Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow በዓለም ደረጃ የተከሰተው ግሽበት...
በዓለም ደረጃ የተከሰተው ግሽበት... Print E-mail
Wednesday, 16 April 2008
በዓለም ደረጃ የተከሰተው ግሽበት የአንድ ትሪሊዮን ዶላር ኪሣራን አስከትሏል

የበለፀጉ አገራት መሪዎች በዓለም ላይ እየደረሰ ያለውን የገንዘብ ቀውስና የምግብ ዋጋ መናር ለመቆጣጠር ወሳኝ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የዋጋ ግሽበት አንድ ትሪሊዮን ዶላር ኪሣራን አስከትሏል፡፡


ባለፈው እሑድ የተጠናቀቀውን የበለፀጉ አገራት የገንዘብ ማኒስትሮችና የብሔራዊ ባንክ ገዢዎች የሦስት ቀናት ጉባዔ ተከትሎ አሶሴትድ ኘሬስ እንደዘገበው፣ በዓለም ላይ የተከሰተውን የምግብ ዋጋ መወደድና ይህም ቀውስ ያመጣውን ግሽበት ለመቆጣጠር አዳዲስ አሠራሮች ሥራ ላይ ሊውሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ አገራት ተወካዮች እና 185 አገሮችን በአባልነት ያካተቱት የዓለም ገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በዚሁ የግሽበት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደነበርም አመልክቷል፡፡ ዓለም አቀፎቹ የገንዘብ ተቋማትም ወቅታዊውን ችግር ለማርገብ የበለፀጉ አገራት ካስተላለፏቸው ውሳኔዎች ጋር ተመሳሳይ የሆነ አቋም እንዳላቸው ዘገባው አመልክቷል፡፡

እንደዘገባው ከሆነ የወቅታዊው የዓለም ኢኮኖሚ ዋነኛ ችግር የሆነውና አሁን እየታየ ያለው የምግብ እህሎች መወደድ መንስዔ ተደርጐ እየተነሳ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ኢኮኖሚ ችግር ውስጥ እየገባ መምጣቱ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት እየደረሰ ያለው የገንዘብ ቀውስና የዋጋ ግሽበት እ.ኤ.አ በ1931 ደርሶ ከነበረው Great Depression በኋላ የመጀመሪያው ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

በኢንዱስትሪ የበለፀጉ አገራት በመጨረሻ ውሣኔያቸው ትኩረት ተሰጥቷቸው በፍጥነት (በመቶ ቀናት ውስጥ) መሠራት ይኖርባቸዋል ያሉዋቸውን ነጥቦች ያስቀመጡ ሲሆን ለተፈፃሚነቱም ሁለም ወገኖች ተባባሪ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ አገራት የጣሊያን ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሪዮ ድራጊ አንዷ የሆነችው የመፍትሔ ሃሳቡን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት “ያቀረብናቸው አዳዲስ ጭብጦች የፖሊሲ ውሳኔ የሚፈልጉ ናቸው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም በቅፅበት የተከሰተውን የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለበርካታ ዓመታት ከተመዘገበ እድገት በኋላ የመጣ መሆኑን ጠቁመው ይህ ችግር ሊከሰት እንደሚችል ከስድስት ወር በፊት አይታወቅም ነበር ብለዋል፡፡

አሶሽየትድ ኘሬስ፣ በዓለማችን ካሉ አገራት የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ከዩናይትድ ስቴትስ ኢኮኖሚ መናጋት ጋር ተያይዞ የተከሰተው ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆልና የፋይናንስ ድቀት ወደ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ኪሣራ እንዳስከተለ የዓለም የገንዘብ ድርጅትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ፖሊሲ አውጭዎች ቀውሱን ለመግታት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተጠይቀዋል፡፡ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ገበያ መረጋጋት (Global financial stability) የዓለም የገንዘብ ድርጅትን እንዲሰፍን ሁኔታውን ማመቻቸት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ሁሉም አገሮች ያጋጠማቸው ችግር ተመሳሳይ ባለመሆኑ ሁሉንም ሊያማክል የሚችል መፍትሔ መቅረብ እንዳለበት አይ አም ኤፍ አሳስቧል፡፡

የአይ አም ኤፍና የዓለም ባንክ የወቅቱ አጣዳፊ ሥራ የሚሆነው የምግብ ዋጋ ጥረት የፖለቲካ አለመረጋጋትና አመፅ ቀስቅሶ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ድህነት ቅነሳ ላይ መሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ይህ ካልሆነ ካለፉት እነዚህ ሀገሮች መጨረሻቸው ጦርነትና አለመረጋጋት እንደሚሆን የአይ ኤም ኤፍ ሊቀመንበር ዲሞኒክ ስትራውስ አስጠንቅቀዋል፡፡
 
< Prev   Next >