Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ንዋየ ቅድሳትና ቅርሳ ቅርሶች ወደ...
ንዋየ ቅድሳትና ቅርሳ ቅርሶች ወደ... Print E-mail
Wednesday, 16 April 2008
ንዋየ ቅድሳትና ቅርሳ ቅርሶች ወደ አውስትራሊያ ሊላክ ሲል ተያዘ

አንድ 20 ፊት ኮንቴነር ሙሉ የቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳትና ባህላዊ እቃዎች በጅቡቲ በኩል ወደ አውስትራሊያ ሊላክ ሲል ጋላፊ ኬላ ላይ መያዙን የሰሜን ምስራቅ ቀጠና ጉምሩክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ቱጂ አስታወቁ፡፡

አቶ ጌታሁን ለሪፖርተር ጋዜጣ እንዳስታወቁት በርካታ የብር መስቀሎች፣ ጸናጽል፣ ማጠንት፣ የቤተክርስቲያን አልባሳት እንዲሁም ከእንጨት የተሰራ እንስራ፣ ጋን፣ ባሕላዊ ወንበሮችና መሰል የቅርስ እቃዎች ወደ አውስትራሊያ ሲላክ መጋቢት 20 ቀን 2000 ዓ.ም በኬላው የፍተሻ ሠራተኞች ተይዟል፡፡

በኃላፊው ገለፃ መሠረት እንዲህ አይነት የቅርስ እቃዎች በኬላው በኩል ወደ ውጭ ለመላክ ሲሞከር የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ ጌታሁን የጉምሩክ ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በ1996/97 በተፈራረመው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት እንደዚህ አይነት እቃዎች በፖስታ አገልግሎት ድርጅትና በኤርፖርት በኩል በሕጋዊ መንገድ የሚላኩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በየብስ መጓጓዣ ወደ ውጭ መላክ ስለመቻሉ የተገለፀ ነገር አለመኖሩን አብራርተዋል፡፡

በዚህም መሠረት እቃው በቁጥጥር ሥር ውሎ ለሚመለከተው አካል ማለትም ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ለመላክ ዝግጅት መደረጉን አቶ ጌታሁን አስታውቀዋል፡፡ ይህንኑ በተመለከተ ለጉምሩክ ባለሥልጣን የኦፕሬሽን መምሪያ ክፍል ማሳወቃቸውን ገልፀዋል፡፡

የእቃው ባለቤት የባንክ ፐርሚት (መፍቀጃ) ቢኖረውም፤ በስምምነቱ መሠረት እንዲህ ያለ እቃ ወደ ውጭ ስለመላኩ በግልጽ ባለመገለፁ በቁጥጥር ሥር ውሎ የማጣራት እርምጃ እንዲካሄድ መደረጉን አቶ ጌታሁን አስታውቀዋል፡፡
 
እቃው እንዲያልፍ ፈቃድ መስጠት ያለበት ባለሥልጣኑ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጌታሁን፤ "እኛ ጋር እንደዚህ አይነት እቃ በየብስ ወደ ውጭ እንዲላክ የሚፈቅድ መመሪያ የለም" ብለዋል፡፡

ጋላፊ በኢትዮጵያና በጅቡቲ ድንበር ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ ኤክስፖርት የሚደረግ እቃ ፍተሻ የሚደረገው ጋላፊ ላይ መሆኑንና እስከዛሬ በተደረገ ፍተሻ ንዋየ ቅዱሳንና የባህላዊ የቅርስ እቃዎች ተይዞ እንደማያውቅ አብራርተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ውሳኔውን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን እንዲወስን እቃው በወታደር ታጅቦ ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክ አቶ ጌታሁን አስታውቀዋል፡፡

በተሾመ ንቁ
 
< Prev   Next >