Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow “ኦፌዴን ከምርጫ ራሱን ማግለሉ...
“ኦፌዴን ከምርጫ ራሱን ማግለሉ... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
“ኦፌዴን ከምርጫ ራሱን ማግለሉ አግባብ አይደለም” አቶ መስፍን ነመራ
በፓርላማ የኦፌዴን ተጠሪ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሰያዊ ንቅናቄ /ኦፌዴን/ ዛሬ ከሚካሄደው የሁለተኛ ዙር የማሟያ የክፍለ ከተማና የቀበሌ ምርጫ ራሱን ማግለሉ አግባብ አይደለም ሲሉ የፓርቲው የፓርላማ ተጠሪ አቶ መስፍን ነመራ ቅሬታቸውን አሰሙ፡፡  ፓርቲው ውሳኔው በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተላለፈ መሆኑን በመግለፅ በአባሉ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡
አቶ መስፍን ፓርቲው ከምርጫው ራሱን ስለማግለሉ ባለፈው ረቡዕ ዕለት ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

አቶ መስፍን የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከምርጫ ራሱን ማግለሉ ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ኦፌዴን በዛሬ ምርጫ በትንሹ ሦስት ቦታዎች ላይ ማሸነፍ የሚችልበት እድል መኖሩን ጠቅሰው የፓርቲውን ውሳኔ ተቃውመዋል፡፡

የፓርቲው የፓርላማ ተጠሪ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔውን አስመልክቶ እንደ ፓርቲ አባልነት ያላማከራቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ለምርጫው መሰዋዕትነትን ከፍለው ለድምፅ አሰጣጡ በተዘጋጁበት ወቅት ፓርቲው ከምርጫው ራሱን ማግለሉ አግባብ አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡ የፓርቲው ውሳኔም ጊዜውን የጠበቀ አለመሆኑን አቶ መስፍን ጠቁመዋል፡፡

የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ “አምባገነናዊነት ይታይበታል” ሲሉ አቶ መስፍን አማርረዋል፡፡ በዚህም የፓርቲው አባላት በጉዳዩ ላይ አለመወያየታቸውን ገልፀዋል፡፡

የአቶ መስፍንን ቅሬታ በተመለከተ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ፓርቲውን ከምርጫ መውጣት አለመውጣት ውሳኔ የሚሰጠው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የሥራ አስፈፃሚው ኮሚቴው በፓርቲው አባላት የተመረጡ መሆናቸውንና ፓርቲው የሚከተለውን አቅጣጫ የመወሰን ኃላፊነት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አያይዘውም አቶ መስፍን ከፓርቲው ስርዓት ውጪ የልዩነት አመለካከታቸውን በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት መሰንዘራቸው አግባብ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ “አቶ መስፍን እንደዚህ ዓይነት ጥፋት ሲያጠፉ የመጀመሪያው ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ያፈነገጠ ሀሳብ ያራምዳል” ሲሉ ተችተዋል፡፡

ለዚህም የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአቶ መስፍን አድራጐት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታውቀዋል፡፡

በተሾመ ንቁ
 
< Prev   Next >