| ልዩ ቡናን ወደ ገበያ ለማቅረብ... |
|
|
| Wednesday, 16 April 2008 | |
|
ልዩ ቡናን ወደ ገበያ ለማቅረብ ኢትዮጵያ ሰፊ ዕድል አላት
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠውን “ስፔሽያሊቲ ኮፊ” (ልዩ ቡና) ለገበያ ለማቅረብ ያላትን ደረጃ ለማሻሻል ሰፊ እድል እንዳላት ተጠቆመ፡፡ የራስዋ የሆኑ የቡና ቀማሾችንም እያበራከተች ነው፡፡ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ የቡና ገበያን የዳሰሰው የአሶሸትድ ፕሬስ ዘገባ እንዳመለከተው ልዩ ቡና በማምረትና ለገበያ በማቅረብ የቡና ኤክስፐርቶች ወሳኝ በመሆናቸው ኢትዮጵያ ይህንን እድል እየተጠቀመችበት ነው ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ “በስፔሽያሊቲ ኮፊ” ያላትን ደረጃ ከፍ ለማድረግና በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንድትሆን ለማድረግ ሰፊ እድል እንዳላት የጠቆሙት በግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የቡና ልማት ከፍተኛ ኤክስፐርትና የብሔራዊ የቡና ጥራት ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ኢሳያስ ከበደ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ደግሞ በስፔሽያሊቲ ኮፊ ቀደምት ለመሆን ለኢትዮጵያውያን ቡና ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠናም አንዱ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ “ኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ እየጨመረ በመምጣቱ እ.ኤ.አ በ2006/2007 በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና ሽያጭ አምስተኛ ደረጃ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥም ከቡና ሽያጭ 194 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ እንዳገኘች አመልክቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ 119 ሚሊዮን ፓውንዱ “ከስፔሽያሊቲ ኮፊ” የተገኘ እንደሆነም ጠቁሟል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሻለ ዋጋ የሚሰጠው “ስፔሽያሊቲ ኮፊ” ምርትን እያሳደገች በመምጣትዋ እነዚህን የቡና ዓይነቶችን በማቅረብ ከኮሎምቢያና ከጓቲማላ ቀጥላ ሦስተኛዋ አገር ልትሆን መቻልዋንም ይፋ አድርጓል፡፡ በአቶ ኢሳያስ አገላለፅ መሠረት፣ ልዩ ቡና ተብለው ከሚቀርቡት ውስጥ ኦርጋኒክ ቡና፣ የጫካ ቡና፣ ከፊል የጫካ ቡና እና ሌሎችንም የቡና ዓይነቶች ከሌሎች አገሮች በተለየ መልኩ ለማምረት እድል ስላላት ይህንንም ምርት በበቂ ሁኔታ በማቅረብ አሁን ያለውን ደረጃዋን ማሻሻል ትችላለች፡፡ የኢትዮጵያን ቡና የገበያ ድርሻ ከፍ ለማድረግና ተመራጭ የሆኑ ምርቶችን ለማቅረብ በአገር ውስጥ የቡና ጥራትን በቅምሻ የሚያረጋግጡ ኢትዮጵያውያን ኤክስፐርቶች ቁጥር እንዲጨምር እየተደረገ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የቡና ጥራትን በመቅመስ ደረጃ ማውጣትና የቡና ዓይነትን በመለየት ለገበያ እንዲቀርብ የማድረጉ ሥራ በአብዛኛው በውጪ ኩባንያዎች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፣ በአሁኑ ወቅት ግን ከውጪ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ባለሙያዎች እንዲሰለጠኑ በመደረጉ በቅምሻና በደረጃ አሰጣጥ ዙሪያ ይታይ የነበረው ክፍተት እየጠበበ መምጣቱን አስረድቷል፡፡ በባለሙያዎች ገለፃ መሠረት ደግሞ፤ ላለፉት አምስት ዓመታት በቡና ገዥዎች፣ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የክልል መንግሥታት በትብብር እንዲሠሩ መደረጉ ኢትዮጵያ ውስጥ የቡና ጥራትን በመቅመስ የቡና ጥራትና ደረጃን የሚያረጋግጡ ባለሙያዎች እንዲፈጠሩ ሊያደርግ ችሏል፡፡ ለኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የሚታወቀው የአሜሪካ ስፔሽያሊቲ ኮፊ አሶሴሽን ሲሆን፣ የአሶሴሽኑ ተወካይና የሥልጠናው መሪ ሚ/ር ቲድ ሊንግል እንደገለፁት፣ ቡናን በማሽተትና በመቅመስ የቡናን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ከተቻለ ማረጋገጫ የተሰጠው ቡና ኮፊ ብሎ እንዲሸጥ ያስችላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሥልጠና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ የቡና ምርት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ በመሆኑ በተለይ ባለፈው ዓመት በኢንተርኔት በተደረገ ያልተቆላ የቡና ሽያጭ ላይ አንድ ፓውንድ ቡና በ130 ዶላር በመሸጥ ሪከርዱን የያዘው የፓናማ ቡና እንደነበር ያስታወሰው የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ፣ በተጀመረው ስልጠናና ሥራ ከቀጠለ በፖናማ ተይዞ የነበረው ደረጃ የኢትዮጵያ እንደሚሆን ግምቱን ሰጥቷል፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |