Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Monday
Oct 06th
Home
You are not authorised to view this resource.
You need to login.
Headline
  • Pause
  • Previous
  • Next
1/10
የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ተነሱ
-ቤተሰቦቻቸው ሙሉ በሙሉ ከአገር ወጥተዋል

በአሰግድ ተፈራ

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ሀሰን በግምገማ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉ ተሰማ፡፡ ከሁለት ወር በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የክልሉን ባለሥልጣናትና የፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ ላይ አነጋግረው ነበር፡፡
Read more...
 
Zena
ዳሽን ቢራ በሥራው ለመቆየት የቢራ...
ዳሽን ቢራ በሥራው ለመቆየት የቢራ መደቦችን ለማጠፍ ዝግጅት እንዲደረግ አሳሰበ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የዳሽን ቢራ፣ የደንበኞች የምርት አጠቃቀም፣ አቅም እየቀነሰ መሄዱን፣ በቢራ ኢንዱስትሪው ላይ የታየው የፍጆታ መዳከምና መቀዝቀዝ ማረጋገጫ እንደሆነና በሥራው ለመቆየት የቢራ መደቦችን ለማጠፍ ዝግጅት እንዲደረግ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ፡፡
Editorial
Image የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ...
የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ኢንቬስትመንት ሁኔታ፣ ችግርና መፍትሔ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ባለው የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ኢንቬስትመንት ላይ፣ በተለይም ለልማት ተወስደው ነገር ግን ሳይለሙ ታጥረውና ተጀምረው በሚቀሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን እየፃፍን ነው፡፡
 
Politics
Image ሲቪል ማኅበራትና ኤን.ጂ.ኦ አንድ ወይስ ሁለት?
በጌታቸው ንጋቱ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን መጀመሩን ተከትሎ ዘንድሮ ሊፀድቁ ከሚችሉ ሕጐች መካከል የሲቪል ማኅበራት ረቂቅ ሕግ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል፡፡ ዓለም አቀፍ የሠብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ረቂቅ ሕጉ የማያሠራ ነው በማለት ተደጋጋሚ ተቃውሞና ትችት እየሰነዘሩ የሚገኙ ሲሆን፣ በአገር ውስጥ ያሉት ድርጅቶች የሚሆነው ሕጉ ሲፀድቅ እናያለን በማለት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡
Briefs
ሙስናን ለመከላከል 48 አዳዲስ...

ሙስናን ለመከላከል 48 አዳዲስ የአሰራር ጥናቶች ሊደረጉ ነው

የፌደራል የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል የሚያስችሉ 48 አዳዲስ የአሰራር ሥርዓት ጥናቶችን እንደሚያካሂድ ገለፀ፡፡

 

 

 
Business & Economy
Image እነ ሐይሌ በአሠላ ከ50 ሚሊዮን ብር...
እነ ሐይሌ በአሠላ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ ግንባታዎችን አካሂደዋል

በዳዊት ታዬ

አትሌት ሃይሌ ገብረሥላሴን ጨምሮ አራት አትሌቶች ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ ግንባታዎች በአሠላ ከተማ ማካሄዳቸውንና ታዋቂ ያልሆኑ አትሌቶችም አሠላ ውስጥ በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች ውስጥ እየተሳተፉ መሆኑ ተገለፀ፡፡
Shemach
ርካሽ ግን አሳሳቢ ምርቶች
በናታን ዳዊት

ለተለያዩ አገልግሎቶች የምንጠቀማቸው ሸቀጣሸቀጦችና ሌሎች ምርቶች አብዛኛው ከውጭ የሚገቡ ናቸው፡፡ በቤት ውስጥ ከምንጠቀምባቸው ትናንሽ ቁሳቀሶች ጀምሮ እስከትላልቅ ማሽነሪዎች ድረስ ያሉ ምርቶች ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የውጭ ስሪቶች ስለመሆናቸው ያለንበትን አካባቢ መቃኘት ብቻ ይበቃል፡፡
 
Interview
Image “ሥርዓተ ትምህርቱ የቴክኖሎጂ...
“ሥርዓተ ትምህርቱ የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን ታሳቢ ማድረግ አለበት”

አቶ ዲሊሞ ኦቶሬ
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ዲሊሞ ኦቶሬ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ናቸው፡፡ የተወለዱት፣ የአደጉት፣ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ሆሳዕና ሲሆን ከሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ናቸው፡፡ በትምህርት ሥርዓቱና ተጓዳኝ በሆኑ ሥራዎች ዙሪያ ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሯቸዋል፡፡
Fermata
ታሪክ - ተዝካር አውጭ
በዘመናት፣ ውስጥ ታሪክና ሥራ የሌለው እጅም ልጅም፣ ወዳጅም፣ ተዝካር አውጭም ስም አስጠሪም የሌለው ነው፡፡ ተዝካር አውጭ ማለት ታሪክ ነው፡፡ ስም አስጠሪም ማለት ሥራ ነው፡፡ በሕይወቱ ሳለ የዋለባቸው ቀኖችና ያደረባቸው ሌሊቶች ሁሉ፤ የተመላለሰባቸው መንገዶች ከሕይወት በኋላ ምን ሠራህ? ምን ፈጠርህ? ምን አደረግህ? እስኪ አስረዳን? በማለት ሳይቆጣጠሩት እንደማይቀሩ ሕሊና ያመዛዝነዋል፡፡

 
Kibur Minister
ክቡር ሚኒስትር
("ለኢትዮጵያ ሕዳሴ ይተጋል" በሚል ርዕስ፣ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መንግሥት እየሰበሰበ ያወያያል፡፡ ባለሃብቶችን ለማወያየት ትልቅ ስብሰባ ተጠርቷል፡፡ አይፈሩም፣ አልተነካኩም፣ በግልጽና በድፍረት ይናገራሉ፤ የተባሉት ክቡር ሚኒስትር፣ "እናንተም ሳትፈሩ ተናገሩ፤ እኔም ሳልፈራ እናገራለሁ" የሚል መግቢያ ሰጥተው በባለሃብቶችና ኢንቨስተሮች ዙሪያ ያለው ችግርና ትጋት ላይ የሚወያይ ስብሰባ ከፈቱ)

Life & Art
Image "እኔን ትልቅ ዘፋኝ ያደረገኝ ሕዝብ ነው"

ታምራት ሞላ

ድምፃዊው ታምራት ሞላ ከስመ ጥር ድምፃውያን ተርታ ይሰለፋል፡ ለ46 ዓመታት በሙዚቃ ሕይወት ውስጥ ያለው የ61 ዓመቱ ታምራት በቅርቡ ባጋጠመው የጤና መታወክ ምክንያት ለሕክምና ወደ አሜሪካ ተጉዟል፡፡ ከመሄዱ በፊት ከጋዜጣው ሪፖርተር ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

 

 
Social
Image ቡታጅራ
በጌታቸው ንጋቱ

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ በ132 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ቡታጅራ ከተማ የመስቀል በዓልን ተንተርሣ ሰሞኑን ሞቅ ደመቅ ብላ ነው የሰነበተችው፡፡ ቡታጅራ የመስቀል በዓልን ለማክበር በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ተወላጆቿ ተሰባስበውባታል፡፡ የወረዳዋ ስያሜ በቅርቡ በመስቃንና ዶቢ በመባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መስማማት ባለማስገኘቱ ታስረው የነበሩት ብዛት ያላቸው ሰዎች ለበዓሉ መለቀቃቸው በዓሉን ደማቅ አድርጎታል፡፡ ቡታጅራ 37..163 ነዋሪዎች እንዳሏት የማዕከላዊ እስታስቲክስ መረጃ ያሳያል፡፡
Science & Technology
Image በሒሳብ ሥራ ዝሆኖች ከሰው ይሻላሉ
አንድ አዲስ ጥናት ዝሆኖች ከሰዎች በተሻለ በሒሳብ ሥራ ጎበዞች እንደሆኑ ማመልከቱ ዘ ሰን ዘግቧል፡፡

ሳይንቲስቶቹ በሁለት የተለያዩ እቃዎች ውስጥ ፍራፍሬዎችን በማስቀመጥ ዝሆኖችን የለቀቁ ሲሆን ዝሆኖቹ የተወረወሩትን ፍራፍሬዎች ብዛት በማስታወስ ብዙ ፍራፍሬዎች ወደያዘው ቅርጫት ማምራታቸው ለጥናቱ ድምዳሜ መሠረት ሆኗል፡፡

 
Diaspora
“ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የአጭር...
“ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የአጭር ጊዜ እርዳታ ሣይሆን ቋሚ ሥራ ነው”

በዳዊት ታዬ

ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ ለ27 ዓመታት ሆላንድ ውስጥ ኖረዋል፡፡ ወደ ውጭ የወጡት እንደ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊያን በደርግ ጊዜ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ነው፡፡ ባለትዳርና የአንዲት ልጅ አባት የሆኑት ኢንጂነር ታደሰ ከስደት መልስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የቤት አውቶሞቢል መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለመገንባት ችለዋል፡፡

Youth
ወጣት አብዮተኝነት በኬንያ
በምሕረት አስቻለው

የኬንያ ወጣቶች ባለፈው ሳምንት ለሶስት ተከታታይ ቀናት "አገራችንን ዳግም መገንባት፣ በህብረተሰባችን መካከል እርቅን ማስፈን፣ የወጣት ኬንያውያን ችግሮችና ተስፋዎች" በሚል መሪ ቃል ባደረጉት ስብሰባ በአገራቸው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጉልህ ተሳትፎ ለማድረግና የአመራር ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆናቸውን እንዳመለከቱ ዘኔሽን ዘግቧል፡፡

 
Opinion
ብቸኛው የሀገራችን ኳራንቲን ...

ብቸኛው የሀገራችን ኳራንቲን ያለሥራ ታጥሮ የተቀመጠ ቦታ አይደለም
(- ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የቀረበ)

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አካል የሆነው የኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር፣ በሀገራችን ኤኮኖሚያዊ ሕይወት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ከጀመረ ከ8 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ ድርጅቱ ለበርካታ ወገኖቻችን የሥራ እድል በማስገኘትና የሀገር ውስጥ ገበያን በማረጋጋት ለሀገራችንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በሥጋ ኤክስፖርት አንደኛ በመሆን ጉልህ ድርሻውን በመወጣት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

 

Letter to Reporter
ሚዛናችሁን አትሳቱ
ከሁለት ሣምንታት በፊት እሁድ ቀን በቤጂንግ ማራቶን አራተኛ የወጣውን አትሌት ድሪባ መርጊያ በሰጠው ቃለ ምልልስ የአቶ ጌታነህ ተሰማ ስም በማንሳት የአንድ ወገን አስተያየት ብቻ ተስተናግዷል፡፡
 
Women
ሴት አሽከርካሪዎች

በምሕረት አስቻለው

ከወንድ አሽከርካሪዎች ጋር ሲነፃፀሩ ሴት መኪና አሽከርካሪዎች በተለያየ መልኩ ጠንቃቆች እንደሆኑ ይነገራል፡፡ እኛም በአዲስ አበባ ከተማ ስላሉ ሴት አሽከርካሪዎች አንዳንድ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ መቆጣጠሪያና ምርመራ መምሪያ አመራን፡፡

 

Temuaget
ፓርላማው ሲከፈት

        "ሰኞ ሥራ አለብን""

የዘንድሮ የ2001 ዓ.ም የ"መስከረም ወር፣ የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ" የሚውለው በ26 ነው፡፡ ላለፉት 13 አመታት እንዳየነው በሕገመንግስታዊ ድንጋጌ እንደተወሰነውም የመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ "የፌዴራሉ መንግስት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የፌዴራሉ መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት" የሥራ ጊዜ መጀመሪያ ነው፡፡ ከዚህ ቀን ጀምሮ (በመካከል መንፈቀ ዓመቱ ላይ የሚኖረው የአንድ ወር እረፍት እንዳለ ሆኖ) እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ የሚዘልቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ዘንድሮ የሚጀምረው ሰኞ መስከረም 26 ቀን ነው፡፡

 

 
Law
የአክሲዮን ኩባንያ ዲሬክተሮች ቦርድ

በሰለሞን ጎሹ

ንቁ የሆነ የሕግ ማኅበረሰብ ያለው ሃገር መሠረታዊ የሕግ ጥሰቶችን አይታገስም፡፡ ልማድ ገንግኖ ሕጉን ቦታ እስኪያስለቅቀው እጁን አጥፎ አይመለከትም፡፡ ይህ ቡድን በሕግ አካዳሚክ ልሂቃን ይመራል፡፡ አይደለም በግልጽ የተቀመጡና አቋም ለመያዝ የማያስቸግሩትን ቀርቶ ከሰላማዊ የሕግ አንቀጾች ላይ በልዩ ሁኔታ ችግር ሊያጋጥም ይችላል በሚባልባቸው ቦታዎች ላይ መጠነ ሰፊ የውይይት፣ የክርክር እና የሐሳብ ልውውጥ ባህልን ያዳብራል፡፡

 

Zennk
ለአንድ አገር ጥንታዊነት...

ለአንድ አገር ጥንታዊነት ምስክሩ ከታሪክ ጋር የተያያዘ ባህሉ ነው

ታሪክ እንደሚነግረን የመስቀል በዓል መሠረቱ ንግሥት እሌኒ ከ200 ዓመት በላይ ተቀብሮ የነበረውን የጌታችንን መስቀል አስቆፍሮ ለማውጣት የወጠነችውን ተግባር ከመልካም ግብ መድረሱ ነው፡፡

 

 
Delalaw
ጤናችን በእጃችን?
ከሃሳብ አልተለየንም፡፡ ሰው ነንና እናስባለን፡፡ ለ2001 ዓ.ም ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ መስጠት ከጀመርን ቆይተናል፡፡ እንደ 2000 የሚሆን ከሆነ እንዲያልፈን ጠይቀናል፡፡ ይለፈን ብለናል፡፡ ምክንያቱም የተሻሻለ እንጂ የተወጠረ፣ የናረና የተናወጠ ኑሮ አቅለሽልሾን ነው፡፡
Teles
ችግር ያጋለጠው ምስጢር

በምሕረት አስቻለው

"ችግር አላደርገውም ያልኩትን እንዳደርግ አስገድዶኛል፡፡ ሲበዛ ሰው ፊት ያወጣል፡፡ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደሜ ውስጥ መገኘቱን ለማንም ሳልነግር ደብቄ ቆይቼ ነበር፡፡ ችግር ሲበረታብኝ፣ የጤናዬ ሁኔታ የግድ መድሃኒት መጀመር ያለብኝ ደረጃ ላይ ሲደርስ ራሴን ገልጬ ወጣሁ" ትላለች ወ/ሮ አልማዝ ከበደ፡፡

 

 
Sport
ነጻ ፕሬስ ነጻ ግለሰብን ሲያጠቃ

በመጀመሪያ ሪፖርተር ጋዜጣ ደረጃውን የጠበቀ የተመጠነና አግባብነት ያላቸውን የመረጃ ምንጮች በመጠቀም ለሚያቀርባቸው መረጃዎች ያለኝን አክብሮት ለመግለጽ እወዳለ

 

Taxi
ቆንጆዎቹና ፖለቲከኞቹ
ታክሲ ከሾፈሩ አይቀር ላዳ ነው፡፡ በተለይ ለኛ ለተቀጣሪ ሾፌሮች ላዳ ትመቸናለች፡፡ "ጥራት" ያለው አነስተኛ ሰው ይዞ መክነፍ፣ "ጥራት" ያለው የፖለቲካ ትንታኔ ለመስማት ያስችላል፡፡ ጥራት ያላቸው ቆንጆዎች ይዞ መብረር፣ ጥራት ያለው የሽቶ ዓይነት በመዓዛው ብቻ ለመምረጥ ያስችላል፡፡ ላዳ ውስጥ የጤፍና የዳቦ መወደድን እያወራ የሚያስጨንቅ አታዩም፡፡

 
World
ደቡብ አፍሪካ ለተፈናቃዮች...

ደቡብ አፍሪካ ለተፈናቃዮች እርዳታ መስጠት አቆመች
በኃይሌ ሙሉ

ደቡብ አፍሪካ ባለፈው ግንቦት ወር የውጭ አገር ዜጎች ጥላቻ ተነሳስተው ጥቃት በፈጸሙ ዜጎቿ ምክንያት ከቤታቸው ለተፈናቀሉ የተወሰኑ የውጭ አገር ዜጎች ስትሰጠው የነበረውን እርዳታ ያቆመች መሆኗን ሜዲካል ቻሪቲ ሜዲሲንስ ሳንስ ፍሮንቴየርስ (ኤም.ኤስ.ኤፍ) የተሰኘው በጎ አድራጊ ድርጅት አስታወቀ፡፡

 

 
  • Do You Know ?
    How To Increase Font Size
    You can increase the font size of the website if it appears smaller than normal. Just click the member area link at the top right of this page and the page will slide down. At the top left corner of the page, look for three small buttons. To increase font size, click the button with "+" sign and "-" sign to decrease font size.
  • Tips !
    Tips for Amharic Version
    • Use Internet Explorer version 6 or better
    • Adjust your screen resolution to 1024 X 768
    • Use the font resizer to increase font size if needed
    • Though it is not strictly needed having power geez unicode font could enhance the font rendering in your browser
 

Notice

Dear Visitors, we are currently moving our web site to a new server to better serve you with fast and accessible site. While we are doing this you might find broken links and missing images. Therefore, we would like to ask you to wait patiently until we restore our site to its original state with all missing images and a new streaming audio/video service.