| የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንክን ለመመስረት... |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንክን ለመመስረት ስምምነት ላይ ተደረሰ በአፍሪካ ውስጥ ተጠቃሽና ተሰሚ የፋይናንስና የገንዘብ ፖሊሲ በማውጣት አንድ ወጥ የሆነ የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንክ ለመመስረት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ፡፡ የአፍሪካን ኢንቨስትመንት በአፍሪካውያን ባንኮች እንዲደገፍ ለማድረግ የአፍሪካ ›=”yeƒS”ƒ v”¡ ”ÅT>ÁeðMÓ uSS’< ”Ç=G<U ¾}ªHÅ‹ አፍሪካን ለመፍጠር በፋይናንስና በቢዝነስ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ተሰሚነት ያላቸው የአፍሪካ ሞኒተሪ ባንክን ለማቋቋም ጥረት እያደረጉ ያሉት የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንኮች ማኅበር በኩል መሆኑን አፍክ የተባለው ጋዜጣ ከትሪፖሊ ዘግቧል፡፡ የማኅበሩ ፕሬዚዳንትና የሊቢያ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ፈረሃት ቤን ድሃራ ሰሞኑን በማኅበሩና በአፍሪካ ኅብረት መካከል ስለሚኖረው ፍሬም ዎርክ ውይይት ማድረጋቸውንና ለአፍሪካ አገሮች ጠቃሚ ይሆናል ተብሎ የታመነበትን የፋይናንሻል ተቋማት ምስረታ ለማከናወን ስምምነት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አያይዘው እንደተናገሩትም ሊቢያና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ባለፈው እሁድ ትሪፖሊ ውስጥ ባደረጉት ስምምነት የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ባንክን ለመመስረት በቅድሚያ የሚያስፈልገውን የመመስረቻና የማስታወቂያ ሥራ የሚሠራው ኮሚሽን በማቋቋም ወደ ሥራ የሚገባበትን ጥርጊያ መንገድ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡ ከስምምነቱ በኋላ በወጣው መግለጫ፣ የባንኩ ፖሊሲ በኤክስፐርቶች እንዲዘጋጅ ከዚያም የማኅበሩ ሥራ አስፈፃሚ የት ይሁን የሚለውንና የባንኩን የወደፊት አቅጣጫ በሚመለከት በመጪው ሚያዚያ 2000 አዲስ አበባ ውስጥ በሚካሄድ ስብሰባ ውሳኔ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህንን ተቋም ለመመስረት ሊቢያ ሃሳብ በማቅረቧ መስሪያ ቤቱ የት ይሁን የሚለው ጉዳይ አከራካሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |