Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ኢትዮጵያ የጊኒዎርም በሽታን በመከላከል...
ኢትዮጵያ የጊኒዎርም በሽታን በመከላከል... Print E-mail
Wednesday, 16 April 2008
ኢትዮጵያ የጊኒዎርም በሽታን በመከላከል ላገኘችው ውጤት የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነች

ኢትዮጵያ የጊኒዎርም /አርኪሶርኪያስስ/ በሽታን በመከላከል ላገኘችው ውጤት ከፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር የምስክር ወረቀት አገኘች፡፡ የምስክር ወረቀቱን ከፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር የተቀበሉት በናይጄሪያ አቡጃ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሱለይማን ደደፎ ናቸው፡፡
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ውስጥ በሽታው ከሚገኝባቸው ዘጠኝ አገራት መካከል የምስክር ወረቀቱን ያገኙት ኢትዮጵያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቶጐ እና ኮትዲ..ር ናቸው፡፡ የምስክር ወረቀቱ በኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራትና ከዚያ በላይ ባሉት ጊዜያት የጊኒዎርም በሽተኛ ያልታየባት ምድር መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ውጤቱ ሊገኝ የቻለው ካለፉት 15 ዓመታት ጀምሮ በሽታውን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረጉት በርካታ ጥረቶች መሆኑን ተገል..ል፡፡

የኢሚግሬሽን ኃላፊ የነበረውና የሀሰት ፓስፖርት ይዛ ከአገር ልትወጣ የነበረችው ተቀጡ

የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን የቦሌ ኢሚግሬሽን ዋና ክፍል ኃላፊና አንዲት ግለሰብ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በሁለት ዓመት እሥራት እንዲቀጡ መወሰኑን የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በመሠረተው ክስ ቅጣቱ ሊወሰንባቸው የቻለው የተሠጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት ለግል ጥቅሙ ለማዋል በማሰብ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነችውን ግለሰቧ የራሷ ባልሆነ የሀሰት ስም በተዘጋጀ ፓስፖርት ከሀገር ለመውጣት ስትሞክር ተይዛ ስትቀርብለት ኃላፊው ተገቢውንና ከኃላፊነት የሚጠበቅበትን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ሲገባው 5 ሺህ ብር መደለያ በመቀበሉ ነው፡፡

በሰሜን ጎንደር የመተማ ዩኒየን ሰሊጥና ጥጥ ለውጪ ገበያ ሊያቀርብ ነው

በበሜን ጎንደር ዞን የመተማ ገበሬዎች ዩኒየን ለመጀመሪያ ጊዜ 60 ሺህ ኩንታል ሰሊጥና ጥጥ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን የመተማ ማስታወቂያ ጽሕፈት ቤት ገለፀ፡፡

ባለፉት ዓመታት አርሶ አደሩ የምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት የመረከብ ለሀገር ውስጥ ገበያ ሲያቀርብ መቆየቱን በዚህ ዓመት ምርት ወደ ውጭ ሀገር መላክ የሚያስችለውን ህጋዊ ፈቃድ አውጥቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ በመተማ ወረዳ ከሚገኙ ጥጥና ሰሊጥ አምራች አርሶአደሮች አንድ ኩንታል ሰሊጥ በአንድ ሺህ 211 ብረ ጥጥ ደግሞ በኩንታል 400 ብር በመግዛት ምቹ የገበያ ሁኔታ በመፍጠር ላይ መሆኑን አብራርቷል፡፡

በንብ ማነብ የተሰማሩ አርሶ አደሮች 15 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ገቢ አገኙ

በደቡብ ጎንደር ዞን በንብ ማነብ ሥራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ከማር ምርት ከ15 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ የአርሶ አደሮቹ ገቢ ባለፈው ዓመት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ አሳይቷል፡፡

በመስኩ የተሰማሩት 49ሺህ አርሶ አደሮቹ ገቢውን ያገኙት ባለፉት ስምንት ወራት ለገበያ ካቀረቡት ከ850 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ማር ሽያጭ ነው፡፡ ከማር ሽያጩ ከፍተኛው 5 ሺህ ብር ዝቅተኛው ደግሞ 900 ብር ማግኘታቸውም አመልክተዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ምርቱን ያገኙት ከ6 ሺህ በላይ ዘመናዊ የሽግግርና ባህላዊ ቀፎዎችን በመጠቀም መሆኑን፣ ከፍተኛ የማር ምርት ሊያገኙ የቻሉት የግብርና ባለሙያዎች የተጠናከረ የኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠታቸውና የተመቻቸ የመኸር ዝናብ ስለነበረ መሆኑንም ገል..ል፡፡
 
< Prev   Next >