባለሃብቶች በንግድና ባለኮከብ ሆቴሎች በታች ኢንቨስት የሚያደርጉትን ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደማያገኙም ተገል..ል፡፡ በቤዛዊት ሥዩም |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |