| የልማት ድርጅቶችን ከውድቀት ለመታደግ |
|
|
| Wednesday, 16 April 2008 | |
|
በማምረት አቅማቸው ደካማ የተባሉ አንዳንድ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለግሉ ዘርፍ በሊዝ ለተወሰነ ዓመት በኪራይ ይተላለፋሉ፡፡ ድርጅቶች በሊዝ ሲከራዩ ለግል መጠቀሚያ እንዲሆኑ የሚያመቻቹ እንዳሉ በእኔ የምለው ገጽ የወጣው ጽሑፍ ያመለክታል፡፡ በአንድ ወቅት የአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን በቱሪካዊ ዜጋ አማካይነት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በዝብዞ ሹልክ ብሎ መውጣቱ ተገል"ል፡፡ ሚያዚያ 5 ቀን 2000 በሪፖርተር ጋዜጣ "እኔ የምለው" ገጽ "በሊዝ የሚከራዩ ድርጅቶች ይመርመሩ" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሁፍ ለዚህ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ቱርካዊ ያንን ያህል ገንዘብ ሲመዘብር በወቅቱ ክትትል አድርጎ ገንዘቡን ለማስከፈል የተንቀሳቀስ የመንግሥት አካል የለም፡፡ በሩ ክፍት ተደርጎለት እንደልቡ ከመዘበረ በኋላ ሲበቃው ወደ አገሩ ተመልሷል፡፡ ይህ የሚያሳየው የጥቅሙ ተጋሪ የሆኑ የአንዳንድ ባለሥልጣኖች እጅ እንዳለበት ነው፡፡ "ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ" እንዲሉ ከሄደ በኋላ ለይስሙላ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጓል፣ በሌለበት ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ የአዋሳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካም የቱርክ ዜግነት ባለው ሌላ ባለሀብትም ተመሳሳይ ዕጣ ደርሶበታል፡፡ ይኸኛው ባለሀብት ደግሞ ተቆርቋሪ ሠራተኞችን በማባረር፣ በማንሳፈፍ፣ በማገድና አስገዳጅ የዓመት ፈቃድ እንዲወጡ በማድረግ ለዓላማው ደጋፊ ሠራተኞች ዕድገት በመስጠት ችግሩን ተዳፍኖ እንዲቀር የማድረግ ሥራ አከናውኗል፡፡ በዚህም የጥቅም ተካፋይ የሆኑ እጅ የለበትም ማለት ይከብዳል፡፡ በፕራይቬታይዜሽን ስም የግል ጥቅምን በማሳደድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሻጥር ይፈፀማል፡፡ ሠራተኛው ለችግር ለሥራ አጥነትና፣ እንግልት ይዳረጋል፡፡ ስለሆነም ጉዳዩ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከውድቀትና ከብዝበዛ ይታደጋቸው እንላለን፡፡ (ሞገስና ሐብቴ፣ ከወሎ ሰፈር) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |